A.A Housing Development & Administration Bureau

A.A Housing Development & Administration Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from A.A Housing Development & Administration Bureau, Government Organization, Addis Ababa.

" 2 ቀናት ብቻ ቀሩት!"ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤ጊዜው እየፈጠነ ነው!!የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያስቀመጠው የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ ሊጠናቀቅ...
03/09/2026

" 2 ቀናት ብቻ ቀሩት!"

ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤
ጊዜው እየፈጠነ ነው!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያስቀመጠው የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ለምን ውል ማደስ ያስፈልጋል?

✍ የሁለቱንም ወገን ሕጋዊ መብት ለማስከበር

✍የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንብን (11.5%) አክብሮ
ለመስራት

✍ ከተጨማሪ ቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት
ለመዳን

አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ፦

በየክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤቶች ፤ በየወረዳው እና በሁሉም የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫዎች በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት

"አሁኑኑ ውላችሁን በማደስ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ አላስፈላጊ ቅጣቶች እና እንግልቶች ራሳችሁን ጠብቁ!”

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የመጨረስ ብቃት ጨምሯል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ AMN- ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አቅዶ፣ በፍጥነት በመጀመር...
02/09/2026

በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የመጨረስ ብቃት ጨምሯል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አቅዶ፣ በፍጥነት በመጀመር በፍጥነት የመጨረስ ብቃት ጨምሯል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ የቀጣይ 5 ዓመታት ዕቅድ እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ የመጨረስ ብቃት መጨመሩን አንስተዋል፡፡ የቀጣይ እቅድ ከሃገራዊ ራዕይ እና ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት ከተቀመጡ እሳቤዎች ጋር በማናበብ መታቀዱንም አስረድተዋል።

አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን የሚል ራዕይ ይዘናል ያሉት ከንቲባዋ፤ ይህም ሂደት ውስጥ መግባቱን እና ውጤቶችም መታየታቸውን አንስተዋል፡፡

ህዝቡ ከድህነት የመውጣት፣ የማደግ እና የመልማት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መጨረስ ብክነትን ያስወግዳል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የስራ ባህል እየዳበረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተቋማዊ ብቃትን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሥራት መቻል፣ እንቅፋቶችን እና ችግሮችን ወደ ድል የመቀየር ልምድ፣ ስራዎችንም በጥራት በመስራት ወደ ውጤት የመቀየር ልምድ አዳብረናል ሲሉም ከንቲባዋ ገልጸዋል።

የሻምበል ምህረት

02/09/2026
የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

" 3 ቀናት ብቻ ቀሩት!"ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤ጊዜው እየፈጠነ ነው!!የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያስቀመጠው የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ ሊጠናቀቅ...
02/09/2026

" 3 ቀናት ብቻ ቀሩት!"

ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤
ጊዜው እየፈጠነ ነው!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያስቀመጠው የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ለምን ውል ማደስ ያስፈልጋል?

✍ የሁለቱንም ወገን ሕጋዊ መብት ለማስከበር

✍የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንብን (11.5%) አክብሮ
ለመስራት

✍ ከተጨማሪ ቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት
ለመዳን

አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ፦

በየክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤቶች ፤ በየወረዳው እና በሁሉም የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫዎች በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት

"አሁኑኑ ውላችሁን በማደስ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ አላስፈላጊ ቅጣቶች እና እንግልቶች ራሳችሁን ጠብቁ!”

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A.A Housing Development & Administration Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share