Lemi Kura woreda 04 Communication

Lemi Kura woreda 04 Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lemi Kura woreda 04 Communication, Government Organization, Bole Arabsa Road, Addis Ababa.

03/09/2026
በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።ነሐሴ 27/2018 ዓ.ምእየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ለነዋሪዎች የሚሰጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ህብረተሰቡን ማስደሰቱ ተገለጸ።በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በየሳምንቱ እሮብ እና አርብ የሚከናወነው በአንድ ማዕከል የአገልግ...
02/09/2026

ለነዋሪዎች የሚሰጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ህብረተሰቡን ማስደሰቱ ተገለጸ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በየሳምንቱ እሮብ እና አርብ የሚከናወነው በአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት በኩል ለነዋሪዎች የሚሰጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ህብረተሰቡን እጅግ ማስደሰቱ ተገለጸ።

የተቋማቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት አስመልከቶ በተደረገው ቅኝት የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ተገኝተው የኅብረተሰቡን ጥያቄዎችና እንግልቶች በመቅረፍ በቅርበት ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በዕለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም መጥተው በተቋማቱ አስተናጋጅነት የተገለገሉ የነዋሪነት ምስክርነታቸውን የሰጡ ባለጉዳዮች በአገልግሎቱ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ እርካታ ገልጸዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ቀደም ሲል ለአንድ ጉዳይ በተለያዩ ቢሮዎች ስንመላለስ የምናባክነው ጊዜ እንግልት እና ጉልበት አሁን በአንድ ማዕከል አሰራር ሙሉ በሙሉ ሊቀረፍ ችሏል በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

አስተዳደሩ አሁንም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ እና የህዝባችንን እርካታ የበለጠ ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ለሚ ኩራ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
📌 መረጃዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲደርስዎ የሶሻል ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ፦ https://linktr.ee/Lemikuraworeda04communication

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የቤተሰባቸውን የኑሮ ደረጃ ከመቀየር ባለፈ ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም ትምህርት ሰጭ መሆኑ ተገለፀ።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ...
01/09/2026

የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የቤተሰባቸውን የኑሮ ደረጃ ከመቀየር ባለፈ ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም ትምህርት ሰጭ መሆኑ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ ቤት በሚደረግ የጠበቀ ድጋፍና ክትትል የከተማ ግብርናንና የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ውጤታማ የሚያደርጉ አበረታች ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ።

በወረዳው የሚገኙ አርሶ አደሮችና የከተማ ግብርና ተሳታፊዎች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉና ለገበያ የሚሆን ምርት እንዲያቀርቡ በተደረገው እቅድ መሰረት በአርሶ አደር ፍቅሩ ዋቄ መኖሪያ መንደር አርአያነት ያለው ደማቅ ስራ ተከናውኗል። አርሶ አደሩ እንደተናገሩት ከወረዳው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የተደረገላቸው የሙያ ድጋፍና እገዛ ለዚህ ስኬት እንዳበቃቸው ገልጸው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የቤተሰባቸውን የኑሮ ደረጃ ከመቀየር ባለፈ ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም ትምህርት ሰጭ መሆኑን ተናግረዋል።

የወረዳው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የህብረተሰቡን የጓሮ አትክልት ምርት ለማሳደግ ተከታታይነት ያለው የሙያ ድጋፍ፣ የምክር አገልግሎትና የቅርብ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይህ ድጋፍ አርሶ አደሮች በዘመናዊ አሰራር ታግዘው አነስተኛ ቦታን በመጠቀም ከፍተኛ ምርት እንዲያመርቱ ትልቅ አቅም ሆኗቸዋል።

በተደረገው ያላሰለሰ ክትትል በአርሶ አደር ፍቅሩ ዋቄ መኖሪያ የእንስሳት ሀብትና የወተት ልማት፣ የዶሮ እርባታና የእቁላል ምርት እና የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ በመኖሪያ አካቢያቸው በሚገኝ ክፍት ቦታ ላይ በማልማታቸው የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የምግብ ዋስትናቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያረጋግጡ አስችሏቸዋል።

📍 ለሚ ኩራ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን
ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም
ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማግኘት፡- እዚህ ይጫኑ (Linktree)https://linktr.ee/Lemikuraworeda04communication
ስለ አገልግሎታችን ያለዎትን ጠቃሚ አስተያየት ለመስጠት፡- የአስተያየት ፎርም (Jotform)https://form.jotform.com/260342356002040

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

Address

Bole Arabsa Road
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lemi Kura woreda 04 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share