Road Safety & Insurance Fund Service

Road Safety & Insurance Fund Service This is the official page of Road Safety & Insurance Fund Service

28/10/2025
28/10/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተፈጥሮ ጋዝ ለከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንዲዉል መድረጉ

 ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ ለመቀንስ እንዲሁም

 የማዳበሪያ ዋጋ በቀነሰ ዋጋ አርሶ አደሩ ጋር እንዲደርስ ስለሚያደርግ ምርት እና ምርታማነት እንዲጨምር እና

 የተፈጥሮ ጋዝ ለተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንድውል ሲደረግ ትራንስፖርት ዋጋ ስለሚቀንስ የኑሮ ውድነት ለመቀነስ ያስችለናል ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇

በድረ ገጽ፡

www.motl.gov.et

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL

በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia

በዩቲዩብ

https://youtube.com/

በትዊተር

https://x.com/MoTLogesti

ለአሽከርካሪዎች  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለፁ..  ... ...የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃ...
27/10/2025

ለአሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለፁ.. ... ...
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ቀረቦ ተገምግሟል።
በዚህም የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አፈፃፀም በተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ በአቶ ጀማል አባሶ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በመጨረሻም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ሰሜ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንዲወስዱ በማድረግ እና አሽከርካሪዎችን ማዕከል ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

መረጃው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው

27/10/2025
ለትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ... ....ጥቅምት 12 / 2018 ዓ.ም / መ.ደ.መ.ፈ.አ /የመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት ለትራፊክ ፖሊሶች ፣ ለአደጋ ...
22/10/2025

ለትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ... ....
ጥቅምት 12 / 2018 ዓ.ም / መ.ደ.መ.ፈ.አ /
የመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት ለትራፊክ ፖሊሶች ፣ ለአደጋ መርማሪዎች እና ለመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረወ ሀገር አቀፍ ስልጠና ተጠናቀቀ ።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የተቋሙ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ ለሰልጣኞት የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ተቋማቸው የግንዛቤና የህግ ማስከበር ሰራዎችን በሰፊው እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል። ከዚህም ጋር በተያያዝ ሰው ሰራሽ በሆኑ ችግሮች የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ግንዛቤ በማስጨበጥ ህግን በማስከበር የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ አንስተዋል።

አክለውም የተሰጠውን ስልጠና በሙሉ አቅም በመጠቀም የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሀገር ደረጀ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በመጨረሻ ስልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው የተሻለ ስራ እንደሚሰሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተናግዋል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሚስጡትን አገልግሎት ለማሻሻል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ.. .... ... ጥቅምት 12 /2018 ዓ.ም /መደመፈአ/የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር አጠቃላይ አሰራርን እና  የ...
22/10/2025

የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሚስጡትን አገልግሎት ለማሻሻል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ.. .... ...
ጥቅምት 12 /2018 ዓ.ም /መደመፈአ/
የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር አጠቃላይ አሰራርን እና
የትራፊክ ደንብ በማስከበር የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የትራፊክ ህግ አስከባሪዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ስልጠና ተሰጠ ።
አምስቱ የመንገድ ደህንነት ምሶሶዎች የሚባሉትን ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፍጥነት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ተሽከርካሪ እና የመንገድ ተጠቃሚዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰራት የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የወጡ ደንቦችን ተፈጻሚ እንዲሆኑ መሰራት እንደሚገባ በስልጠናው ተነስቷል።
ከዋና ዋና የትራፊክ ደንብ መተላለፉ አይነቶች ውስጥ ከተፈቀደው ፍጥነት ወሰን በላይ ፣ መጠጥ ጠጥቶ ፣ ሀሺሽ ተጠቅም ፣ የደህንነት ቀበት ሳያደርጉ ማሽከርከር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።
ስልጠናው ለፌድራል፣ ለክልል፣ ለአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ትራፊክ ፖሊስ አባላት ፣ ትራፊክ አደጋ መርማሪዎች እና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች ለአደጋ አጋላጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፁ.. ... ... ጥቅምት  12/2018 ዓ.ም ቢሾፍቱየትራፊክ ቁጥጥር ነገራዊ ሁኔታና በትራፊክ...
22/10/2025

የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች ለአደጋ አጋላጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፁ.. ... ...
ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ቢሾፍቱ
የትራፊክ ቁጥጥር ነገራዊ ሁኔታና በትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 አፈፃፀም እና በተገኘ ውጤቶች ላይ ጥናትዊ የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ተጀምሯል ።

በመርሀ -ግብሩ የፌድራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ፖሊስ አባላት፣ ትራፊክ አደጋ መርማሪዎች እና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የትራፊክ አደጋ  መቀነሻ መፍትሄዎች ላይ ስልጠና ተሰጠ።... -- .... ጥቅምት 11/ 2018  ዓ.ም የተሸከርካራ ፍጥነትን ለመግታት የሚወሰዱ መፍትሄዎች በመተግበር አደጋን ለመቀነስ በሚያ...
21/10/2025

የትራፊክ አደጋ መቀነሻ መፍትሄዎች ላይ ስልጠና ተሰጠ።... -- ....
ጥቅምት 11/ 2018 ዓ.ም
የተሸከርካራ ፍጥነትን ለመግታት የሚወሰዱ መፍትሄዎች በመተግበር አደጋን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ፣ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምርመራና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተደጋጋሚ አደጋ የሚደርሰባቸው ቦታዎች ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገር አቀፍ ስልጠና ለባለመያዎች ተሰጠ ።

ፎቶ ዜና የመንገድ ትራፊክ አደጋ ምርመራና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተደጋጋሚ አደጋ የሚደርሰባቸው  ቦታዎች ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገ...
21/10/2025

ፎቶ ዜና
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ምርመራና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተደጋጋሚ አደጋ የሚደርሰባቸው ቦታዎች ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገር አቀፍ የስልጠና መድረክ ላይ ውይይት ሲደረግ ።

የመንገድ ትራፊክ  ደህንነት ጉዳዮች የሀገር አጀንዳ ሊሆነ እንደሚገባ  ተገለፁ.. ... ...ጥቅምት 11 / 2018 ዓ.ምየመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ለፌድራል ፖሊስ፣ ለሁለቱ...
21/10/2025

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ጉዳዮች የሀገር አጀንዳ ሊሆነ እንደሚገባ ተገለፁ.. ... ...
ጥቅምት 11 / 2018 ዓ.ም
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ለፌድራል ፖሊስ፣ ለሁለቱ ከተማ መስተዳድር ፣ ለክልል ትራፊክ ፖሊስ አባላት ፣
ለትራፊክ አደጋ መርማሪዎችና ለመንገድ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።

በስልጠና መድረኩ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጀማል አባሶ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። አሳቸውም እንደገለጹት የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ለመቀነስ በተግባር አውቆ የሚያሳውቅ ባለሙያን በማፍራት ራስን በመጠበቅ ህዝብ እንዳይዘናጋ ለማድግ በጥናት ተለይቶ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ስልጠናው የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ኃላፈነታቸሁን እንድትወጡ ለማስቻል የአሰልጣኞች ስልጠና ተዘጋግቷል ብለዋል።

19/10/2025
በመንገድ ደህንነት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ ፤ጥቅምት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋየመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የድሬዳ...
18/10/2025

በመንገድ ደህንነት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ ፤

ጥቅምት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የድሬዳዋ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ።

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ መስብሰቢያ አሰራር ስርዓትን በሲስተም ለማድረግ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ስራውን በድሬዳዋ ማስጀመር ተችሏል፡፡

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ስራ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መሰረት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም ቁልፉ እና የማህበረስብ አቀፉ ስራ መሆኑን ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡ ፡

Address

Addis Ababa
P.O.BOX1288

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Road Safety & Insurance Fund Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Road Safety & Insurance Fund Service:

Share