Disaster Risk Management Commission የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን Ethiopian Disaster Risk Management Commission የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

በኤል-ኒኖ ክስተት ምክንያት ሊከሰቱ በሚችሉ ተፅዕኖዎች ዙሪያ የምክክርና የተግባር ግምገማ መድረክ ተካሄደ(አዲስ አበባ፡ ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም//ኢ.አ.ስ.ሥ.አ.ኮ// አሁን ያለውን የኤል-...
28/08/2026

በኤል-ኒኖ ክስተት ምክንያት ሊከሰቱ በሚችሉ ተፅዕኖዎች ዙሪያ የምክክርና የተግባር ግምገማ መድረክ ተካሄደ

(አዲስ አበባ፡ ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም//ኢ.አ.ስ.ሥ.አ.ኮ// አሁን ያለውን የኤል-ኒኖ ሁኔታ፣ በክስተቱ ሊጎዱ የሚችሉ ተለይተው የታወቁ ክልሎችና ወረዳዎች፣ እየተወሰዱ ያሉ የምላሽ እርምጃዎች እንዲሁም ቀጣይ የአተገባበር አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የግብርና፣ የጤና እና የውሃና ኢኔርጂ ሚኒስቴር የፌዴራል ሴክተር ተቋማት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ቢሮ ተወካዮች አጭር ሪፖርት አቅርበዋል።

ተሳታፊ የፌደራል ተቋማት፣ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮቹ በየአካባቢያቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ፣ በተለይ ለኤል-ኒኖ ተፅዕኖ ተጋላጭ ተብለው የተለዩ ወረዳዎችና አካባቢዎች፣ የተዘጋጁ ዕቅዶች፣ እየተወሰዱ ያሉ የቅድመ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎቻቸውን እንደየክልላቸው ነባራዊ ሁኔታ አቅርበዋል።

በምክክሩም የኤል-ኒኖ ክስተት ሊያስከትላቸው የሚችሉ አደጋዎችን በቅድሚያ በመለየት፣ የተጋላጭነት ደረጃን በመገምገም እና የቅድመ ማስጠንቀቂያን ወደ ተግባራዊ ቅድመ እርምጃ በመቀየር ላይ ያተኮረ የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል።

በዚህም በየደረጃው ያለውን የቅድመ ዝግጅት፣ የምላሽና የክትትል ሥራ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም እስካሁን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንና ቀጣይ የአተገባበር ቼክ ሊስትን በማቅረብ፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤቶች በፌዴራል፣ በክልል እና በታችኛው የአስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስችል ቅንጅታዊ ሥራ አቅጣጫ በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ቀርቧል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ክቡር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራዉ ተክለማርያም የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ክቡር አቶ ደሳለኝ ተሻለ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒንስትር ዴኤታ የውይይት መድረኩን የመሩ ሲሆን በቀጣይ የተለዩ ተጋላጭ አካባቢዎችን በትኩረት መከታተል፣ የሴክተር ተቋማትንና የክልሎችን ቅንጅት ማጠናከር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃን በወቅቱ ለሕብረተሰቡ ማድረስ በተለይም አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የግብርና ሚኒስቴር ፣ የጤና ሚኒስቴር እና ውሃና ኢኔርጂ ሚኒስቴር የፌዴራል ሴክተር ተቋማት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ቢሮ የተዘጋጁ የቅድመ እርምጃ ዕቅዶችን በተጠናከረ አግባብ ተግባራዊ ማድረግ ዋና ዋናዉ ቀጣይ አቅጣጫዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

መድረኩ የኤል-ኒኖ ሁኔታን በተቀናጀ መልኩ በመከታተል፣ ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን ከመከሰታቸው በፊት ለመቀነስ እና የተጋላጭ ማህበረሰቦችን ጥበቃና የመቋቋም አቅም ለማጠናከር ተቋማዊ ቅንጅትንና የተጠያቂነት ሥርዓትን የማጠናከር ጠቃሚ አጋጣሚ ሆኖ ተጠናቋል።

25/08/2026
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችንና የተቋማትን ትስስር እንደሚያጠናክር ተገለጸነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. — ጊንርበኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት፣ በምስራቅ ባሌ ዞን፣ በጊንር ወረዳ በ...
23/08/2026

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችንና የተቋማትን ትስስር እንደሚያጠናክር ተገለጸ

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. — ጊንር

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት፣ በምስራቅ ባሌ ዞን፣ በጊንር ወረዳ በሸወዴ ቀበሌ የተካሄደው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን የዕርስ በርስ ትስስር፣ መረዳዳት፣ አብሮነትና የማህበራዊ ኃላፊነት ባህል በማጠናከር የራስ አቅምንና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት የጎላ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

በመርሃ ግብሩ የኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ አይድሩስ ሃሰን፣ እና የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ጃርሶ ቦሩ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

በፕሮግራሙ ከሀገራዊው የገጠር ኮሪደር ልማትና የገጠር ስማርት ከተሞች ኢኒሼቲቭ ጋር በተቀናጀ መልኩ 20 መኖሪያ ቤቶችና አንድ መዋለ ሕፃናት እንዲገነቡ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። ከእነዚህም አሁን በግንባታ ላይ የሚገኙ 10 ቤቶችና መዋለ ሕፃናት ትምህርት ቤቱ በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ 5 ቤቶች በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና 5 ቤቶች በምስራቅ ባሌ ዞን አስተዳደር እንደሚገነቡ ተገልጿል። በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነ 42 ሺህ ችግኞች የመትከል ሥራ፣ ለ540 ሕፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የደም ልገሳ እና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር የማነቃቂያና የውይይት መድረክ የመርሀግብሩ አካል ናቸው።

በመርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ፣ በጊንር ወረዳ በመርሃ ግብሩ የተከናወኑ ተግባራት 100 ሚሊየን ብር የሚገመት ዋጋ እንዳላቸው ገልጸው፣ እንዲህ ዓይነት ተግባራት የህዝቦችንና የተቋማትን ግንኙነትና ትስስር የሚያጠናክሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በበኩላቸው ክቡር አቶ አይድሩስ ሃሰን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን በመወከል የኮሚሽኑን አመራር ይዘው በስፍራው በመገኘት የወጣቶች ንቅናቄ ኢኒሼቲቭ የወጣቶችን ጉልበት፣ እውቀትና ፈጠራ ወደ ተጨባጭ የማህበረሰብና የልማት ለውጥ ለመቀየር ያለውን ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተዋል። ወጣቶችም በበጎ ፈቃድ፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና በልማት ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሚሽኑ ስራ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በዕቅድ፣ በአፈጻጸም፣ ዙሪያ ያለውን ክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ከአንድ ወርበፊት መጀመሩን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በአዲሱ አመት የቤቶቹ ግንባታ አልቆ አገልግሎት እስኪሰጡ ድረስ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል፡፡

የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ጃርሶ ቦሩ እንደገለጹት እነዚህ አሁን በግንባታ ላይ የሚገኙና መሰረት ያለቀላቸው አስሩ ቤቶች በሀገራዊ የስማርት ሲቲ ኢንሸቲቪ ስታንዳር የሚያሟሉ፤ የመኖሪያ ክፍሎችን የከብት ማደሪያን ጨምሮ አታክልት የሚያለሙት ጎሮ ያካተተ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት የገጠሩን ማህበረሰብ ኑሮ ለመቀየር እያደረገ ያለውን ሂደት የሚበረታታ ነው፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሻግሬ ተሾመ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት (HRS) ፍኖተ ካርታ፤ ዋና ዋና ምሰሶዎችና የትግበራ አቅጣጫዎች ላይ ገለጻ አቅርበዋል። ገለጻውም የሀገር ውስጥ አቅምን በማጎልበት፣ ሀብትን በማሰባሰብና የማህበረሰብና የተቋማትን ተሳትፎ በማጠናከር ከጥገኝነት ወደ ራስ አቅም ለመሸጋገር ያለውን አቅጣጫ አስቀምጧል።

