08/09/2026
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የጷጉሜ 3 የፅናት ቀን በሰንደቅ ዓላማ መስቀልና ሌሎች ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
*********************
ጷጉሜ 3 -2018 ዓ.ም
ሁሉም የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ በተገኙበት የጷጉሜ 3 የፅናት ቀን ሰንደቃላማ በመስቀልና በሌሎች ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል::
በመንገዳችን ለሚገጥሙን እንቅፋቶች ሳንበገር በፅናትና በአይበገሬነት መንፈስ መሻገር ይገባል ያሉት የክፍለ ከተማው ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የሥራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡን ሀገር መገለጫ የሆነውን ባንዲራ መጠበቅና ከፍ ማድረግ ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት መሆኗን ጠቅሰው በቀጣይም የዛሬው የፅናት ቀን የኢትዮጵያውያንን አንድነት እና ፈተናዎችን አልፎ ለልማት የመቆም ባህልን የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የጳጉሜ 3 የፅናት ቀን ለኢትዮጲያ ማንሰራራት መሰረት የሆነዉ ፅናታችን የሉዓላዊነታችን መሰረት መሆኑ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሐገራችን ሉዓላዊነት መገለጫና የዜጎቿ ፅናት ምስክር ነው ተብሏል።
በተያያዘ ዜና የጳጉሜ 3 የፅናት ቀን በአዲስ መሶብ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሰንደቃላማ መስቀልና ሌሎች ዝግጅቶች ተከብሯል::
# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication