04/02/2023
ግንዛቤ
የንግድ ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ አደጋ ለመከላከል የሚያስችሉ መሰረታዊ ቁምነገሮች
1. ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ከመክፈል ይልቅ በባንክ በኩል መፈፀም የተቀባዮቻችን ዱካ ለመከታተል ያስችላል፣
2. ደረሰኝ ሲቀበሉ ደረሰኙ ላይ ያለውን መረጃ ሻጩ ሻጩ ከለጠፈው የንግድ ስምና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር ያመሳክሩ በዚህም መረጃው የተለያየ ከሆነ ከህገወጥ ድርጅት ጋር ግብይት እየፈፀሙ ነውና ግብይቱን ያቋርፁት፣
3. ዕቃ ወይም አገልግሎት የሸጠልዎት ድርጅት አድራሻ ማወቅ አለብዎት የሻጩን አድራሻ ማወቅ ድርጅቱ ህገዋጥ ሆኖ ሲገኝ በህግ ለመጠየቅ ያግዝዎታል፣
4. ለድርጅትዎ ባለሙያዎች ስለታክስ ግዴታዎች ማስገንዘብ እና ማሳወቅ በግብይት ወቅት አስፈላጊው ጥንቃቄ ለማድረግ ያስችላል፣
5. ስራ አስኪያጆች/ያድርጅት ባለቤቶችየድርጅታቸውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለባቸው በድርጅቱ ባለሙያዎች ህገወጥ ድርጊት ለፈፀም ስለሚችል የድርጅትዎን የፋይናንስ እቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለብዎት፣
6. የድርጅትዎን አሰራር በቴክኖሎጅ የተደገፈ ማድረግ አሰራርን ማዘመን ለህገወጥ ሥራ በር ይሚከፍቱ አሰራሮችንለማስቀረት ይረዳል፣
7. በግብይት ወቅት የድለላ ጣልቃ ገብነት መቀነስ ግብይት ያለሦስተኛ ወገን ጣልቃገብነት መፈፀም ስለሻጩ ማንነት ለማወቅ ያስችላል፣
8. ሻጩ ድርጅት የተሰማራበት የንግድ ዘርፍ እርስዎ የሚገዙት እቃ/አገልግሎት ማቅረብ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ በድርጅቶች በድርጅቶች የሚቀርቡ ደረሰኞች ተቀባይነት የሚኖራቸው የተሰማበት የንግድ ዘርፍ ዕቃው/አገልግሎቱ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን ነው ለምሳሌ ስሚንቶ ሻጭ ልብስ ሸጫለሁ ብሎ ደረሰኝ ቢቆርጥ ተቀባይነት የለውም፣
9. አጠራጣ ደረሰኝ ሲያጋጥምዎት በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ በመሄድ ስለድርጅቱ ትክክለኛነት ያረጋግጡ ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያሰራጩ ህገወጦች በመኖራቸው ግብይት በሚፈጽሙበት ወቅት አጠራጣ ነገር ሲያጋጥምዎት ክፍያ ከመፈፀምዎ አስቀድመው የገቢዎች ባሙያዎችን ያማክሩ፣