Addis Ababa city courts

Addis Ababa city courts Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa city courts, Government Organization, mexico, Addis Ababa.

23/09/2022

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት
 የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 መሰረት የተቋቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዳኝነት አካል ናቸው፡፡
 ፍርድ ቤቶቹ በመጀመሪያ እና በይግባኝ ሰሚነት ደረጃ የተዋቀሩ ሲሆን የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤቱ በከተማው ፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ስር በሚወድቁ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ሲኖረው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ደግሞ በከተማው የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው ሌሎች አካላት የሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ የይግባኝ ሰሚነት ስልጣን አለው፡፡
 ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ነገር ግን ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ወገን የሰበር ቅሬታውን በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ስር ለተቋቋመው ሰበር ሰሚ ችሎት ማቅረብ ይችላል፡፡
 ፍርድ ቤቶቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41፤ በቻርተሩ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 408/98 እንዲሁም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234 ላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት የዳኝነት ስልጣናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች፣ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንዲሁም የከተማው የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በሚሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ የይግባኝ ሰሚነት ስልጣን አላቸው፡፡
 በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41፤ በቻርተሩ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 408/98 መሰረት እንዲሁም በፌዴራል ፍርድ ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234 አንቀጽ 5(1) (ደ) እና አንቀጽ 4(16) መሰረት የሚከተሉት ጉዳዮችን አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት የዳኝነት ስልጣን አለቸው፡-
 በአዋጅ 361/95 ዓ.ም እና 408/01 የተሰጠን ስልጣን መተርጎም
 ስልጣንና ተግባራት የስልጣን ምንጭ የመንግስት ስልጣን በህግ ከተቀመጠለት ገደብ እንዳያልፍና ይህንንም በተግባር ለማረጋገጥ መጀመሪያ የስልጣንን ምንጭ እና መገለጫ ባህርያት በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል

Address

Mexico
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa city courts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa city courts:

Share