በመርሃ ግብሩ የሁለቱም የፌዴራል ተቋማት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርሶ አደሮችና ወጣቶች በስፋት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም ታሪካዊና የተፈጥሮ ቅርስ የሆነውን የሶፎ ዑመር ዋሻ ጎብኝተዋል።

በአጠቃላይ ይህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር የመንግሥትን የልማት ፖሊሲና ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ከህዝብ ተሳትፎ ጋር በማስተሳሰር የራስ አቅምን፣ የመረዳዳት ባህልን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የዘላቂ ልማት መሠረቶችን ለማጠናከር ጠቃሚ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

#መረዳዳት

የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስተዳደር ለሀገራዊ አይበገሬነት ግንባታ ወሳኝ መሠረት መሆኑ ተገለጸአዳማ | ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም፦ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አ...
16/08/2026

የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስተዳደር ለሀገራዊ አይበገሬነት ግንባታ ወሳኝ መሠረት መሆኑ ተገለጸ

አዳማ | ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም፦ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከUNDRR የአፍሪካ ክልላዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ከነሐሴ 8–10 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየውን የDELTA Resilience ብሔራዊ ካስኬድ ስልጠና አጠናቋል። ስልጠናው በአደጋ ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳትና ውድመት በሥርዓት ለመመዝገብ፣ ለማስተዳደር፣ ለመተንተንና ለውሳኔ አሰጣጥ ለመጠቀም የሚያስችል ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በስልጠናው የአደጋ ጉዳትና ውድመት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ኤርጃቦ፣ በሀገር ደረጃ የተቀናጀ የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃ ሥርዓት መገንባት በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራርንና የውሳኔ አሰጣጥን ለማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ አብራርተዋል። በተጨማሪም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን፣ ሳይንሳዊ እውቀትንና ተዓማኒ መረጃን በማጣመር የአደጋ መረጃን ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና ለውሳኔ አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በስልጠናው ወቅት የኢትዮጵያ የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃ ሥርዓት፣ ብሔራዊ የፖሊሲና ተቋማዊ ማዕቀፍ፣ የመረጃ አስተዳደርና የተቋማት ሚናና ኃላፊነት፣ የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃ አሰባሳብ ደረጃዎች፣ የአደጋ ዓይነት ምደባና የክስተት ኮድ አሰጣጥ፣ የሜታዳታ አስተዳደር እንዲሁም ከቀድሞው DesInventar ሥርዓት ወደ DELTA Resilience የሚደረገው ሽግግር በዝርዝር ተዳሰዋል። ተሳታፊዎች የDELTA Resilience አሠራር፣ ሞጁሎችና ዋና ዋና ተግባራትን በተግባር በመለማመድ የአደጋ ክስተቶችን መመዝገብ፣ ጉዳትና ውድመት መረጃን ማስገባት፣ ማረጋገጥ፣ የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥና ማጽደቅ ላይም ልምምድ አድርገዋል።

በተጨማሪም የተሰበሰበ እና የተረጋገጠ የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃ ለቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ፣ ለአደጋ ዝግጁነትና ምላሽ፣ ለመልሶ ማቋቋም፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ለብሔራዊ የአደጋ ስታቲስቲክስና ለአይበገሬነት ልማት ዕቅድ እንዴት ሊውል እንደሚችል ተመልክቷል። በዚህም የአደጋ ተጽዕኖን በትክክል ለመረዳት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የምላሽ እርምጃዎች ለመለየትና ሀብትን በተገቢው ለመመደብ የሚያስችል የመረጃ መሠረት እንደሚፈጠር ተጠቁሟል።

በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች የDELTA Resilience ሥርዓት በተግባር መለማመዳቸው የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃን በተመሳሳይ ደረጃና በተቀናጀ መልኩ ለመሰብሰብና ለመጠቀም ያላቸውን ግንዛቤ እንዳሳደገ ገልጸዋል። በቀጣይም ተከታታይ የአቅም ግንባታ፣ የተቋማት ቅንጅት፣ የመረጃ መጋራትና የቴክኒክ ድጋፍ በማጠናከር ሥርዓቱ በፌዴራልና በክልል ደረጃ በውጤታማነት እንዲተገበር ያስፈልጋል ብለዋል።

