Tocha Woreda Health Office

Tocha Woreda Health Office This is an official face book page of Tocha woreda health office

30/08/2022
24/08/2022

የደም ባንክ አስተባባሪዎችን በገጠማቸው ማህበራዊ እክል የዛሬ ደም ልገሳው ለተወሰኑ ቀናት መራዘሙን ከይቅርታ ጋር እያሳወቅን ቀጣይ የልገሳ ቀኑን በቅርቡ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

23/08/2022

#ታላቅ የበጎ አድራጎት ጥሪ ለቶጫና አከባቢዉ ማህበረሰብ በሙሉ
=========================================
የቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ከታርጫ ደም ባንክ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በነሐሴ 18/2014 ዓ.ም በቶጫ ከተማ የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጅቶሎታል፡፡ በነጻ እና በበጎነት የምንለግሰዉ ደም የደም ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ ወገኖችን ህይወት ለማስቀጠል በነጻ የሚሰጥ ነዉ፡፡

#የምንለግሰዉ ደም፡-
በእርግዝና እና በወሊድ ምክንያት ከፊተኛ የደም እጥረት እና መፍሰስ ለሚያገጥማቸዉ እናቶች
በመኪና አደጋ ለተጎዱ ወገኖች
ለካንሰር ታማሚዎች
ለደም ማነስ ታማሚዎች እና ሌሎች የደም አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸዉ ወገኖችያለ አንዳች ክፊያ በነጻ ይሰጣል፡፡

#ደም መለገስ ህይወትን ከማስቀጠል በተረፈ ለለጋሹ የሚከተሉት የጤና ጥቅሞች ይኖሩታል፡፡
#ደም መለገስ፡-
በሰዉነታችን ዉስጥ የሚገኝ የብረት መጠን በማስተካከል የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
ለልብ ድካም የመጋለጥ ዕድልን ይቀንሳል
አላስፈላጊ የሆነ የደም መወፈር እና መጣበቅን ይቀንሳል
አላስፈላጊ የሆነ የሰዉነት ክብደትን ያስተካክላል
የአዕምሮ ዕርካታን ይሰጣል
የደም ግፊት ተጋላጭነትን ይቀንሳል

#ደም መለገስ የሚችሉት እነማን ናቸዉ?
ዕድሜያቸዉ ከ18-65 ዓመት የሆኑ
የሰዉነት ክብደታቸዉ ከ45 ኪ.ግ በላይ የሆኑ
የተስተካከለ የደም ግፊት መጠን ያላቸዉ
ነፍሰ ጡር እና አጥቢ ያልሆኑ
ለተለያዬ በሽታ መድኃኒት እየወሰዱ ያልሆኑ በሙሉ

#ደም ከስጦታዎች ሁሉ የሚበልጥ ዉድ ስጦታ ነዉ
#ደምን መስጠት ህይወትን ለምትሰጥ እናት ህይወት መስጠት ነዉ
#ደምን መስጠት የወገኖችን ህይወት ማስቀጠል ነዉ
#ኑ ደምን በመስጠት የወገኖቻችን ሕይወት እንታደግ

የልገሳ ቦታ:- ላይ አራዳ መስቀል አደባባይ ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ

የቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት

ዛሬ የቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤ አካሂዷል። በጉባኤው የጤና መምሪያ ኃላፊ፣ የወረዳ ፊት አመራሮች፣ የባለድርሻ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የግል ጤና ተቋማት ባለቤቶች...
18/08/2022

ዛሬ የቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤ አካሂዷል። በጉባኤው የጤና መምሪያ ኃላፊ፣ የወረዳ ፊት አመራሮች፣ የባለድርሻ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የግል ጤና ተቋማት ባለቤቶች፣ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና የሆስፒታል ባለሙያዎች፣ የቀበሌ ሊቃነ መናብርት እና ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።ጉባዔው የ2014 በጀት ዓመቱን አፈጻጸም በብስለት ገምግሞ ለቀጣይ ዓመት አፈጻጸም አቅጣጫ አስቀምጧል። በጉባኤው በ 2015 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ሆስፒታል እና ጤና ኬላ የሶስትዮሽ እንዲሁም ጤና ጥበቃና ሆስፒታል የሁለትዮሽ ግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

