Addis Ababa Social Trust Fund

Addis Ababa Social Trust Fund Addis Ababa City Administration Social Trust Fund Official Page. Social work

01/11/2024

ለአዲስ አበባ ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናው በፕሮጀክት ዝግጅት፡ ማኔጅመንትና ትግበራ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ይህም ስለፕሮጀክት ምንነት፣ጠቀሜታና አዘገጃጀት እንዲሁም ጊዜን በአግባቡ አብቃቅቶ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የማነቃቂያ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
አንድ ፕሮጀክት ሲቀረጽ ዓላማ ያለው ሲሆን፤በዋናነት አንዲን ችግር ለመቅረፍ በቂ ጊዜና በጀት ተበጅቶለት ጥራት ባለው መልኩ በመከናወን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ነው ሲሉ አሰልጣኙ አስገንዝበዋል፡፡
እንደዚሁም በሥነ-ምግባርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ሥነ-ምግባር በሥነ-ምግባር ቅቡልነት የሌላቸውን ሠራተኞች የሚያስተካክል ልጓም ነው፡፡ ስለሆነም ሥነ-ምግባራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ልንሠራ እንደሚገባ ተገልጧል፡፡
ሥነ ምግባር ለሁሉ ነገር መሠረት በመሆኑ በቅንነትና ሙሉ ሰብዕና በመላበስ በታማኝነት፣ አክባሪነትና አድሎአዊነት በሌለው ሕዝብን ማገልገል እንደሚገባ ከሥልጠናው ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
አሁን እየታዬ ያለው የዕውቀት ችግር ብቻ ሳይሆን በቅንጅት የመሥራት ጉዳይ በመሆኑ በቅንጅት ከተሠራ ተቋማችንን ተወዳጅ፣ ተመራጭና ቀዳሚ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሰብአዊነትን በማስቀደም ኅሊናን ሊያረካ የሚችል አገልግሎት መስጠት ይገባል ተባሏል፡፡
የአዲስ አበባ ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አሥራት ንጉሴ የተሰጡት ሥልጠናዎች ከተቋሙ ተልእኮና ራእይ አንጻር በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ በተለይ ሠራተኛው በነበረው ላይ ዕውቀቱን በሥልጠናው ስለሚያጎለብትና ስለሚያነቃቃ ይበልጥ ለአገልግሎት እንዲተጋ የሚያግዝ ነው በማለት በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ሥልጠናውን ለሰጡት አካላት ምስጋና አቅርበው ይህ ዓይነቱ ሥልጠና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡

በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ውይይት ተካሄደየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ባዘጋጃቸው የሀብት ማሰባሰብ፣ የሀብት ማስተዳደርና የሀብት ማስተላለፍ  ረቂቅ መመ...
24/10/2024

በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ውይይት ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ባዘጋጃቸው የሀብት ማሰባሰብ፣ የሀብት ማስተዳደርና የሀብት ማስተላለፍ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከተለያዩ የተቋሙ ባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዱዋል፡፡
ውይይቱን የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ እንደተናገሩት ውይይቱ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ከተሳታፊዎች የሚገኙ ግብአቶችን በመሰብሰብና በማካተት መመሪያው የተዋጣለትና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያማከለ ለማድረግ ታስቦ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩዋ እንደገለጹት ይህ መመሪያ ጸድቆ ወደስራ ሲገባ ብዙ የአሰራር ችግሮችን በመፍታት ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ እንደሚያስችለው ተናግረዋል፡፡
ረቂቅ መመሪያውን ለተሳታፊዎች ያቀረቡት የሀብት ማስተዳደርና ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አየሁ መኮንን ሲሆኑ ረቂቅ መመሪያውን ለማዳበርና የሚያሰራ እንዲሆን ለማድረግ የሁሉም ተሳታፊ አካል የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የስትራቴጅክስ ፕሮጋራሞች ማኔጅመንት ጽ/ቤት የአንዱ ፕረጀክት ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ሀይሉ በመመሪያ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ቡድን አባላት መመሪያውን ለማዘጋጀት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው በመመሪያው የተለያዩ ክፍሎች ላይ በጣም በጥልቀት በማየት መመሪያው የተዋጣለት እንዲሆን የተለያዩ ሀሳቦችን በመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ የተገለጸ ሲሆን በሚቀጥሉትም ጊዜያት ከተቋሙ ጋር አብረው ለመስራት ደስተኛ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሉዋል፡፡
በመጨረሻም ከተለያዩ ባለድርሻ መስሪያ ቤት የመጡ ተወካይ አካላት የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች የአዲስ አበባ ከተማ አአስተዳደር ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ እና የረቂቅ መመሪያውን ያዘጋጁት የቡድን አባላት ምላሽ በመስጠጥ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋዋል፡፡

21/10/2024
21/10/2024
21/10/2024
21/10/2024

Address

Addis Ababa Mayor Office, Municipal Compound Pizza
Addis Ababa
00000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Social Trust Fund posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Social Trust Fund:

Share