የDELTA Resilience ሥርዓት መጠናከር በተለይም ተቋማዊ ለውጥን ለማፋጠን የሚያግዝ ሲሆን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራርን በግምትና በተበታተነ መረጃ ላይ ከተመሠረተ አሠራር ወደ ሳይንሳዊ፣ በመረጃ የተደገፈ፣ በቴክኖሎጂ የተቀናጀና ተቋማዊ የእውቀት ሥርዓት ለማሸጋገር ወሳኝ አቅም ይፈጥራል። ይህም በኮሚሽኑ የለውጥ አቅጣጫዎችና በሚመለከታቸው የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎች መሠረት ዘመናዊ፣ ብቃት ያለውና በማስረጃ የሚመራ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ሥርዓት ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ሚናው የጎላ ነው።

በቀጣይ ኮሚሽኑ የልማት አጋሮቹ DELTA Resilienceን በሀገር ደረጃ ለማስፋፋትና ተቋማዊ ለማድረግ፣ የመረጃ አመንጪና ተጠቃሚ ተቋማትን አቅም ለማጠናከር፣ የመረጃ ጥራት ለማሻሻል፣ የተቋማትን ቅንጅት ለማጠናከርና ዘላቂ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት በመገንባት ላይ እንደሚያትሩ ተመላክቷል። ይህም ጥረት በሀገር ደረጃ የተቀናጀ፣ ደረጃውን የጠበቀና በማስረጃ የሚመራ የአደጋ ጉዳትና ውድመት መረጃ ሥርዓትን በመገንባት ሀገራዊ የአይበገሬነትና ዘላቂ ልማት ለማጠናከረ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

EDRMC Advances Technology-Enabled Disaster Loss and Damage Data Management through National DELTA Resilience Training|Ad...
16/08/2026

EDRMC Advances Technology-Enabled Disaster Loss and Damage Data Management through National DELTA Resilience Training

|Adama, Ethiopia | 16 August 2026(EDRMC): The Ethiopian Disaster Risk Management Commission in collaboration with the United Nations Office for Disaster Risk Reduction (UNDRR) Regional Office for Africa, has successfully concluded a three-day National Cascade Training on DELTA Resilience, held from 14–16 August 2026 in Adama. The training brought together relevant federal and regional institutions, data custodians, development partners and UN agencies to strengthen Ethiopia’s capacity to systematically generate, manage, analyze and use reliable disaster loss and damage data.

Opening the training, Mr. Melaku Erjabo, Disaster Risk Damage and Loss Lead Executive at EDRMC, emphasized the importance of strengthening a nationally coordinated disaster loss and damage information system to support evidence-based disaster risk management and informed decision-making. He highlighted the need to harness modern technologies and scientific knowledge to improve the availability, quality and use of disaster data across the country.

The training covered a range of key areas, including Ethiopia’s disaster loss and damage data ecosystem; the national policy and institutional framework; data governance and institutional responsibilities; standardized approaches to disaster loss and damage data collection; hazard classification and event coding; metadata management; and the transition from the legacy DesInventar system to DELTA Resilience. Participants also undertook practical sessions on the architecture, modules and functionalities of DELTA Resilience, including disaster-event registration, loss and damage recording, data validation, quality assurance and approval.

The sessions further examined how reliable loss and damage data can be applied to early warning and early action, anticipatory action, disaster preparedness and response, recovery and rehabilitation, climate adaptation, disaster risk reduction, national disaster statistics and resilient development planning. Participants also discussed institutional priorities and future actions for the national rollout and institutionalization of DELTA Resilience.

Participants expressed appreciation for the training, noting that the practical and technology-oriented approach provided a better understanding of the DELTA Resilience platform and its potential to improve the consistency, accessibility and reliability of disaster loss and damage information. They also emphasized the importance of continued capacity development, institutional coordination, data sharing and technical support to ensure the effective application of the system at federal and regional levels.

The training reaffirmed that reliable disaster loss and damage data is a critical foundation for building national resilience. By enabling institutions to better understand the scale, nature and distribution of disaster impacts, the system can support risk-informed planning, prioritization of resources, early action, effective response, recovery and long-term resilience-building efforts.

