Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau

Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau This is the Official page of
Addis Ababa City Innovation and Technology Development Bureau!

15/08/2026
15/08/2026
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች የእንጦጦ-ቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ*************************** ITDB፦ ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም የአዲስ ...
14/08/2026

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች የእንጦጦ-ቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ
***************************

ITDB፦ ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ አስጎብኚነት የእንጦጦ-ቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ።

የጉብኝቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ከተማዋን ዉብና ማራኪ ከሚያደርጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የእንጦጦ-ቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን ገልፀዉ ቢሮዉ የይቻላልን መንፈስን በተቋሙ ሰራተኞች ላይ የማስረፅ ፅንሰ ሀሳብን በማንገብ ይህንን የጉብኝት መርሃ ግብሩን እንዳዘጋጀ በማመላከት መልካም የጉብኝ ግዜን ተመኝተዋል።

የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ቀደም ሲል ለብክለት፣ ለቆሻሻ መጣያነትና ለደህንነት ስጋት የነበረው የ10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት የወንዝ መስመር ወደ ውብ የስነ-ምህዳር መናፈሻነት የተቀየረ መሆኑንና 87.6 ሄክታር መሬትን አረንጓዴ በማልበስ እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ውብ ዛፎችን በመትከል የከተማዋን የስነ-ምህዳር ሚዛን መመለስ የቻለ ፕሮጀክት እንደሆነ ገልፀዋል።

አያይዘውም ትላንት ይሸትና ያስፈራ የነበረውን ስፍራ ዛሬ መልካም ጠረን የያዘና ነዋሪውም የሚኮራበት ውብ ስፍራ በማድረግ፣ የኢትዮጵያን አዲስ የከፍታ ጉዞ በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን በማመላከት የጉብኝት መርሃ-ግብሩን ላይ ዝርዝር ማብራርያ በመስጠት በበላይነት መርተዋል።

በጉብኝቱ መጨረሻም የቢሮ ሀላፊ የጉብኝት መርሃ ግብሩ መልካም እንደነበርና ቀበና የአዲስ አበባ ሌላኛው ዉብ ገፅታን የተቋሙ ሰራተኛዉ በተነቃቃ መንፈስ በጋራ በመጎብኘቱ የተሰማቸዉን ደስታ ገልፀዉ ይህንን መሰል ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): [email protected]
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

ዘመኑን የዋጀ ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ሲስተም ዝርጋታ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ************************ ITDB፦ ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም የአዲስ አ...
13/08/2026

ዘመኑን የዋጀ ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ሲስተም ዝርጋታ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ
************************

ITDB፦ ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በጋራ በመሆን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዘመኑን የዋጀ ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጠት የሚያስችል Next generation emergency response solution system ዝርጋታ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ።

የዉይይት መርሃ-ግብር ዓላማ ቀደም ሲል የነበረውን የመፍትሔ ሀሳብ ሊተካ የሚችል አዲስ የመፍትሔ ሀሳብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ። የቢሮ አመራሮችና የፕሮጀክቱ ቴክኒክ ኮሚቴዎች፣ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙበት ሲሆን በቀጣይ መከናወን ስላለባቸዉ ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ የዉይይት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።


ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): [email protected]
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

12/08/2026
12/08/2026

Address

Addis Ababa

Telephone

+251949343865

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share