እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እናት ፓርቲ, Political Party, Addis Ababa.

🔴እናት ፓርቲ ድምጽ ለተነፈጋቸው መላ ኢትዮጵያውያን ያለአድሎ ድምጽ በመኾን አገዛዙ ከእኩይ ድርጊቱ እንዲታቀብ፣ ፍትሕና እድገት በምልዓት እንዲሰፍን ያለመታከት ይሠራል። ዜጎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከተጋረጠባቸው የሕልውና አደጋ ለማዳን አበክሮ ይሠራል፤
🔴እናት ፓርቲ ፈጣሪን መፍራት መርኁ አድርጎ ውሕድ ወግ ጠባቂ ማኅበራዊ ዴሞክራሲን ያራምዳል!
👉🏾ይቀላቀሉን!

በመርሕና በስክነት የተካሄደ ምክክር ሳይኾን የእነ አጼ በጉልበቱ ትዕይንት በመኾኑ ሕዝብ እንዳይቀበለው!(በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ከእናት ፓርቲ በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ) እናት ፓርቲ ከመነሻው ...
22/08/2026

በመርሕና በስክነት የተካሄደ ምክክር ሳይኾን የእነ አጼ በጉልበቱ ትዕይንት በመኾኑ ሕዝብ እንዳይቀበለው!
(በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ከእናት ፓርቲ በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ)

እናት ፓርቲ ከመነሻው የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ግልጽነት የጎደለውና በአገዛዙ የተጠለፈ መሆኑን ተረድቶ፣ የተዛነፈው አካሄድ መሥመር እንዲይዝ ለሀገር ይበጃል ያላቸውን አቅጣጫዎች ሲጠቁም መቆየቱ ይታወቃል። በቅርቡም ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣነው መግለጫ መስመሩን የሳተ ሂደት እንደሆነ ጠቅሰን ሕዝቡም በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ ሆኖም የፓርቲያችንና የሌሎች መሰል ተቋማት ምክንያታዊ የእርምት አስተያየቶችን በበጎ ከመቀበል ይልቅ ጆሮ ዳባ ልበስ በመባሉ የምክክር ጉባዔው የእነ አጼ በጉልበቱ መፈንጫ ሆኖ አልፏል፡፡ አልፎ ተርፎም እንኳንስ ለአገር አዲስ መፍትሔ ሊያዋልድ ይቅርና ላለው ሀገራዊ ቀውስ ጭራሽ ቤንዚን የሚያርከፍከፍ የዜሮ ድምር ውጤት ሆኗል፡፡