The successful completion of the training also demonstrates EDRMC’s continued effort to transform disaster risk management through scientific evidence, digital technology, innovation and institutionalized knowledge systems. The Commission is working to strengthen its institutional capacity and establish a modern, technology-supported disaster risk management system in which timely and credible information informs decisions and actions at all levels.

Going forward, EDRMC and its development partners will focus on national rollout and institutionalization of DELTA Resilience, strengthening the capacity of data-producing and data-using institutions, improving data quality and interoperability, enhancing coordination and establishing sustainable mechanisms for disaster loss and damage data management and use. These efforts are expected to contribute to a more coordinated, standardized and evidence-based national disaster loss and damage information system and, ultimately, to a more resilient Ethiopia.

National Cascade Training on DELTA Resilience Underway ******************************************************| EDRMC| 14...
14/08/2026

National Cascade Training on DELTA Resilience Underway
******************************************************

| EDRMC| 14 August 2026 |Adama, Ethiopia | The Ethiopian Disaster Risk Management Commission (EDRMC), in collaboration with the United Nations Office for Disaster Risk Reduction (UNDRR) Regional Office for Africa, has commenced a three-day National Cascade Training on DELTA Resilience in Adama. The training brings together representatives of federal and regional institutions, disaster risk data custodians, academic and research institutions, development partners and UN agencies to strengthen Ethiopia’s national disaster loss and damage data system.

The training is aligned with the Government of Ethiopia’s commitment to strengthening risk-informed disaster risk management, preparedness, early action, response and recovery through reliable and timely disaster risk information. It also supports the mandate of the EDRMC under the national disaster risk management policy and Proclamation No. 1386/2025, which provide for strengthening national disaster risk management systems, coordination, information management and evidence-based decision-making.

The training focuses on strengthening institutional capacity for systematic collection, management, analysis and use of disaster loss and damage data. It also supports the development of a more coordinated and standardized national data system that can generate reliable evidence for understanding disaster impacts and informing risk reduction and resilience-building interventions.

The training is expected to contribute to the establishment of a nationally coordinated, standardized and evidence-based disaster loss and damage data system, thereby strengthening risk-informed decision-making and the country’s capacity to anticipate, prepare for, respond to and recover from disasters, while advancing resilient and sustainable development.


ምርጫችሁ በማድረግ ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን፡፡
The Commission expresses its heartfelt appreciation to all who continue to follow and support its efforts.
በፌስ ቡክ https://web.facebook.com/profile.php?id=100080363110015

ቴሌግራም፡ https://t.me/+JncBcJ9i3EBjYmI8

በቲውተር: https://x.com/EDRMC_info

በቲክቶክ፡

በድረ ገጽ: https://edrmc.gov.et

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCG6KuvTtBptmEJO1i1pEMTg

13/08/2026
የዜጎችን ክብርና ደህንነት ያማከለ የዲፕሎማሲና የትብብር ጥረት ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ተገለጸነሐሴ 06/2018 ዓ.ም፦ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ዜጎችን ክብር፣ ደህንነትና መ...
12/08/2026

የዜጎችን ክብርና ደህንነት ያማከለ የዲፕሎማሲና የትብብር ጥረት ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ተገለጸ

ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም፦ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ዜጎችን ክብር፣ ደህንነትና መሠረታዊ ሰብዓዊ ፍላጎቶች በማማከል የሚሰጠው የሰብዓዊ ድጋፍ በመንግሥት፣ በልማትና በሰብዓዊ ድጋፍ አጋር ተቋማት በሚደረገው የዲፕሎማሲ፣ የትብብርና የቅንጅት ጥረት እየተጠናከረ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም እንደገለጹት፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በሀገር ውስጥ አቅምን በመገንባት ላይ መሆኑን ገልጸው ከልማት አጋር ተቋማት ጋር የሚደረገውን ዘላቂ ትብብር በማጠናከር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብንም ይጠይቃል።

