17/10/2021
እነሆ መፍትሔ።
በተከሰተው ናዳ ምክንያት የኧሌ ልዩ ወረዳ መውጫ መንገድ (ከክልል ጋር የሚገናኝበት፤ ጽኑ ህሙማን ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል የሚላኩበት፤ የህዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የሚመላለሱበት) መዘጋቱ ይታወቃል። ለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት የተነሳ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ህብረተሰቡ የልዩ ወረዳውን መንግስት በተደጋጋሚ ጠይቋል። በዚህ መሠረት የልዩ ወረዳው ልዑክ (ዋና አስተዳዳሪ፣ ዋና አፈ ጉባኤ፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት፣ የዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት) ከክልሉ ባለድርሻ ተቋማት( ር/መስተዳደር ጽ/ቤት፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ፣ ደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን፣ መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ፣ ደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን አርባምንጭ ዲስትሪክት፣ ከዲራሼ ት/መ/ል/ጽ/ቤት) ጋር በአካል፣ በስልክና በጽሑፍ በመወያየት በዛሬው ዕለት ማሽኖችን(Grader, Loader, Roller, & Dump Truck) ይዘን ገብተናል። ለዛሬው የቅዳሜ ገበያ ሦስት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ አንቡላንሶችና ሌሎች የመንግስት ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ ተደርጓል። በደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን የአርባምንጭ ዲስትሪክትን እያመሰገንን ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር አስፈላጊውን መፍትሔ እስኪንሰጥ ድረስ ትብብራችሁ እንዳይለየን እንላለን። 'Access Road' ላላገኘ ቅድሚያ ይሰጥ። እንተጋገዝ፤ እንደጋገፍ፣ ወደ ከፍታ ማማ እንውጣ!!!!