ገና በእንቁላሉ ይስተካከል ስንል የከረምነው መዋቅራዊ ስህተት፤ ኮሚሽኑ ራሱ ላስቀመጠው መርሕ እንኳን ያለመገዛት፤ አብዛኛውን ተሳታፊ የወከለው ራሱ ገዢው ፓርቲ መሆን፤ አብዛኛውን ሰዓት ለበሳል ምክክርና ክርክር ሳይሆን በእረፍትና በዋዛ ፈዛዛ በማሳለፍ ጠንካራ ጉዳዮች ትኩረት መነፈግ፤ ሀገርን ሰቅዘው የያዙ ጉዳዮችና ችግሮችን ማለባበስ፤ ቀድመው በጓዳ በር የተወሰኑ ውሳኔዎችን ለማጸደቅ ሽኩቻና ሀሳቦችን ለይስሙላ ማንሳት፤ አሰልጣኝ ተብዬዎች ፕሬዝዳንቱን በሕዝብ ከመምረጥ ይልቅ እንደ ደቡብ አፍሪካ ከፓርላማ መምረጥ የምትለዋንና መሰል የጓዳ ውሳኔዎችን ብቻ እንዲያጸኑ የመጡ ሰባኪያን ሆነው መገኘት፤ የእጅ አሰጣጡ ለተወሰኑ ሰዎችና ለሚፈልጓቸው ብቻ መሆኑ፤ ድምጽ ባልተሰጠበት ሁኔታ “አብዛኛው/ሁሉም ተመካካሪ የተስማማበት” እየተባሉ ምክረ ሀሳቦች መቀመጥ፤ አጀንዳው በሚፈለገዉ መንገድ ያልሄደ ከመሰላቸው ደግሞ ምክክሮች ካለቁ በኋላ ያለቀን ጉዳይ መልሶ መላልሶ የማቅረብ፤ ከተመካካሪዎች የሚሰጡ ምክረ ሀሳቦች በድምጽ አሰጣጥ ሂደት እንደሚያልፉ ከተመካካሪዎች ስምምነት ውጭ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩን ወደ ስምምነት የሚያመጣ የክልል ም/ቤት የተቋቋመ ቢሆንም ይህ ነው የሚባል ሥራ ያልሠራና የይስሙላ መሆኑ፡፡ ይህንና ለመዘርዘር የሚያዳግቱ መሰል ሂደታዊና መዋቅራዊ ግድፈቶች የነበሩበት ነበር፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች አንኳርና ለማሳያ የተጠቀሱ እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በተለይ ሌሎች ጉዳዮችን እንዲሸፍን ሆነ ተብሎ በሚመስል አኳኋን ሲራገብ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይ አብዛኛው ተመካካሪ ተስማምቶ ያስቀመጠው ሀሳብ “አዲስ አበባ ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ ትሆናለች” የሚል ቢሆንም ብልጽግና በሚፈለገዉ መንገድ የተወሰነ ባለመሆኑ ያዳራጃቸው ቡድኖች አዳራሽ ረግጦ መውጣት፣ አዳራሽ መረበሽ፣ የተቋጨን አጀንዳ እንደገና ማንሳት፣ ማስፈራራት፣ ውስጥም ከአዳራሽ ውጭም ድባቡ እንዲያስፈራ ማዋከብና “የክልል ም/ቤት” የሚባለው ከተረሳና ጊዜዉ ካለፈ በኋላ እንደገና ተሰብሰቦ ጉዳዩን እንዲያይና ያልተመከረበትን ወይም በአብዛኛው/አብላጫው ውድቅ ያደረገውን ሀሳብ ቅቡልነት እንዳለው ተደርጎ መቅረቡ ኮሚሽኑ ወጥ መርኅ የሌለውና የገዢው መንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ መሆኑን በገሃድ ያሳየ ጉዳይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ጉዳይ ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በ50፣ 250፣ 500 ቡድኖች ጸድቆና ስምምነት ተደርጎ ለ4000 ቡድኖች ቀደም ብሎ ቀርቦ ምክክሩም ከሞላጎደል የተጠናቀቀ ሲሆን የተፈለገውና የእነ አጼ በጉልበቱ ፍላጎትና የጓዳ ውሳኔ ያ ባለመሆኑ ምክክሩ አንዴ ጠዋት ተቀጥሮ ምሽት ሲገናኝና በአብዛኛውም እንዲሁ በመጉላላት ሲበተን እስከ አርብ እንዲራዘም ተደርጎ ምን አልባትም ተመካካሪው በተሳለቸበት፣ ሙሉ ቀን ሲታሽ ውሎ ባለቀ ሰዓት ጊዜ በማሳጠር፣ በጨለማና ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ፣ ከተመካካሪዎች ስምምነት ውጭ አስጨብጭቦ ለማሳለፍ በታሰበ አኳኋን ሲራዘም ቆይቷል፡፡ እውነታውን ግን አይቀይረውም፤ ሕዝብም እንዲህ ካለው የእቃ እቃ ጨዋታ የሚወጣ ሕግን ፈጽሞ ሊቀበል አይችልም! አዲስ አበባ በታሪክም በመርሕም የነዋሪዎቿ ብሎም የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የአንድ ሁሉን የእኔ ባይ ቡድን ፍላጎት ማስፈጸሚያ አልነበረችም፣ አይደለችም፣ አትሆንምም! ይህ የታሪክም የፖለቲካም ቀይ መስመር እንደሆነ ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከዚህ እውነት ያፈነገጠ ሀሳብ ቢሰነዘር የሕልውና ጥቃትና ሀገር የማፍረስ ማስጀመሪያ ፊሽካ አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡

የምክክሩ አጠቃላይ ሂደትና የተቋጨበትን መንገድ ስንመለከት ኮሚሽኑ ከመነሻው ባዘጋጀውና ለተሳታፊዎች ባስተዋወቀው የምክክር ሂደት የሥራ መመሪያ ተ.ቁ 3 ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት 3.2 በርዕሰ ጉዳይ ላይ ተመካካሪ ቡድን ደረጃ የውሳኔ ስምምነት (Consensus) አለ ለማለት የተሳታፊዎቹን 75% ድጋፍ ማግኘት ሲችል ነው ብሎ በግልጽ ያስቀመጠና ይህንኑ ለተሳታፊዎች የገለጸ ቢሆንም የአሠራር ለውጥ ማድረጉ ለጉባዔ ተሳታፊዎች ባላሳወቀበት ኹኔታ በአንድም ጉዳይ ላይ ድምጽ ተሰጥቶ በ Consensus ሆነ ያ ሊደረስ ካልቻለ በማለት ባስቀመጠው qualified ባለው አካሄድ ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ባለመኖሩ ኮሚሽኑ ራሱ የዘረጋውን ሥርዓት በመናድ አተገባበሩ በሆይ ሆይ (በዝርፊያ በተሠማሩ ሰዎች ቋንቋ ሿሿ) እንዲሆን ተደርጎ የታለፈ በመሆኑ ተደረሰባቸው የተባሉ ስምምነትቶች በሙሉ ከዚህ አኳያ ሕጋዊነት እንደማይኖራቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ፓርቲያችን ይገደዳል።

በፓርቲያችን እምነት ምክክሩ ሌሎች ሀገሮች ሲደረግ እንዳየነውና እንደሰማነው በመርሕም እንደምናውቀው ቁልፍና አንገብጋቢ ሀገራዊ ችግሮችን መፍቻ ስልት ተደርጎ የተካሄደ አይደለም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ እኛ ያደረግነው ምክክር እንኳን እንዲህ ዙሪያ መለስ ቀውስ ውስጥ ላለ ሀገር አይደለም ለቅንጦት እንኳ እንዲደረግ የሚመከር አይደለም፤በአጠቃላይ ምክክሩ ውስብስብ ችግሮችን እያለባበሰ፣ ቀላል ችግሮችን ደግሞ ማወሳሰቢያ መድረክ ሆኖ አልፏል ቢባል ማጋነን አይሆንም!

በመሆኑም፤
1. በታሪክ ፊት ምክክሩ ተጨባጭና አዎንታዊ ውጤት እንዳያስገኝና ባለው ቀውስ ላይ ተጨማሪ ቀውስ እንዲወለድ በር የከፈተው ጠበብ ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና ሰፋ ሲል ገዢው ብልጽግና ነው፡፡

2. መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክሩ ሂደት የተቃኘበትን አደገኛ መንገድ ተገንዝቦ ከዚህ የተዛባና አቅጣጫውን ከሳተ የይምሰል ምክክር የሚወጡ አሳሳች ውሳኔዎችና ሰነዶችን እንዳይቀበልና በአመቸው መንገድ ሁሉ እንዲቃወም ጥሪ እናደርጋለን፡፡

3. እናት ፓርቲ ምክከሩ ከጅምሩ ጀምሮ የጎላ ችግሮች እንደነበሩበት ለኮሚሽኑና ለሕዝብ ያሳወቀ በመሆኑ አሁንም ውጤቱን ለማስቀየር እነአጼ በጉልበቱ የሚዘውሩት ድራማ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ እውቅና የማይሰጠው መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

20/08/2026

https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-992N5d65uT3
👆🏾👆🏾👆🏾
እናስታውስዎ!
ዛሬ ሐሙስ ምሽት 4:00 በ tiktok live የትብብሩ አመራሮች ገብተው ገለጻና ማብራሪያ ይሰጣሉ። ይግቡ ይሳተፉ፤ ሌሎችን ያጋሩ!

 !   ግድያ_ይብቃ! የትብብራችን አመራሮችና ልኂቃን ገለጻ ያደርጋሉ!ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 ምሽት 4:00 በ  #ቲክቶክ ቀጥታ ሥርጭት። ይከታተሉ፣ ይሳተፉ!
19/08/2026

!
ግድያ_ይብቃ!

የትብብራችን አመራሮችና ልኂቃን ገለጻ ያደርጋሉ!

ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 ምሽት 4:00 በ #ቲክቶክ ቀጥታ ሥርጭት። ይከታተሉ፣ ይሳተፉ!

 #ሰላም!
19/08/2026

#ሰላም!

 !
18/08/2026

!

Abeshige extrajudicial killings ‘comparable to the Red Terror’, demands investigation!August 15, 2026 Temesgen Getachew,...
17/08/2026

Abeshige extrajudicial killings ‘comparable to the Red Terror’, demands investigation!
August 15, 2026

Temesgen Getachew, Yitagesu Asegidew and Gizaw Girmaye, pictured next to a public transport vehicle. World news updates

The Coalition for Ethiopian Unity, a five-party oppositionpoliticalcoalition, has condemned the reported killing of three young men in Abeshige Woreda of Central Ethiopia Regional State, saying the killings were “comparable to the Red Terror” and demanding an independent investigation.

The coalition said on Saturday the three men, Temesgen Getachew, Yitagesu Asegidew and Gizaw Girmaye, were targeted on 30 July in Nacha Kulit Kebele after allegedly being accused of being “Fano.” Photographs purportedly showing the men tied up, beaten, and shot dead were published and widely circulated on social media. News subscription service.

The men were forcibly removed from a public transport minibus and killed in what the Coalition described as an “extremely inhumane manner – exceeding even what history recalls of the Red Terror era,” an era in late 1970s during which Ethiopia’s military junta, the Derg, conducted mass extrajudicial killings of civilians.

Citing local sources, the coalition said the brother of Yitagesu Asegidew, one of the victims, was “previously seized from Hawassa and executed in a similar manner”, which it said indicates that the killings may be targeting families and identity. It also cited the case of Gizachew Girma, another young man who was allegedly arbitrarily executed about a month ago in Darge Kebele, within the same Abeshige Woreda. It described Girma as a respected young entrepreneur who had created job opportunities for many youths in the community.

The Coalition’s denouncement follows reports early this week that the three men were forcibly removed from public transport in the Agena area of Abeshige and subsequently killed. Photographs purportedly showing the men tied, beaten and shot were also circulated. Local reporting cited eyewitnesses who attributed the killings to government forces working with local police and militia. Ethiopian culture magazine. The Central Ethiopia Regional State Peace and Security Bureau has not explicitly acknowledged the reported killings or confirmed that government forces were responsible.

At a regional government press briefing on 12 August, Bureau Chief Temesgen Kassa said security forces had taken “action” against armed individuals in parts of Abeshge who had rejected government calls to surrender. He described the targeted individuals as “bandits” and alleged they were involved in killings, robbery and extortion. Political commentary blog “Those who refused were apprehended and brought to justice,” Temesgen said, without providing details of arrests, charges, court proceedings or judicial outcomes.

The bureau has also said security forces were conducting coordinated operations with the federal government and the Oromia Regional State against what it described as “banditry” in parts of Gurage Zone. Temesgen rejected claims that the operations were directed at particular ethnic communities, calling such reports “far from the truth.” The coalition, however, said suspected criminal activity could not justify killings outside the legal system.

“Even if a person is suspected of involvement in a crime, they should face public trial through legal channels rather than being unlawfully tied up and shot dead,” it said, describing the reported killings as evidence of “systemic human rights violations, mob justice, and cruelty.”

The coalition also cited the killing of another young man, Gizachew Girma, in Darge Kebele of Abeshige about a month earlier. It described Gizachew as a young entrepreneur who had created employment opportunities and was respected in the community.

The group said the reported violence was particularly alarming in an area known for “peaceful coexistence, love, and mutual respect,” and accused local officials and security forces of making statements that could facilitate impunity.

The coalition called for “an immediate, independent, transparent, and credible investigation” into the killings and demanded that both those who carried them out and those who allegedly ordered them be held accountable.

It also called on Ethiopians to participate in a one-day social media campaign on 18 August under the slogan “Stop Massacre of Civilians”, saying the campaign should draw international attention to what it described as arbitrary killings across the country. Regional authorities in Central Ethiopia have acknowledged recent “security problems” in Abeshige that resulted in “loss of life and property damage”, and attributed the insecurity to armed groups operating in “forested areas.” The coalition rejected extrajudicial punishment and urged authorities to ensure that allegations of criminal conduct are addressed through due process.

