Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና

Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተ።በየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ  "መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ...
03/09/2026

መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተ።

በየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ "መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ የበዓል ባዛር ተከፍቷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ግዛው ባዛሩ ሻጮችንና ሸማቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ የግብይት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ውጤታማና አጥጋቢ የግብይት ሥርዓት እንዲሰፍን የሁሉም አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ዶ/ር ኤፍሬም ባዛሩ በሰላማዊና ሥርዓት በተሞላበት መልኩ እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው፣ ባዛሩ ለነዋሪዎችና ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት የሚያግዝ፣ የግብይት ሥርዓቱን የሚያሻሽልና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

የባዛሩ ዓላማ በሸማቾች እና በአምራቾች መካከል ቀጥተኛ የግብይት ሥርዓትን በማጠናከር የምርት አቅርቦትን ማሳደግና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰቡ ማቅረብ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንዳልካቸው፣ ለባዛሩ ስኬታማ አፈጻጸም የተረባረቡ አካላትን በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

ባዛሩ በቀጣይም በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር እንዲጠናከር አስፈላጊው ሥራ በየደረጃው መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የተከፈተው የበዓል ባዛር እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማው ንግድ፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ህብረት ሥራ፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና እንዲሁም ሥራና ክህሎት ተቋማት በጋራ በመሆን የባዛሩን አገልግሎት እያስተባበሩ ይገኛሉ።
#የካ

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
03/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

የብልፅግና ዕሳቤ  ሁለንተናዊና ከፍ ያለ ራዕይ ያለው የልማት አቅጣጫ ነዉ! የብልፅግና ዕሳቤ የአንድ ዘርፍ ወይም የአንድ ዘመን የልማት አቅጣጫ ብቻ አይደለም። ሁለንተናዊ የሆነ የኢኮኖሚ፣ የ...
03/09/2026

የብልፅግና ዕሳቤ ሁለንተናዊና ከፍ ያለ ራዕይ ያለው የልማት አቅጣጫ ነዉ!

የብልፅግና ዕሳቤ የአንድ ዘርፍ ወይም የአንድ ዘመን የልማት አቅጣጫ ብቻ አይደለም። ሁለንተናዊ የሆነ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ ልማት፣ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የውጭ ግንኙነት ራዕይን ያካተተ ጥልቅ ዕሳቤ ነዉ፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግና የቁሳዊና የሰብዓዊ ፍላጎቶችን በማጣመር፣ የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል እና የሀገርን አቅም በማጎልበት የሚገነባ ልማት ነው።

የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በማጠናከር፣ ግብርናንና ኢንዱስትሪን በማስተሳሰር፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ አምራችነት ማሸጋገር ዋና ትኩረት ነው። የገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ በጥራትና በብዛት መተካት፣ የኤክስፖርት ምርትን ማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማስፋት እና ለዜጎች ዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር የኢኮኖሚያዊ ብልፅግና ዋና መሠረቶች ናቸው። በዚህ መርህ ላይ በመመርኮዝም ዘላቂ፣ ፈጣንና አካታች የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት፣ ድህነትን መቅረፍ እና የኑሮ ደረጃን ማሻሻል የብልፅግና ጉዞ ዋና ግቦች ናቸው።

ሰላምና ሀገራዊ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሁለንተናዊ ብልጽግና ዕሳቤ አንዱ አካል ነዉ፡፡ ልማት ያለ ሰላም ዘላቂ አይሆንም። ስለዚህ ሰላምን ማረጋገጥ፣ የሀገርን ሉዓላዊነትና ደህንነት ማስጠበቅ እና የሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር የብልፅግና ጉዞ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው።

የዲሞክራሲ ሥርዓትን ማስፋት፣ የዜጎችን ጥያቄዎች በተገቢው መመለስ፣ የማኅበራዊ ትሥሥርን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሁለንተናዊ ብልፅግና አካል ነው። የኢትዮጵያን ክብር፣ ጥቅምና ሉዓላዊነት በሚያስጠብቅ መንገድ የውጭ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ማስፋት እና የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት ማሳደግ የብልፅግና ራዕይ አካል ነው።

