Addis ketema Wereda 13 Communication

Addis ketema Wereda 13 Communication This is Addis Ketema Sub-city wereda 13 Communication Offical page,Come and join us!

በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 13 እና ወረዳ 14 አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላትን ውጤታማነት ለማሳደግ የጋራ የሆነ "የአንድ ማዕከል ስምሪት" ተሰጠ።በአካባቢ ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅና ዘላቂ ሰላ...
03/09/2026

በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 13 እና ወረዳ 14 አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላትን ውጤታማነት ለማሳደግ የጋራ የሆነ "የአንድ ማዕከል ስምሪት" ተሰጠ።

በአካባቢ ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተሰማሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ስራቸውን ይበልጥ በተቀናጀ እና በታቀደ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ የሚያስችል "የአንድ ማዕከል ስምሪት ተሰጠ።

ይህ የስምሪት መድረክ በዋናነት መጪውን አዲስ አመት ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት ለማበረታትና እንዲሁም መረጃዎችን በፍጥነት ለመለዋወጥና ለጸጥታ ስጋቶች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ አቶ አስፍው ተፍሪ ለአካባቢው ሰላም አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ ስራ መሆኑን እና አባላቱም ከህዝቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከረሰ አስተዳደሩም የሰላም ሰራዊት ስምሪቱን ከመቼውም በላይ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

የሰላም ሰራዊት አባላቱ በበኩላቸው የተሰጣቸውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ፣ የአካባቢያቸውን ሰላም በንቃት ለመጠበቅና ማንኛውንም የጸጥታ ችግር ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ነሀሴ 28/12/2018

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥርአዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ  ስራዎች ብቻ ሳይ...
03/09/2026

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥር

አዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ ስራዎች ብቻ ሳይሆን፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ ለማድረግ አጠቃላይ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ማዕከል በሆነው የሰብዓዊ ልማት እና ትውልድን በማነጽ ላይ በሰራችው ስር ነቀል ለውጥ ጭምር ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም”ን በብቃት በመምራታቸው በዓለም አቀፉ “አክት ፎር ኤርሊ ይርስ” (Act For Early Years) ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው ተሸልመዋል። ይህ ትልቅ እውቅና ከተማዋን ለህፃናት የምትመች ከተማ እና ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ መዲና ለማድረግ የሰነቀችውን ራዕይ የሚያንፀባርቅ፣ እንዲሁም ለትውልድ ግንባታ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ያመጣውን ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።

የዚህ ስኬት እና የከተማዋ አስደናቂ እድገት ማሳያ የሆነው ከቁጥር በላይ የሆነው መረጃ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የሕፃናት ማቆያዎች መስፋፋት ነው። 20 የመጫወቻ ስፍራዎች ብቻ የተነሳው የከተማዋ አስተዳደር በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 5 ሺህ 500 ማድረስ ችሏል። በሌላ በኩል 5 ሺህ 3 የሚሆኑት የልጆችን የዕድገት ደረጃና ሥርዓት ታሳቢ ያደረጉ የመጫወቻ ቦታዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም የሕዝብ የሕፃናት ማቆያዎች ከ11 ብቻ ተነስተው በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 100 ደርሰዋል። ይህ በተለያዩ ሞዴሎች የተደራጀው የማቆያ ቁጥር በጥቅሉ 1 ሺህ 155 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሺህ 302 ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ይህ ስኬታማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በመዲናችን የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ሕፃናትን፣ በተለይም 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ታዳጊዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለሙ አምስት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

አዲስ አበባ ዛሬ አለምን ያስገረመችው እና የትኩረት ማዕከል የሆነችው በውብ የኮሪደር ልማቷ፣ በወንዝ ዳርቻዎቿ ውበት፣ ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቿ ብቻ አይደለም። ብሩህ አእምሮ ያለው ጤናማ ትውልድ በማፍራት፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ መሆኗን በተግባር በማሳየትና የዜጎችን በተለይም የሕፃናትን ሕይወት በሚቀይር የሰብዓዊ ልማት ሥራዋ ጭምር ነው። ይህ በሰብዓዊነት እና በትውልድ ላይ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት የመንግስትን የመደመር እሳቤ መሬት ያወረደ፣ ዜጎችን በአንድነት አስተባብሮ ከተማዋን እውነተኛ የብልፅግና ተምሳሌት ያደረጋት ሲሆን፣ ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድትቀዳጅ ያስቻላት ዋነኛ ሚስጥርም ይኸው ነው።

የሰላም ሰራዊት አባላት ከመደበኛ የሰላም ማስከበር ስራ በተጨማሪ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ::****************ነሐሴ 28-2018ዓምበአ...
03/09/2026

የሰላም ሰራዊት አባላት ከመደበኛ የሰላም ማስከበር ስራ በተጨማሪ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ::
****************
ነሐሴ 28-2018ዓም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 1፣ 3 እና በወረዳ 4 ለሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል::

በመርሐግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ጏላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ጏላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች አመራሮች የሰላም ሰራዊት አባላቱን አበረታትተዋል::

በእለቱ ተገኝተው ለፀጥታ አካላት ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሰላም ሰራዊቱ ከመደበኛ የሰላም ስራው በተጨማሪ የተለያዩ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የበኩሉን ሚና በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ገልፀው በቀጣይ የሚከበሩ የአዲስ ዓመት እና ሌሎች በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አካባቢን በንቃት መጠበቅ ይገባል ብለዋል።


የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው በበኩላቸው ሰላም ሰራዊት አባላቱ ከሚመለከታቸው ፀጥታ አካላት ጋር ሆነው የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት በንቃት በመጠበቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ጏላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ከዚህ ቀደም የከተማችንን ሰላምና ፀጥታን አስተማማኝ እንዳደረግነው በቀጣይ የሚከበሩ በዓላትም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ጏላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ሰላም ሰራዊቱ በሚወስደው የተጠናከረ ስምሪት ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ከማስቻሉም በላይ የፀረ ሰላም ሀይሎች እኩይ ዓላማና ፍላጎት እንዳይሳካ እያደረገ ነው ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ
በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በምሽት በፀጥታ ስራ ስምሪት በመውሰድ ለአከባቢው ዘብ እየሆኑ ያለበት አግባብ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ንግድ ጽ/ቤት ያዘጋጀው የበዓል ምርቶች መሸጫ ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተከፈተ።በምልከታዉ...
03/09/2026

መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ንግድ ጽ/ቤት ያዘጋጀው የበዓል ምርቶች መሸጫ ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተከፈተ።

በምልከታዉ በባዛሩ ላይ የቀረቡት የግብርና ምርቶች፣የተለያዩ መሰረታዊ የሸማች ፍጆታዎች የአዲስ ዓመት በዓል መቃረቡን በሚያበስር መልኩ ገበያውን እጅግ ሞቅ እና ደመቅ አድርገውታል።

ባዛሩ መከፈቱ በተለይ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የበዓል ሸመታን ያለ አማካሪዎች እጅ፣ በቀጥታ ከአምራቾችና ከአቅራቢዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።

የወረዳው ንግድ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አበራ ባስተላለፈዉ መልዕክት የሰንበት ገበያዎችንና መሰል የበዓል ባዛሮችን በማስፋፋት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ገልፆ የደመቀው የበዓል ግብይት ተሳታፊ በመሆን የወረዳው ነዋሪዎች በተዘጋጀዉ የባዛር ቦታ በመገኘት ምርቶችን እንዲጎበኙና የፈለጉትን የሸመታ ፍላጎት በቅናሽ ዋጋ እንዲያሟሉ ጽሕፈት ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

ነሐሴ 28/2018
ወረዳ 13 ኮሙኒኬሽን

የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው ባዛር አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር ወሳኝነት እንዳለው ተገለፀ::***********************ነሐሴ 28-2...
03/09/2026

የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው ባዛር አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር ወሳኝነት እንዳለው ተገለፀ::
***********************
ነሐሴ 28-2018ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ አምራችና ሸማቹን ያገናኘ የተለያዩ ምርቶች የቀረቡበት የኤግዚቢሽንና ባዛር በይፋ ተከፍቷል።

በአስኮ ታክሲ ተርሚናል የተከፈተውን ባዛር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና የስራ ሃላፊዎች መርቀው ከፍተውታል::

በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ የግብይት ባዛሩ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በአንድ ቦታና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ይህንን እንደ አርአያ በመወሰድ መሰል ተግባራትን በስፋት ለሸማቹ ህብረተሰብ መዘጋጀት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ ገበያ እንዲፈጠር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው የባዛሩ መከፈት ኅብረተሰቡን ያማከሉ ጥራት ያላቸውንና ትክክለኛ ቅናሽ የተደረገባቸውን ምርቶች ማቅረባቸውንና ጎን ለጎንም ባዛሩ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚረዳቸው ገልፀዋል።

ሸማች ነዋሪዎች በበኩላቸው በአቅራቢያችን የተከፈተው ባዛር በተመጣጣኝ ዋጋ በመቅረቡ ደስተኞች ነን ሲሉ ተናግረዋል::

ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ በክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት፣ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት፣ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት፣ ህብረት ስራ ጽ/ቤት፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለመጪው የአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ ሁሉም አይነት የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸው  ተገለፀ::*******************ነሐሴ 27-2018 ዓ.ም በክፍለ ከ...
02/09/2026

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለመጪው የአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ ሁሉም አይነት የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸው ተገለፀ::
*******************
ነሐሴ 27-2018 ዓ.ም

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም የህብረት ስራ ማህበራት መጭውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ ለሸማቹ ህብረተሰብ እየቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል::

ለበዓል የሚሆኑ የፍጆታ ግብዓቶችን በሸማች ማህበራት እንዲሁም በእሁድ ገበያዎች አማካኝነት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት እየቀረቡ መሆናቸውን እንዲሁም ከምርት አቅርቦት አንፃር ሸማች ማህበራት አማካኝነት መቅረባቸው ተገልጿል::

የአዲስ ዓመት በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የምርት እጥረትና የገበያ ጫና ለመቀነስ የአቅርቦት ሂደቱ በስፋትና በጥራትና የቀረበ ሲሆን በበዓሉ ሰሞን የሚጨምረውን የሸማቾች ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በበቂ መጠን መቅረባቸው ተገልጧል::

በሸማች ማህበራቱ ከቀረቡ ምርቶች መካከል እንቁላል፣ ቂቤ፣ በርበሬ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፓስታ፣ መኮረኒ እና የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው::

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ በመሆናቸው የሚፈልጉትን ምርት እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል::


# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 -

Address

Winget
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis ketema Wereda 13 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis ketema Wereda 13 Communication:

Shortcuts

Share