Source and credit:- Addis Standard;
https://addisstandard.com/coalition-says-abeshige-extrajudicial-killings-comparable-to-the-red-terror-demands-investigation/?fbclid=IwdGRjcATtPGtjbGNrBO2Os3Bkb2YBZXh0bgNhZW0CMTEAc3J0YwZhcHBfaWQMMzUwNjg1NTMxNzI4AAEeb9cdBA9dlge_aG5eewLl43r_0qE5WxAExFFokKBCGnxqT3LhaRfmouVa-1o_aem_uBgkluXE26h3NIe3cj914w

በአበሽጌ የተፈጸመው ግድያ ቀይሽብርን የሚስተካከል ነው!(መሰል ግፍን በቃ ለማለትና እንዳይደገም ለአንድ ቀን እናስባቸው)በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫሐምሌ...
15/08/2026

በአበሽጌ የተፈጸመው ግድያ ቀይሽብርን የሚስተካከል ነው!
(መሰል ግፍን በቃ ለማለትና እንዳይደገም ለአንድ ቀን እናስባቸው)

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ፣ ናቻ ቁሊት ቀበሌ ሦስት ወጣቶች በማንነታቸው ተመርጠውና ከሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ላይ እንዲወርዱ ተደርገው "ፋኖ ናችሁ" በሚል ሰበብ ታሪክ እንደሚያወሳን በቀይ ሽብር ዘመን ሲደረግ ከነበረውም በላይ እጅግ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ግድያ መፈጸሙን አረጋግጠናል። ከአካባቢው ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት የጭካኔውን ወደር የለሽነት የሚያረጋግጠው ዘግናኙን ድርጊት ፈጻሚው የፀጥታ አካል ከገደላቸውም በኋላ አስከሬናቸውን የቀብር አፈር እንዳይቀምስ በመከልከሉ በአውሬ እንዲበላ መደረጉንም ሰምተናል። ከግፍ ሰለባዎቹ አንዱ የሆነው ይታገሱ አሰግደው ከዚህ ቀደም ወንድሙ ከሐዋሳ ተይዞ በተመሳሳይ እንዲረሸን ተደርጓል። ይህም ግድያው ቤተሰብንና ማንነትን ማዕከል ያደረገ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ይላሉ የአካባቢው ምንጮች። በተመሳሳይ ከወር በፊት ግዛቸው ግርማ የተባለ ሌላ ወጣት በዚያው በአበሽጌ ወረዳ፣ ዳርጌ ቀበሌ በዘፈቀዳዊ መንገድ ተረሽኗል። ወጣቱ ሥራ ፈጣሪና ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል የከፈተ ብሎም በአካባቢው እጅግ ምሥጉን ነበር።

የዞኑም ሆነ ወረዳው ማኅበረሰብ በፍቅርና በመከባበር በመኖር የሚታወቅና እንደምሣሌም የሚጠቀስ ነው። አንዳንድ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት እያመጡት ያለው መግለጫም አደገኛና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የሚደረግ ከመሆኑም በተጨማሪ ዜጎች ምክንያት እየተፈጠረላቸው በዘፍቃድ እንዲጨፈጨፉ የሚያበረታታ መሆኑንም በግልፅ የሚያሣይ ነው። ሰው በወንጀል ተግባር ተሳትፏል ቢባል እንኳን ለፍርድ ወደ ሕግ ቦታ ቀርቦ ፍርዱን በአደባባይ ያገኛል እንጂ ከሕግ ውጭ ዜጎችን የፊጥኝ አሥሮ በጥይት ደብድቦ መግደል የሚያሳየው ሥርዓቱ በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓባዊ መብት ጥሰት፣ የደቦ ፍርድና ጭካኔ መሆኑን ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት(የሦስቱ ፓርቲዎች ጥምረት) ያምናል፤ የግፍ ግድያውንም በጽኑ ያወገዛል፡፡ ለሞቱት ነፍስ ይማር እያለ ለአካባቢው ማኅበረሰብና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሦስቱ ወጣቶች ዘፈቀዳዊ ግድያና በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ ተመሳሳይ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን በማውገዝ የአንድ ቀን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ “የንጹሓን የግፍ ግድያ ይብቃ//Stop Massacre of Civilians//” በሚል ቃል እንዲያወግዝና ድምጹንም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያሰማ ጥሪ እያቀረብን፤