ኮሚሽነሩ አክለውም፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ ዜጎችን በክብርና በደህንነት መቀበልና መደገፍ የመንግሥትን ዜጋ ተኮር አስተዳደር አቅጣጫ የሚያሳይ ተግባራዊ ሥራ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንንም ለማሳካት ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ተቋማት፣ ከኪንግ ሳልማን የሰብዓዊ ድጋፍና የዕርዳታ ማዕከል (KSrelief) ጋር የተጀመረው ትብብር ወደ ዘላቂ የልማትና የሰብዓዊ ድጋፍ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የተመላሽ ዜጎችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ፍላጎት ለመሸፈን፣ የመመለሻ ሂደቱን የተቀናጀ ለማድረግ እና የሰብዓዊ ድጋፍ አቅሙን በተቋማዊ መሠረት ለማጠናከር በትኩረት እየሠራ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህ የትብብር ማዕቀፍ የኪንግ ሳልማን የሰብዓዊ ድጋፍና የዕርዳታ ማዕከል ለተመላሽ ዜጎች የሚውል 1.333 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ድጋፉ በኮሚሽኑ በአደጋ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ሥር እየተተገበረ ይገኛል። ይህም ተመላሾች ወደ ቤተሰቦቻቸውና መኖሪያ አካባቢያቸው በክብርና በደህንነት እንዲደርሱ ለመጓጓዣ፣ ለምግብ፣ ለመጠለያ፣ ለአልባሳት እና ለሌሎች መሠረታዊ የአስቸኳይ ፍላጎቶች ድጋፍ እየዋለ ነው።

የድጋፉ አካል የሆነው ለተመላሽ ዜጎች የመጓጓዣ አገልግሎት የሚውሉ ሦስት አዳዲስ ተሸከርካሪዎች የተሰጡ ሲሆን፣ ይህም የተመላሾችን ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው የመጓጓዣ ፍላጎት በተሻለ አቅም በማሟላት የመመለሻ ሂደቱን ይበልጥ የተቀናጀ ለማድረግ ያግዛል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተጀመረውን ትብብር ወደ ቀጣይ የልማትና የሰብዓዊ ድጋፍ አጋርነት ለማስፋት፣ ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከርና የዜጎችን ሰብዓዊ ፍላጎት በዘላቂነት ለመደገፍ የቀጣይ ትብብር ስምምነት በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና KSrelief መካከል ተፈራርሟል።

የስምምነቱ መፈረም በተመላሽ ዜጎች ድጋፍ ላይ የተጀመረውን ትብብር ከአስቸኳይ ሰብዓዊ ምላሽ ባሻገር ወደ ቀጣይና ዘላቂ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ትብብር ለማሸጋገር ያለውን የሁለቱን ተቋማት ቁርጠኝነት ያሳያል።

በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያና የሳዑዲ ዓረቢያ ተቋማት እንዲሁም የልማትና የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮች በቅንጅት የሚያከናውኑት ሥራ የዜጎችን ክብርና ደህንነት ያማከለ የዲፕሎማሲ፣ የትብብርና የአጋርነት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ያሳያል።

አመራሮችና ሠራተኞች ደም ለገሱየኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መ/ቤትና የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ደም ለገሱ።የኢትዮጵያ ደም...
11/08/2026

አመራሮችና ሠራተኞች ደም ለገሱ

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መ/ቤትና የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ደም ለገሱ።

የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ ባንክ ባለሙያዎች በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት የደም ልገሳ አገልግሎቱን ያከናወኑ ሲሆን፣ ከኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ደም መሰብሰቡን የኮሚሽኑ የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሐራጓ ማሞ ገልጸዋል።

ከአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመምጣት ደም የለገሰችው ወጣት ብዙአየሁ አበራ በበኩሏ፣ “የሀገሬን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገሴ ደስተኛ ነኝ” በማለት ስለ ደም ልገሳ ያላትን አመለካከት ገልጻለች።

የደም ልገሳው ተግባር የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ለማኅበረሰቡ የሚያደርጉትን ማኅበራዊ ኃላፊነት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ተሳትፎ ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

Address

EDRMC/Nifas Silk Near To Gotera Complex Road On The Debre Zeyt Road, Before Mulege Bld
Addis Ababa
251

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Disaster Risk Management Commission የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Disaster Risk Management Commission የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን:

Shortcuts

Share