Financial Intelligence Service-Ethiopia

Financial Intelligence Service-Ethiopia ይህ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ነው።This is the official page of Financial Intelligence Service.

የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ -------------------ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ምበወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ ...
28/05/2026

የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ
-------------------
ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሣሪዎች ብዜትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎች መከላከልና መቆጣጠር ቅንጅታዊ ሥራዎች ማጠናከር ዙሪያ ከመንግስትና የግሉ ዘርፍ ከተውጣጡ የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ስልጠናና ውይይት እየተካሄደ ነው።

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ !
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ !

55ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎችየሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም  ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ...
26/05/2026

55ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው አካላት ተጠቃሚ የሚሆኑ ባለቤቶችን መረጃ ግልጸኝነት ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በአግባቡ ለማስፈጸም እንዲያስችል ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

PUBLIC NOTICE FROM NATIONAL BANK OF ETHIOPIA------------------------------------------------------------------------    ...
25/05/2026

PUBLIC NOTICE FROM NATIONAL BANK OF ETHIOPIA
------------------------------------------------------------------------
PUBLIC NOTICE
NOTICE ON FX DIRECTIVE AMENDMENT AND RATIONALIZATION OF FEES AND CHARGES ON LETTERS OF CREDIT
25 May 2026 | Addis Ababa, Ethiopia
The National Bank of Ethiopia, as part of its ongoing transition toward a market-based foreign exchange regime, has been implementing a series of carefully sequenced reforms to strengthen the efficiency, transparency, and competitiveness of the foreign exchange market.
Since the introduction of the market-based foreign exchange regime in July 2024, the NBE has continued to advance reforms aimed at establishing a well-functioning foreign exchange system that aligns with international best practices. These efforts have contributed to notable progress in enhancing market operations and supporting foreign exchange market stability.
Despite these improvements, further amendment to the FX Directive has become necessary to relax foreign exchange administration and approval bottlenecks for ease of doing business and thereby strengthen the development of foreign exchange market. In this regard, the articles of FXD/01/2024 are hereby amended as follows:
I. Amendment to FX Directive No. FXD/01/2024
1. Banks are authorized to approve Letters of Credit on acceptance for institutions holding foreign currency accounts, and retention accounts holders, without prior approval of NBE.
2. Banks are authorized to approve Cash Against Documents on acceptance for institutions holding foreign currency accounts, and retention account holders, without prior approval of NBE.
3. Institutions holding foreign currency accounts, including retention account holders, may order or initiate shipment of goods under Cash Against Documents arrangements without prior approval of Banks. Payment processing shall be subject to the submission and verification of the required documents.
II. Rationalization of Fees and Charges on Letters of Credit
The structure of fees and charges applied by commercial banks on foreign exchange related Letter of Credit (LC) transactions remain inconsistent with prevailing global norms. In view of this, the NBE has undertaken a rationalization of fees and charges on LC arrangements to ensure alignment to international standards.
Accordingly, the National Bank of Ethiopia hereby instructs all banks to implement the following:
1. Fees and charges applicable to Letter of Credit transactions for institutions holding foreign currency accounts, including retention account holders, shall be determined on an annualized basis and applied pro-rata in accordance with the tenor of the respective Letter of Credit.
2. The annualized fee rate applicable to Letter of Credit transactions shall not exceed the maximum limit previously set by the National Bank of Ethiopia.
This measure is intended to ensure that LC-related charges are competitive and consistent with international pricing practices. It is also expected to reduce transaction costs for importers and exporters, enhance the competitiveness of Ethiopia’s trade finance environment, and further strengthen the credibility and effectiveness of ongoing foreign exchange reforms.
The National Bank of Ethiopia will continue to monitor developments closely and take additional measures as necessary to support a stable and efficient foreign exchange market.

በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በስነ-ምግባር ደንብ፣ በጥቅም ግጭት ምንነት፣ መንስኤዎችና መከላከያ እርምጃዎች ላይ ለሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
22/05/2026

በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በስነ-ምግባር ደንብ፣ በጥቅም ግጭት ምንነት፣ መንስኤዎችና መከላከያ እርምጃዎች ላይ ለሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ማፅዳት እንዴት ይፈፀማል?-----------------------------------------------------ወንጀለኞች የንግድ ግብይቶችን በማጭበርበር ገንዘብ...
21/05/2026

በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ማፅዳት እንዴት ይፈፀማል?
-----------------------------------------------------
ወንጀለኞች የንግድ ግብይቶችን በማጭበርበር ገንዘብ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ያሸጋግራሉ። እንዴት?