1. ከሕግ ውጭ ምክንያት ፈጥሮ ግድያ የፈጸሙ የፀጥታ ኃይሎችና ግፉ እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ አካላት ለፍትሕ አደባባይ እስከሚቀርቡ ሕዝቡ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

2. ግፉን ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት እየሰጡ ያሉት የማንአለብኝነት መግለጫ እንዲቆም እያሳሰብን ግድያዎች አፋጣኝ፣ ገለልተኛ፣ ግልጽና አስተማማኝ ምርመራ እንዲደረግባቸው እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ነሐሴ ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት  እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም!በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የ...
12/08/2026

የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም!

በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ኢትዮጵያ ሀገራችን እያለፈችበት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት በምክክር ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አገር ልትጸና ይገባል በሚል ጽኑ እምነት ፓርቲያችን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሥረታው፣ በኮሚሽነሮች አመራረጥና በኮሚሽኑ የአሠራር ሂደት፣ የአካታችነት ችግሮች፣ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖና መሰል አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችንና የመፍትሔ ጥቆማዎችን ፓርቲያችን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል። ፓርቲያችን በምክክሩ ሂደት እና ከምክክሩ አስቀድሞ ስኬታማ ምክክር ለማካሄድ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ብሎ የሚያምንባቸውን ሃሳቦችና ቅድመ ሁኔታዎች በግልጽ አስቀምጦ ያለመታከት ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ በመጥፋቱ አገር ባለችበት ሁኔታ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። እናት ፓርቲ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ተጉዞ በስኬታማ መልኩ ሊጠናቀቅ ቢችል የአገራችን መፃኢ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልን ሂደት ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በማለት በቸልታ ሊመለከተው ያልፈለገ ሲሆን ይልቁን ሂደቱ ውስጥ በማሳተፍ ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ ለአገር የሚበጁ ሀሳቦችን በማንሳት ለመሞገት ብሎም በተመካካሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ በጎ ተጽዕኖ መፍጠርን በማሰብ በምክክሩ እየተሳተፈ ይገኛል።

አገር የገባችበት ችግር ከምንጊዜውም ይልቅ በተወሳሰበበት ሁኔታ ውስጥ የምክክሩ ሂደት ከነችግሮቹ እያነከሰ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለ ቢሆንም በሂደቱ የጎሉ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል። ለአብነትም በወረዳ ደረጃ ተደረጉ ከተባሉ ምክክሮች ጀምሮ የምክክር ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ባለው በዚህ ምክክርም አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መሆናቸውን መረዳት ችለናል። በምክክሩ ሂደት ድምጾች እንዳይሰሙ መገደብ፣ የአካታችነት ችግሮች፣ የተሳታፊዎች ምርጫና ምደባ፣ የፍትሓዊነት፣ የገለልተኝነት፣ የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ የውይይት ተሳትፎውን ለማጥበብ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናና ወከባዎች፣ የምክክሩ አጠቃላይ ወለል ወይም ቀይ መሥመር ያለመኖር እና የመሳሰሉ ጉልህ ችግሮች የተስተዋሉበትን እውነታ ታዝበናል።

ምክክሩ ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን እንዳለፈው ጊዜ ስሑት ትርክትና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ብሎም ሁሉ ለእኔ ብቻ ፍላጎት በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር እና ዋና መገለጫ ጌጦቿን ኹሉ ለድርድር ያቀረበ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚኽም የምክክሩን ፍትሓዊነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ይኽ ደግሞ ፓርቲያችንና ሌሎች ተሳታፊዎች ከሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያስገደደ ይገኛል።