18/08/2022
18/08/2022
18/08/2022

❖ የጤና ተቋማት ተግባር ለማሳለጥ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቅንጅታዊ የአሠራር ሥርዓት መከተል ለዓላማው ስኬት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። አቶ ታደለ ታዬ ዋና አስተዳዳሪ፤

ነሐሴ፦ 12/2014 ዓ/ም (የቶጫ ወረዳ የመኮጉ ጽ/ቤት)

❖ በዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የ2014 ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2015 ዓ/ም ጠቋሚ ዕቅድ ማስተዋወቂያ የንቅናቄ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

❖ በመድረኩ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የፓርቲና የመንግሥት አመራር አካላት እንዲሁም የቀበሌ መዋቅር አመራር አካላት የጽ/ቤትና የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

❖ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስናቀ አብርሃም በመክፈቻ ንግግር በጤና ዘርፍ የሚከናወነዉ ተግባር ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማስመዝገብ የልማት አንቀሳቃሽ ኃይል ጤንነቱ በተገቢው ሁኔታ መጠበቅ ሲችል ነዉ ብለዋል።

❖ በመሆኑም ያሉት ኃላፊዉ የሕዝብ ጤንነትን ለመጠበቅ የሁሉም ድርሻ ወሳኝ እንደሆነ በንግግራቸዉ አመላክተዋል፡

❖ አክለዉ ጉባኤዉ በአጽንኦት ሊመክርበት ይገባል ያሉት የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የእናትና ሕጻናት ሞት ቅነሳ፣ የማዐጤመ ጉዳይ እና ሌሎችንም ጠቁመዋል።

❖ የቶጫ ወረዳ ዋና አስ/ሪ ታደለ ታዬ፤ የጤና ተቋማት ተግባር ለማሳለጥ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቅንጅታዊ የአሠራር ሥርዓት መከተል ለዓላማው ስኬት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ ገልጸዋል።

❖ አክለውም የባለድርሻ አካላት በዚሁ ልክ በመረባረብ የሰዉን ሕይወት የማትረፍ ተግባር ማጠናከር ጤናማና ንቁ አምራች ኃይል ከመፍጠር ረገድ የበኩላችንን ድርሻ በተገቢው ሁኔታ መወጣት ይገባልም ብለዋል።

❖ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወሰን ጨመሳ በምንም ሁኔታ የጤና ተግባር አፈጻጸም ላይ አነስተኛ ዉጤት መመዝገብ የለበትም ሲሉ ገልጸዉ በዚህ ደግሞ የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ሚና ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

❖ የጤና ተግባራት የሕዝብን ጤንነት የመጠበቅ፣ በሽታን የመከላከልና ጤናማ ዜጋ የመፍጠር ዓላማ በመያዝ የሚሠራና እጅግ በላቀ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚከናወን በመሆኑ የባለድርሻ አካላት በዚሁ ልክ ተረድተዉ መሥራት አለባቸውም ሲሉ አቶ ወሰን ጠቁመዋል።

ዘገባው፦ የቶጫ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሕዝብና የሚዲያ ግንኙነት ነዉ።
ነሐሴ፦ 12/2014 ዓ/ም

12/08/2022
ዛሬ በወረዳችን አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ የመንግስት እና ግል ጤና ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ባለቤቶች እና Senior ባለሙያዎች ጋር በጽ/ቤታችን ውይይት አድርገናል። በዉይይት ሂደቱም አገልግ...
10/08/2022

ዛሬ በወረዳችን አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ የመንግስት እና ግል ጤና ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ባለቤቶች እና Senior ባለሙያዎች ጋር በጽ/ቤታችን ውይይት አድርገናል። በዉይይት ሂደቱም አገልግሎት አሰጣጥ እና አገልግሎት ጥራትን፣ በማህበረብ ውስጥ በባህላዊ እና ብቁ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሞከሩ ህገወጥ ውርጃን፣ የባለሙያ ስነ ምግባርን፣ ህገ ወጥ የመድኃኒት ዝውውርን እንዲሁም በትርፍ ሰዓታቸው በግል ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን ዉል ህጋዊነት አስመልክቶ በጥልቀት መክረናል። በተያያዘም የግል ጤና ተቋማት አዋጁን እና መመሪያውን ተከትለው በጥንቃቄ የ 24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ እና የሪፖርት ስርዓቱን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በአጽንኦት መልዕክት ተላልፏል።

03/08/2022

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tocha Woreda Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share