• ለንግድ እቃዎች ዋጋ ከእውነተኛው የገበያ ዋጋ በላይ ደረሰኝ በማቅረብ (Over-Invoicing) ተጨማሪ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረግ፣
• ለንግድ እቃዎች ዋጋ ከእውነተኛው የገበያ ዋጋ በታች የሆነ ደረሰኝ በማቅረብ (Under-Invoicing) ዋጋን ወደ ውጭ ሀገር ማሸጋገር፣
• የእቃዎችን መጠን፣ ጥራት ወይም ዓይነት በሐሰት ማቅረብ፣
• የተላኩ የንግድ ዕቃዎች ከቀረቡ ሰነዶች ጋር የማይጣጣሙ መሆን፣
• የንግድ ዕቃዎችን ግንኙነት ባላቸው ወይም እህት ድርጅቶች መካከል በተደጋጋሚ እንዲላላክ በማድረግ የንግድ እንቅስቃሴ ያለ ለማስመሰል ሀሰተኛ የንግድ እንቅስቃሴ መፍጠር፣
• የንግድ ሰነዶችን ሙሉ በሙሉ በሐሰት ማዘጋጀት
ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል ናቸው።

የአካውንት እና የግብይት እንቅስቃሴ የስጋት/አደጋ ምልክቶች--------------------------------------------------------------በንግድ ላይ የተመሰረተ ከወንጀል ...
20/05/2026

የአካውንት እና የግብይት እንቅስቃሴ የስጋት/አደጋ ምልክቶች
--------------------------------------------------------------
በንግድ ላይ የተመሰረተ ከወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ እንዳይታወቅ የማድረግና የማፅዳት የወንጀል ተግባራት አመላካች የስጋት ምልክቶችን ከንግዱ መዋቅራዊ ሁኔታ፣ ከንግድ ድርጅት የንግድ ተግባራት፣ እንዲሁም ከንግድ ሰነዶችና ዕቃዎች አንፃር አስቀድመን ተመልክተናል።
በዚህ ፅሑፍ ከአካውንት እና የግብይት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የወንጀል ስጋት/አደጋ ጠቋሚ ምልክቶች እነዚህ ናቸው፦

1. የክፍያ ሁኔታ በመጨረሻ ሰዓት መቀየር

የንግድ ድርጅት ክፍያውን በመጨረሻ ሰዓት ወደ ያልታወቀ አካል መለወጥ ወይም የክፍያ ቀን/መጠን ለመቀየር መጠየቅ።

2. ከንግድ ተፈጥሯዊነት ውጭ የሆነ ከፍተኛ ግብይት

አካውንቱ ከተገለጸው የንግድ እንቅስቃሴ ጋር የማይጣጣሙ በቁጥር ወይም በዋጋ ከፍተኛ ግብይቶችን ማሳየት።

3. “መሻገሪያ/Pay-through” አካውንት መጠቀም

ከፍተኛ ግብይት በፍጥነት መካሄድ እና በቀኑ መጨረሻ ትንሽ ቀሪ ገንዘብ ብቻ መኖር።

ከውጭ ለሚመጡ የንግድ እቃዎች የሚከፈለው ክፍያ ከእቃዎቹ ተቀባይ ውጭ ባለ አካል ይፈጸማል። ይህም ግልጽ የኢኮኖሚ ምክንያት የሌለው ሲሆን ለምሳሌ በንግድ ግብይቱ ውስጥ ያልተሳተፈ በተሸፈነ (በተደበቀ) ኩባንያ ወይም በፊትለፊት ኩባንያ ሊፈፅም ይችላል።

4. ክፍያ በሶስተኛ ወገን መፈፀም

ከእቃ ተቀባይ ውጭ ያለ አካል (shell/front Company) ክፍያ መፈፀም።

5. የግብይት ሪፖርቶች ተደጋጋሚ ከገደብ በታች መሆን፣

ግብይቶች ሁልጊዜ ከሪፖርት ገደብ በታች መኖር። የንግድ ድርጅቱ የጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ሌሎች ግብይቶች በተደጋጋሚ ከሚጠየቀው የሪፖርት ገደብ በታች ብቻ ሆነው ይታያል።

6. ድንገተኛ የግብይት እድገት እና በድንጋት መዝጋት

ከንግድ ድርጅቱ ጋር የተያያዙ የግብይት እንቅስቃሴዎች በፍጥነት እና በከፍተኛ መጠን ይጨምራሉ። ከዚያም ከአጭር ጊዜ በኋላ ድንገት እንቅስቃሴ ይቆማል።

