Defence Construction Design Enterprise - DCDE

Defence Construction Design Enterprise - DCDE Defence Construction Design Enterprise mainly engaged in building & road design, and consulting.

26/09/2023
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አብሮ በመሥራት ጉዳይ ምክክር አድርጓል (መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት)፡፡ተቋ...
20/09/2023

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አብሮ በመሥራት ጉዳይ ምክክር አድርጓል (መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት)፡፡

ተቋማቱ በአጋርነት እና በትብብር በመሥራት ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ ብሎም በጊዜና የሃብት አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና ብክነትን በመቀነስ ጥራት ያለውን ሥራ መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረው መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መርዕድ ታዬ ድርጅቱ በግንባታ ዲዛይን ዝግጅት፣ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የማማከር ሥራዎች ላይ በሀገሪቱ የህንጻ፣ የመንገድ፣ የግድብና የመስኖ ግንባታ የሥራ ዘርፍ እየተወጣ ያለውን ክፍተኛ ሀገራዊ ድርሻ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሀገሪቱ የዘርፉ ገበያ ውስጥ በመሳተፍ እና ተወዳዳሪ በመሆን በግንባታው የልማት ዘርፍ ውስጥ ብቃት ያለው ተሳታፊ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ አሸናፊ ሆኖ በጥራት እና በሌሎች በጎ መለኪያዎች ተጠቃሽ ሆኖ ለመዝለቅ ድርጅቱ ያስቀመጣቸውን ግቦችና የቀረጻቸውን ስትራቴጂዎችንም ገልጻዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋሲሊቲዎች አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሚዴቅሳ ቶለሳ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባንኩ የኮንስትራክሽን እና የኮንትራት አስተዳደር አመራሮች፤ ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ እና የድርጅት ዕድገትና ገበያ ልማት መምርያ አመራሮች በጋራ ሆነው በመከሩበት በዚህ መድረክ ወደፊት አብሮ በአጋርነት ውጤታማ ሥራ መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት  በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 187/2002 ሐምሌ 2002 ዓ.ም መሰረት የተቋቋመ ለመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆኖ  በቦርድ እንዲመራ ተደርጎ ...
15/09/2023

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 187/2002 ሐምሌ 2002 ዓ.ም መሰረት የተቋቋመ ለመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆኖ በቦርድ እንዲመራ ተደርጎ የተዋቀረ የኮንስትራክሽን የዲዛይን ሥራ እና አማካሪ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ በተቋቋመበት ደንብ መሰረት በተሰጠው ስልጣንና ተግባር ከመከላከያ ተቋማትና ከሌሎች አካላት የሚቀርቡ የህንጻ፣ የመንገድ፣ የመስኖና የግድብ የዲዛይን፣ የቁጥጥርና የማማከር እንዲሁም የኮንትራት አስተዳደር እና የተለያዩ መሰል ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለፉት ዓመታት በርካታ የህንፃ እና የመንገድ የግንባታ ዲዛይን እና የኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን ለመከላከያ እና ከመከላከያ ውጪ ላሉ ደንበኞች በማከናወን በሀገራችን የግንባታ ሥራው ጥራቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋና ፍትሀዊነትን የተላበሰ እንዲሁም ከወቅቱ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ያለ ድርጅት ነው፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋነኛ ተልዕኮው በግንባታ ዲዛይን ዝግጅት፣ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የማማከር ሥራዎች ላይ በአገሪቱ የህንጻ፣ የመንገድ፣ የግድብና የመስኖ ግንባታ የሥራ ዘርፍ የሀገር መከላከያ ፍላጎትን በማሟላት የሰራዊቱን የወትሮ ዝግጁነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በሀገሪቱ የዘርፉ ገበያ ውስጥ በመሳተፍ እና ተወዳዳሪ በመሆን በግንባታው የልማት ዘርፍ ውስጥ ተሳታፊ መሆን ነው፡፡ በመሆኑም በገበያ ውድድር ውስጥ ብቃት ያለው ተሳታፊ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ አሸናፊ ሆኖ በጥራት እና በሌሎች በጎ መለኪያዎች ተጠቃሽ በመሆን በትርፋማነት ለመዝለቅ የሚያስችል ስትራቴጂ ቀርጾ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኝ የልማት ተቋም ነው፡፡

ተልዕኮ
• የግንባታ ፍላጎት ለማሟላት ማንኛውም የዲዛይን እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራዎችን መሥራት፣
• በተጓዳኝ የመንገድ፣ የግድብ፣ የመስኖ፣ የሕንጻና ሌሎች የማማከር፣ የዲዛይንና ኮንትራት አስተዳደር ሥራዎችን መሥራት፣
• ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎችን መሥራት፡፡

ራዕይ
የመከላከያን የመሠረተ ልማት ግንባታ ዲዛይንና የኮንትራት አስተዳደር ፍላጎት በማሟላት በተቋሙ አስተማማኝ የዝግጁነት አቅም በመፍጠርና እየተመዘገበ ባለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የራሱን ድርሻ የሚጫወት ተመራጭ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን አቅም ሆኖ በ2020 ዓ.ም ማየት

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የሥራ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች የመከላከያ ስፔሻይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድ...
08/09/2023

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የሥራ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች የመከላከያ ስፔሻይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡

ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት) በዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መርዕድ ታዬ የተመራው የድርጅቱ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በቢሾፍቱ ከተማ ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘውን የመከላከያ ስፔሻይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ጎብኝተዋል።