የብልፅግና ጉዞ በቀስታ የሚሄድ የልማት ጉዞ ሳይሆን፣ መፍጠር፣ መፍጠንና መዝለል በሚሉ የልማት አቅጣጫዎች የተመራ ጥረት ነው። ዓላማውም የኢትዮጵያን የሰው፣ የተፈጥሮና የኢኮኖሚ ሀብቶች በብቃት በማንቀሳቀስ፣ ምርታማነትን በማሳደግና የዜጎችን ተሳትፎ በማጠናከር በአንድ ትውልድ ዕድሜ ውስጥ የበለፀገች፣ ሰላማዊና ተወዳዳሪ ኢትዮጵያን መገንባት ነው።

ሁለንተናዊ ብልፅግና ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር፣ የዜጎች የተሻለ ኑሮ፣ የሀገር አቅምና የጋራ ተጠቃሚነት ግብ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅርጠኝነት መስራት ይኖርበታል፡፡



የወል ትርክታችን የጋራ ታሪካችንን፣ እሴቶቻችንን እና የነገ ተስፋችንን በጋራ የምንገነባበት ጠንካራ መሰረት ነው። ባለፉት ዘመናት ያሳለፍናቸው ፈተናዎችና ያስመዘገብናቸው ድሎች የመላው ኢትዮጵ...
02/09/2026

የወል ትርክታችን የጋራ ታሪካችንን፣ እሴቶቻችንን እና የነገ ተስፋችንን በጋራ የምንገነባበት ጠንካራ መሰረት ነው። ባለፉት ዘመናት ያሳለፍናቸው ፈተናዎችና ያስመዘገብናቸው ድሎች የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ አሻራ ያረፈባቸው በመሆናቸው፣ እነዚህን የታሪክ ገጾች በበጎ እና በጋራ እይታ መቃኘት ለነገዋ ሀገራችን ብሩህ መንገድ ይከፍታል። በልዩነቶቻችን ውስጥ ያለውን ውበት አጎልብተን፣ ሁላችንንም የሚያስተስስሩንን የጋራ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶች ማጎልበት ስንችል፣ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ለሁላችንም የምትሆን የበለፀገች ሀገር መገንባት እንችላለን።

​ይህ የወል ትርክት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን መጎልበትና ለመዋሃዳችን ዋነኛ ማሰሪያ ገመድ ነው። ልዩነቶቻችን የውበትና የጥንካሬያችን ምንጭ እንጂ የመለያየታችን ምክንያት ሳይሆኑ፣ በጋራ መከባበርና እኩልነት ላይ የተመሰረተ ህብረት እንድንፈጥር ያስችሉናል። ሁላችንም የዚህች ታላቅ ሀገር እኩል ባለቤቶች መሆናችንን በሚያረጋግጥ መንገድ በጋራ በመቆም፣ የጥልና የጥርጣሬ ትርክቶችን በይቅርታና በፍቅር በመተካት የህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ማጽናት ይኖርብናል።

በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05፣06፣07 እና 08 አስተባባሪነት "የወል ትርክታችን ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን" በሚል መሪቃ የስነፅሁፍ መድረክ ተካሄደ።







የኢትዮጵያ ማንሰራራት!የዘንድሮው የጳጉሜን ወር "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች፣...
02/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!

የዘንድሮው የጳጉሜን ወር "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች፣ ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በፅናትና በፈጠራ በመሻገር፣ በአሁን ወቅት በማንሠራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

የጳጉሜን ወር በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዘይቤ ውስጥ ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን የተገኙ ወረቶች የሚደመሩበት እንዲሁም ለቀጣዩ ዓመት የከፍታ ጉዞ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት ልዩ ሀገራዊ መለያችን ነው።

የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባበር የነበሩ ጥንካሬዎችን የሚያስቀጥል፣ የታዩ ክፍተቶችን የሚያርም፣ አዳዲስ የፈጠራ ስልቶችን ታሳቢ ያደረገ፣ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በሚገባ የሚጠቀም፣ የተመዘገቡ ትላልቅ ስኬቶችን የሚያስታውስ፣ አዳዲስ ብስራቶችን የሚያበስር በመሆሃ በሳቢ ኹነቶችና የንቅናቄ መንገዶች የሚመራ ይሆናል።

የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት አከባበር ከቀደሙት ዓመታት በተለየ መልኩ በብሥራት፣ በተስፋ እና በሁለንተናዊ የብልጽግና ራዕይ ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ አመላክቷል።

የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት፤ ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)፣ ጳጉሜን 2 (የማንሰራራት ቀን)፣ ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)፣ ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን) እንዲሁም ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን) በሚሉ መርሃ-ግብሮች በድምቀት የሚከበሩ ይሆናል።

የአስተሳሰብና የተግባር አንድነታችንን በማጠናከር በተደመረ ትጋታችን ሀገራችንን እንገነባለን!ለሀገር ዕድገት፣  ለህዝብ ተጠቃሚነት የድርሻን መወጣት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የዜግነት ሀ...
02/09/2026

የአስተሳሰብና የተግባር አንድነታችንን በማጠናከር በተደመረ ትጋታችን ሀገራችንን እንገነባለን!

ለሀገር ዕድገት፣ ለህዝብ ተጠቃሚነት የድርሻን መወጣት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የዜግነት ሀላፊነት ነው፡፡ ሀገራችን የምትገነባው በጠንካራ ተቋማቶቿ እንዲሁም በሁሉም ዜጎቿ ታሪካዊ አሻራ በመሆኑ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ሀገራዊ እሴቶቻችንን ማጠናከር ተገቢ ነው።

የተቸገረን መርዳት፣ የተራበን ማብላት፣ የወደቀን ማንሳት፣ የተስፋ ቃል መናገርና በችግር ጊዜ አብሮ መቆም የሰብዓዊነትና የዜግነት ትልቁ መገለጫ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ የመጡ ማህበራዊ እሴቶች ናቸው፡፡

በሀሳብ የበላይነት ማመን፣ ምክንያታዊነትን መላበስ፣ ለህግ የበላይነት ተገዢ መሆን፣ የሌሎችን መብት ማክበር፣ ለሰላም መቆም፣ ለማህበረሰባችን ብቻም ሳይሆን ለሚመጣው ትውልድ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት አሻራን ማሳረፍም ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነትና ግዴታ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡

የህዝባችን የጠነከረ ማህበራዊ ትስስር የተገነባው በደስታውም በሀዘኑም አንዱ ለአንዱ አለኝታ በመሆን ነው፡፡ የመረዳዳትን፣ የመደጋገፍን፣ የመተሳሰብንና የአብሮነትን እሴቶችን በተግባር መተርጎም ለጋራ እጣፈንታችን ወሳኝ ሚና አለው፡፡

ሀገራዊ ጉዳዮችን ከግል ፍላጎት የሚያስቀድም አስተሳሰብ ስንላበስ፣ እጆቻችንን አብሮ ለመስራት እና ለመረዳዳት ስናስተባብር፣ ጉልበታችንን፣ ገንዘባችንን፣ እውቀታችንን ለሀገር ግንባታ ስናስተባብር የምንጓጓላትን የበለፀገች ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ እውን እናደርጋለን፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ከምርጫ ድል ማግስት — ጠንካራ ፓርቲ! ​በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም. የ4ኛ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።​በኮንፈረንሱ የሴቶች ክንፍ አባ...
01/09/2026

ከምርጫ ድል ማግስት — ጠንካራ ፓርቲ!

​በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም. የ4ኛ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

​በኮንፈረንሱ የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸምን በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።

​በመድረኩም የሴቶችን ተሳትፎና አመራር በማጠናከር፣ የአደረጃጀቱን አቅም በማሳደግና ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ያተኮሩ የቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

​በተጨማሪም፣ አዳዲስ አባላትን በማፅደቅ ፣ የወጡ አባላትን በመተካትና የአደረጃጀቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ፣ የቀጣይ ዘመን ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም የጋራ አቋም ተይዟል።



የአረንጓዴ አሻራ ቱሩፋቶች ለትውልድ ተሻጋሪ  ድሎች መሰረት ናቸው!የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ለማልማት እና ለቀጣይ ...
01/09/2026

የአረንጓዴ አሻራ ቱሩፋቶች ለትውልድ ተሻጋሪ ድሎች መሰረት ናቸው!

የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ለማልማት እና ለቀጣይ ትውልድ ምቹ አካባቢ ለማስረከብ የተጀመረ ህዝባዊ መሰረት ያለው ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።

ይህ ሀገራዊ ፕሮግራም የደን ሽፋንን በማስፋፋት፣ የመሬት መራቆትን በመከላከል፣ የውሃ ሀብቶችን በመጠበቅ እና የብዝሃ ሕይወት ሀብትን በማሳደግ ለሀገራችን ዘላቂ ልማት ጠንካራ መሠረት መሆኑ በተጨባጭ መረጋገጥ ጀምሯል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የልማት ኢኒሸቲቭ ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ምቹ መደላድል እየፈጠረ ይገኛል።

ሁሉም ዜጋ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ለተተከሉ ችግኞች በቂ እንክብካቤ በማድረግ የለመለመች፣ በሁለንተናዊ መልኩ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩሉን አሻራ በማሳረፍ ተስፋን መትከል ይገባዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

31/08/2026
ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተ...
31/08/2026

ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!

የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተግባራት የህዝባችን ብዝሀ አብሮነት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል።

የህዝባችን በጎ እሳቤዎች በተገቢው መንገድ ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራር ስርዓቶች መዘርጋታቸውም ለዕድገታችን መፋጠን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በክረምቱ ወራት ተወስነው የነበሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት፣ በተፈጠረው የአስተሳሰብ ለውጥ፣ እንዲሁም በዳበረው ሁሉንም አቅሞች የማስተባበር ቁርጠኝነት ዓመቱን ሙሉ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ለወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰጠው ልዩ ትኩረትም ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሚያከናውኗቸው በገንዘብ የማይተኩ ተግባራት ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እያጠናክሩ ነው።

የህዝባችን ጥንታዊ እሴቶች በየጊዜው እየተሸረሸሩ ከመምጣታቸው ባሻገር አቀናጅቶ የሚያስተባብር ተቋም ስላልነበር በተለያዩ አግባብ የሚገለፁ የሀብት፣ የጊዜ እንዲሁም የጉልበት ብክነቶች ሲስተዋሉ ቆይተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲን ሰው ተኮር እሳቤዎች አልቆ ለመተግበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የተቀናጀና የተደራጀ ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽንን በማቋቋም አገልግሎቱን ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው ማድረጉ የበጎ ፈቃደኞችን የተደመረ አቅም ፈጥሯል።


በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤትም በተለይም በወጣቶች ክንፍ እና በሴቶች ክንፍ አባላት አስተባባሪነት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊነት እና ዘላቂነት በልዩ ትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የታመሙትን በመጎብኘት ተስፋና ሞራል የመስጠት የበጎነት በሆስፒታል መልካም ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው።

ለአቅመ ደካሞች ቤት ገንብቶ የማስረከብ የበጎነት ተግባርም የበርካታ የሀገር ባለውለታ ዜጎችን ህይወት ማፍካት ችሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ባለፀጎችን በማስተባበር ያስገነባቸው የበጎነት መንደሮች ለከተማችንም ተጨማሪ ድምቀት ሆነዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተለይም በበዓላት ወቅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የሚያከናውነው ማዕድ የማጋራት ተግባርም በከተማችን በተገነቡ የምገባ ማዕከላት ተቋማዊ መልክ ይዞ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማስተባበር ዓመቱን ሙሉ እየተከናወነ መሆኑን ልብ ይሏል።

ደም በመለገስ በደም እጥረት ምክንያት ሊጠፋ የሚችል ህይወትን የመታደግ የበጎነት ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መምህራን በማስተማር፣ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ህሙማንን በማከም፣ ሌሎችም በየተሰማሩበት የሚያከናውኗቸው ሙያዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትም የከተማችንን ዕድገት አፋጥነዋል::

የፓርቲያችንን ሰው ተኮር እሳቤዎች በተግባር ለመተርጎም የሚደረገው ርብርብ ዘላቂ ዕድገትን እያረጋገጠ መሆኑ ተጨባጭ ሲሆን ፤ ማህበራዊ አካታችነትን እንዲሁም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ከፍ ማድረግ አስችሏል።

መልካም የስራ ሳምንት!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Address

Addis Ababa

Telephone

+251985116238

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share