7. በዙር መጠን ክፍያዎችን መፈፀም

በዘርፉ ያልተለመዱ ከፍተኛ መጠን ያለው ክፍያ በዙር ይፈፀማሉ።

8. የፈንድ ምልልስ

ገንዘብ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ወጥቶ እና በሌሎች አገራት ካለፈ በኋላ ወደ መጀመሪያው አገር ይመለሳል።

ከንግድ ሰነዶች እና ሸቀጦች ጋር የተያያዘ የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰል ስጋት ማሳያዎች------------------------በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ የማስመሰል የወንጀል ተግ...
15/05/2026

ከንግድ ሰነዶች እና ሸቀጦች ጋር የተያያዘ የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰል ስጋት ማሳያዎች
------------------------
በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ የማስመሰል የወንጀል ተግባር ከሚፈፀምባቸው መንገዶች መካከል የንግድ ሰነዶችን እና የሸቀጦችን መግለጫዎች በመጠቀም ነው። ከዚህ የወንጀል ተግባር ጋር በተያያዘ የተለመዱ ስምንት የስጋት ማሳያ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።

1. በኮንትራት ውሎች፣ በደረሰኞች ወይም ሌሎች የንግድ ሰነዶች ላይ የወጥነት ማጣት ሁኔታ መኖር፦ በወጪ ንግድ ላኪ ድርጅት ስም አካል እና በክፍያ ተቀባይ ድርጅት ስም መካከል አለመጣጠም መኖር፣ በዋጋ ደረሰኞች እና የውል ስምምነቶች መለያየት ወይም በእቃዎቹ ብዛት፣ ጥራት፣ መጠን ወይም ዋጋ እና መግለጫዎቻቸው ጋር በተያያዘ ልዩነቶች መኖር እንደ ማሳያ ይጠቅማል፤

2. ኮንትራቶች፣ ደረሰኞች ወይም ሌሎች የንግድ ሰነዶች ከንግድ ነክ ጉዳዮች ጋር የማይጣጣሙ፣ ከገበያ ዋጋ ጋር የማይጣጣሙ ወይም ከቀደሙት ተነፃፃሪ ግብይቶች አኳያ በእጅጉ ተለዋዋጭ የሆኑ ክፍያዎችን ወይም ዋጋዎችን የያዙ ከሆኑ፤

3. የእቃዎቹ መግለጫ ግልጽ አለመሆን፦ የንግድ ሰነዶች (ኮንትራት፣ ኢንቮይስ ወይም ሌሎች የንግድ ሰነዶች) ስለሚነገዱት እቃዎች በጣም ጥቅል ወይም ግልጽ ያልሆነ መግለጫ ብቻ የያዙ ሆነው መገኘት።

4. ችግር ያለባቸው የንግድ ሰነዶች፦ ግብይቱን የሚደግፉ የንግድ ወይም የጉምሩክ ሰነዶች አለመኖር፣ ሀሰተኛ የሚመስሉ፣ ሐሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ የያዙ፣ ቀደም ሲል ውድቅ የተደረጉ ሰነዶችን ዳግም አያይዞ የማቅረብ፣ በሰነዶቹ ላይ ተደጋጋሚ ማሻሻያ ወይም ማስተካከያ የሚደረግባቸው ከሆነ፤

5. የኮንትራቶች በጣም ቀላል ሆኖ መገኘት፦ ከውስብስብ ወይም መደበኛ የንግድ ግብይቶች ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ኮንትራቶች በጣም ቀላል እና ያልተለመደ አደረጃጀት ያላቸው ከሆኑ በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ የማስመሰል ስጋት አንዱ ምልክት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ በኦንላይን/በኢንተርኔት ላይ በቀላሉ የሚገኙ ናሙና የኮንትራት አደረጃጀቶችን ተከትሎ የተዘጋጀ ሊሆን ይችላል።

6. የአስመጭና የወጪ ንግድ ዋጋ ከባንክ ማስተላለፊያዎች ጋር ትልቅ ልዩነት ማሳየት፦ የአንድ ድርጅት የተመዘገቡ የአስመጭ እቃዎች ዋጋ ከውጭ ባንኮች ለአስመጭ ከሚደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ መጠን ጋር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ሆኖ ሊገኝ ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ የተመዘገቡ የወጪ እቃዎች ዋጋ ከገቢ የውጭ ባንክ የገንዘብ ማስተላለፍ መጠን ጋር ያለው ልዩነት ሰፊ ሆኖ ሲገኝ።