የሆስፒታሉ ጠቅላላ ዲዛይን ሥራ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ተሠርቶ ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚኘው ይህ ሆስፒታል በቢሾፍቱ ከተማ አጠቃላይ ስፋቱ 76,560 ካሬ ሜትር የተንጣለለ ግቢ ውስጥ በ29 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በህክምናው ቴክኖሎጂ የተደረሰበትን አብዛኛውን ግብዓት ያሟላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሆስፒታሉ ኃላፊ ጀነራል ሸዋዬ ኃይሌ ታካሚዎች ለከፍተኛ ህክምና ውጭ ሀገር ድረስ በመሄድ የሚደርስባቸውን እንግልትና ከፍተኛ ወጭ የሚቀንስ እናም በአህጉር ደረጃ ተወዳደሪ የሚሆን የህክምና ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሆስፒታሉ ከፍተኛ ህክምና ከመስጠት ባሻገር የህክምና ግብዓቶችን በማምረት በሀገራችን የሚታየውን የግብዓት ችግር ለመቅረፍም ጭምር ታስቦ በዘመናዊ መንገድ የተገነባ መሆኑንም ጀነራል ሸዋዬ አሳውቀዋል፡፡

ሆስፒታሉ ቀድሞ ከሦስት አሥርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አየር ኃይል አማካይነት በ1975 ዓ.ም ታቅዶ በ1982 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ በወቅቱ በነበረው መጠን አገልግሎት መስጠት የጀመረ ቢሆንም በተፈላጊ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ጠቅሰው ነገር ግን የተደራጀ ዘመናዊ ሆስፒታል እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ተረክቦ በ2000 ዓ.ም ዘመኑ የደረሰበትን የህክምና ደረጃ በሚያሟላ መልኩ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ መጀመሩን፤ ጀነራል ሸዋዬ እና የግንባታ ፕረጀክት ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር አሸብር ተስፋዬ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መርዕድ ታዬ የግንባታ ዘርፉ ጥራት እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎችን በበለጠ ትኩረት እና በአጋርነት ለመሥራት በድርጅታቸው በኩል ያለውን ከፍተኛ ዝግጁነት ገልጸው በጉብኝቱ ላይ ለተደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

እንኳን ደስ ያላችሁ !በነበራቸው ማዕረግ በተለያዩ  የሥራ መደቦችና ኃላፊነቶች ተመድበው ተልዕኳቸውን በታላቅ ትጋትና ታማኝነት የፈጸሙ የተቋማችን ባልደረቦች የማዕረግ ሹመት አግኝተዋል፡፡ዛሬ ...
05/09/2023

እንኳን ደስ ያላችሁ !

በነበራቸው ማዕረግ በተለያዩ የሥራ መደቦችና ኃላፊነቶች ተመድበው ተልዕኳቸውን በታላቅ ትጋትና ታማኝነት የፈጸሙ የተቋማችን ባልደረቦች የማዕረግ ሹመት አግኝተዋል፡፡

ዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት እና በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እህት ተቋማት መደበኛ የማዕረግ መቆያ ጊዜያቸውን በስኬት ያጠናቀቁ ባልደረቦች በተሰጣቸው ሹመት በየደረጃቸው ማዕረግ ለብሰዋል፡፡

የማዕረግ ተሿሚዎቹ የሀገር ሉዓላዊነትን እና ሰላምን ከማስከበር ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፎች ላበረከቱት እናም እያበረከቱ ላለው ታላላቅ ተግባራት ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ ዛሬ የተሰጣቸው ማዕረግ ወደፊትም ሀገሪቱ የምትፈልጋቸው ተልዕኮዎችን ለመፈጸም እንዲነሳሱ እና የበለጠ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

05/09/2023

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን" በሚል መሪ ሐሳብ በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀውንኤግዚቢሽን ጎብኝቷል (ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም) ።

የድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች ኤግዚቢሽኑን ከመጎብኝት ጎን ለጎን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ በአጋርነት አብሮ መሥራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የግንባታው ዘርፍ ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ዲዛይንና ቁጥጥር በማድረግ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትልቅ አሻራ በማሳረፍ የዳበረ ልምድ ያለው ድርጅት እንደመሆኑ ከተቋማት ጋር በአጋርነት ስለሚሠራ ቸው ሥራዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት  ለሠራተኞች የግንዛቤ  ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ( የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት)  የሠራተኛውን ብቃትና ክህሎ...
05/09/2023

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ( የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት) የሠራተኛውን ብቃትና ክህሎት በማሻሻል ጥራቱን የጠበቀ ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋይ ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩትን ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ " የሥራ ሥነምግባር" በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው ተቋሙ በቀጣይ የሥራ ጊዜ ሊሠራቸው ያቀዳቸውን ዘርፈ ብዙ የኮንስትራክሽን ልማት ሥራዎችን በከፍተኛ ጥራት፣ ብቃት እና ፍጥነት በማከናወን በዘርፉ ተመራጭ ተቋም ለመሆን ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት እንዲቻል የፈጻሚውን እና አስፈጻሚውን አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መርዕድ ታዬ በስልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሙያን መሠረት ያደረገ ስልጠና የሠራተኛውን አቅም በማጎልበት ለተቋም የአፈጸፀም ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ -አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
20/04/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ -አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
13/04/2023

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Address

Kirkos Sub City
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Defence Construction Design Enterprise - DCDE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share