ምክክር የቅንጦት ጊዜ ኹነት ሳይኾን የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ ውጥን ነው። ቀዳሚው ዘርና ጎሳ ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም ሀገራችንን ሊያጠፋት ከጫፍ ደርሶ እያለ ይህን ያፈጠጠ አደጋ ሊያስቀር ወይም ሊያለዝብ የሚችል መፍትሔ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልክቱ እንኳ አለመታየቱ እጅግ የሚያስቆጭ ነው። እንዲያውም ገና ምክክሩ ሳይጠናቀቅ አንዳንድ ክልሎችን በስም ተጠርተው ሌላ ክልል ለማዋለድ ምክረ ሀሳብ ሲነሳ ብቻ በደስታ ይጨበጨባል፤ ሌላው ደግሞ ማን ነክቶን እያለ በማን አለብኝነት መግለጫ ይሰጣል። ይህም በዘርና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለሀገር አንድነትና ሕልውና ሥጋት መሆኑን አንዱ ማሳያ ነበር። በሌላ በኩል ይህ ምክክር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ሦስት ክልሎች ላይ ጦርነቶች እየተካሄዱ ነው፤ ሌላውም መጣሁ እያለ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱን ጉዳይ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ እውነተኛ፣ ጥልቅ ውይይትና ደፋር ምክረ ሀሳብ ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሂደቱ ግን እከከኝ ልከክህ ሆኖ የአንድን ወገን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ቀድሞ የተወሰነን ውሳኔ በሀገራዊ ምክክር ስም ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ እየተከናወነ ነው። የታሪክና የትርክት መፋለሶች በናኙበት በዚህ ዘመን ቢያንስ እውነት አፈላላጊ ቡድኖችን አዋቅሮ ግማሽ መንገድ እንኳን ማቀራረብ ይገባ ነበር።

እነዚኽንና መሰል አንኳር ጉዳዮች እንጂ የኢትዮጵያ መሪ (ከፕሮቶኮል አንጻር ነው አመክንዮው) ጠቅላይ ሚንስትር ሳይሆን ፕሬዝዳንት መኾን ነው ያለበት ላይ አልነበረም የችግሮቹ ቋጠሮ ያለው። ዙሪያ ዙሪያዋን ሲሏት የነበረችውን አዲስ አበባ በወከባ ብዛት ለአንድ ቡድን ሆ ብሎ ለማሳቀፍና አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስም አልነበረም ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ ድሬዳዋ ከየት ወገን ትሑን የሚለው ሀገር ሊያፈርስ ደርሶም አልነበረም በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት አባክነን ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ በዓለም በልዩነት የምንታወቅበት ዘመን አቆጣጠር አሥሮ ይዞንም አልነበረም ምክክር ያስፈለገን፡፡ በአጠቃላይ የተጠቀሱና መሰል የተስተዋሉ ሳንካዎች ምክክሩ ከታለመለት ዓላማና በሀገሪቱ ያለውን ችግር ከሥሩ ከመፍታት ይልቅ ጠግኖ ለማስቀጠል፣ ለይምሰል የተደረገ፣ የአገዛዝ እና ቡድን(ኖች) ጠባብ ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ይሰማናል። በዚህም በመሠረታዊ የሀገር ሕልውና ጉዳዮች በዋናነት የርስ በርስ ጦርነትን በማስቆም፣ የዘርና ጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስቀረት/ማለዘብ እንደ ዋና ግብ መያዝና መሰል የተጋረጡ ፈተናዎች በአግባቡ ተረድቶ እልባት የሚበጅበትን አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ከመነሻው እንደከሸፈ ለመረዳት ነቢይ መሆን አይጠይቅም።

እናት ፓርቲ ከዚህ በመለስ ባሉ የምክክር አጀንዳዎች እና በምክክር ስም ተላለፉ በሚባሉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን የማያሰፍር መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቅ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚህም፤

1. ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ለማሳካት ከሚፈለግ ማንኛውም ፍላጎትና ሀገርን አስይዞ ከሚደረግ የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ እናሳስባለን።

2. ተመካካሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ውሳኔዎች ሽፋን ከመስጠት እና በታሪክ ተወቃሽ ከሚያደርጉ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሀገርና ለሕዝብ መቆምን በቀረችው አጭር ጊዜም ቢሆን በድፍረት እንዲያሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን።

3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት አካላትን ፍላጎት ማስፈጸሚያና ለአዲስ ቁርሾ የሚያዘጋጅ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እናት ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share