7. ጊዜያዊ አስመጭ ስርዓት ወደ አገር ውስጥ የገቡ እቃዎች በሀሰተኛ ሰነዶች ተደግፈው ተመልሰው ወደ ውጭአገር የመላክ ሁኔታ ሲኖር፤

8. ምንም አይነት የንግድ ወይም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር እቃዎች በብዙ ሀገራች ውስጥ እንዲያልፉና እንዲጓጓዙ የማድረግ ሁኔታ ሲኖር በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰልና በመደበኛ የንግድ ስርዓት ውስጥ ለማስገባት የሚደረግ ሂደት መኖሩን የምጠቁም ቀይ መብራት በመሆኑ ተገቢውን የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ይጠይቃል።

ተጠርጣሪዎች የተሰወረ ታክስን እንዲከፍሉ ማድረግ ተችሏል
12/05/2026

ተጠርጣሪዎች የተሰወረ ታክስን እንዲከፍሉ ማድረግ ተችሏል

ተጠርጣሪዎች የተሰወረ ታክስን እንዲከፍሉ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታክስ የሰወሩ ተጠርጣሪዎችን በወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ ባሻገር የተሰወረው ታክስ እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል አሉ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ።

ዋና ዳይሬክተሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ፥ ከሁለት ዓመታት ወዲህ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በኩል የታክስ ስወራን የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ነው።

የታክስ ስወራ ጥርጣሬ ሲያጋጥም ለታክስ ሰብሳቢ ተቋማት በማሳወቅ ምርመራ እንደሚካሄድ አንስተው፤ በዚህም ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የተሰወረ ታክስ እንዲመለስ መደረጉን አስታውሰዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ከታክስ ስወራ ጋር የተያያዙ ክትትሎች እና ምርመራዎች በተጠረጠሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የባንክ ሒሳቦች ላይ ተደርገዋል ብለዋል።

በታክስ ስወራ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ6 ሺህ በላይ የባንክ ሒሳቦች ላይ ምርመራ መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም ባለፉት 9 ወራት ከታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ለክልል እና ለፌደራል ተቋማት 129 የደህንነት ሪፖርት መላኩን ገልጸዋል።

969 ተጠርጣሪዎች በቀጥታ የተሰወረውን ታክስ እንዲከፍሉ ማድረግ መቻሉንም አስረድተዋል።

ታክስ የሰወሩ ተጠርጣሪዎችን ከፍትህ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በወንጀል ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ መቀጠሉንም አስረድተዋል።

በታሪክ አዱኛ

በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ማፅዳት፦ አደገኛ የስጋት ምልክቶች !-----------------------------------------------------------------የንግድ ተግባር ላይ...
11/05/2026

በንግድ ሽፋን የወንጀል ገንዘብ ማፅዳት፦ አደገኛ የስጋት ምልክቶች !
-----------------------------------------------------------------
የንግድ ተግባር ላይ የተመሰረተ የማጽዳት ሁኔታ፣
በንግድ ላይ የተመሰረተ ከወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ እንዳይታወቅ የማድረግና የማፅዳት የወንጀል ተግባራት አመላካች የስጋት ምልክቶችን ከአራት ጉዳዮች ማለትም፦
• ከንግዱ መዋቅራዊ ሁኔታ፣
• ከንግድ ድርጅት የንግድ ተግባራት፣
• ከንግድ ሰነዶችና ዕቃዎች እንዲሁም
• ከግብይትና የሂሳብ ምዝገባ ተግባራት አንፃር ለያይቶ መመልካት እንደሚቻል እና ከንግዱ መዋቅራዊ ሁኔታ የሚስተዋሉ አመላካች ተስጋት ምልክቶችን ከዚህ በፊት ተመልክተናል።
በዚህ ይዘት ከንግድ ተግባር ጋር የተያያዙ የወንጀል ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰልና ለማጽዳት የሚደረጉ ሂደቶች አመላካች ስጋቶች ምንድን ናቸው? የሚለውን እንመልከት።
ከወንጀል የተገኘ ገንዘብ በንግድ ሽፋን ህጋዊ መደበኛ የንግድ ስርዓት ውስጥ በማስገባት ህጋዊ የማስመሰል እና የማፅዳት ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው የሚያሳዩ 7 አደገኛ የስጋት ምልክቶች፦
1. የንግድ እንቅስቃሴው ከድርጅቱ የተገለፀው የስራ መስክ ጋር አለመጣጠም።
(ለምሳሌ የተሽከርካሪ ንግድ ላይ የተሰማራ መሆኑ የተገለፀ ድርጅት አልባሳት አስመጪ ወይም ላኪ ወይም የውድ እቃዎች (ወርቅ፣ አልማዝ ሌሎች) ነጋዴ ሆኖ ሲገኝ፤)
2. ያልተጠበቁ ሶስተኛ ወገኖችን በንግድ ሂደቱ ውስጥ ማስገባት።
አንድ የንግድ ድርጅት ከንግድ መስኮቹ ጋር የማይጣጣሙ ብዙ የሶስተኛ ወገኖችን በንግድ ሂደቱ ውስጥ በማካተት ውስብስብ የንግድ ግብይቶች ላይ ተሳትፎ ሲገኝ፤
3. ያልተለመዱ የመጓጓዣ ዘዴዎችን መጠቀም።

አንድ የንግድ ድርጅት ከመደበኛና ከተለመደው የንግድ ተግባራት ለየት ያሉ ግብይቶችን፣ የመርከብ/የመጓጓዣ መንገዶችን ወይም ዘዴዎችን መጠቀም ሁኔታ ሲኖር ፤
4. ውስብስብ እና ያልተለመዱ የፋይናንስ ምርቶችን መጠቀም።
አንድ የንግድ ድርጅት ያልተለመዱ ወይም በጣም ውስብስብ የሆኑ የፋይናንስ ምርቶችን በተለያዩ የንግድ ስራው ምዕራፎች ውስጥ አወሳስቦ የመጠቀም ሁኔታ ሊኖር ይችላል። ለምሳሌ የክሬዲት ደብዳቤ (LC) በልተለመደ ሁኔታ ያለምክንያት ለረጅም ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ የማራዘም ሁኔታ መታየት እንዲሁም የተለያዩ የንግድ ፋይናንስ ምርቶችን በተለያዩ የንግድ ግብይት ክፍሎች ላይ በመቀላቀል መጠቀም የወንጀል ተግባሩ ስለመኖሩ አንዱ አመላካች ጠቋሚ ሊሆን ይችላል።
5. በጣም ዝቅተኛ የትርፍ ህዳግ ማሳየት።
የአንድ የንግድ ድርጅት በግብይቶቹ ውስጥ ያልተመኘ ዝቅተኛ የትርፍ መጠን በቀጣይነት ማሳየት፤
ለምሳሌ፡ እቃዎችን በችርቻሮ ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ ዋጋ መግዛት (import) ወይም እቃዎችን በተመሳሳይ ዋጋ ወይም ከግዢ ዋጋ በታች መሸጥ (re-sale)።
6. አዲስ የተቋቋመ ድርጅት በከፍተኛ መጠን እና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ንግዶች ውስጥ ድንገት መግባት።
አንድ የንግድ ድርጅት አሳማኝ ባልሆነ መልኩ በተደጋጋሚ ዝቅተኛ የትርፍ ህዳግ ያስመዘግባል። ድርጅቱ ለምሳሌ የጅምላ ሸቀጦችን አስመጪ ቢሆን ሸቀጦችን በችርቻሮ ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ዋጋ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ወይም ደግሞ ሸቀጦቹን ባስመጣበት ዋጋ ወይም ካስመጣበት ዋጋ ባነስ የመሸጥ ሁኔታ ሲኖር አንዱ ማሳያ ነው።
7. ከንግድ ተግባሩ ጋር የማይጣጣሙ የገንዘብ ፍሰቶች።
አዲስ የተቋቋመ ወይም ወደ እንቅስቃሴ ተመልሶ ከገባ ረጅም ጊዜ ያልቆየ የንግድ ድርጅት ከፍተኛ መጠን ያለው እና ከፍተኛ ዋጋ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ ሊገኝ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ያልታወቀ ድርጅት በድንገት ታይቶ ወደ ገበያ በመግባት ከፍተኛ እንቅፋት ባለባቸው ዘርፎች ውስጥ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል።
በአጠቃላይ ከአንድ የንግድ ድርጅት ተግባራት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ የወንጀል ገንዘብን ህጋዊ የማስመሰልና ወደ መደበኛ የንግድ ስርዓት ለማስገባት የሚደረግ ተግባር የስጋት አመላካች ምልክቶች ከላይ የተጠቀሱ እንደ ተጠበቁ ሆነው ሌሎች ማሳያዎችንም እንደየሀገሩ እና የንግድ ሁኔታ በመለየት ለመከላከልና መቆጣጠር ተግባሩ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Financial Intelligence Service-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Financial Intelligence Service-Ethiopia:

Share