02/05/2026
የክላስተር ሁለት 3ኛ ዙር የታክስ እና ጉምሩክ ክበባት የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር በአዘጋጁ ምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርጫፍ ጽ/ቤት አሸናፊነት ተጠናቀቀ ፡፡
…………ሚያዚያ 24/2018 ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
የገቢዎች ሚንስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የታክስ እና የቀረጥ ዕውቀትን ለትውልዱ ለማስገንዘብ ያታክስ ክበባትን በማቋቋም የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር እያካሄደ ይገኛል:: ይህንም ተከትሎ በዛሬው እለት የክላስተር ሁለት 3ኛ ዙር የታክስ እና ጉምሩክ ክበባት የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርጫንጫፍ ጽ/ቤትን በወከለው የካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወሮ ወርቃለም ተሾመ የጥያቄና መልስ ውድድሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩ ሲሆን "እንደ ሀገር ታማኝ እና ሀላፊነት ያለው ትውልድ ለመፍጠር በታክስና በጉምሩክ ጉዳዮች ዙሪያ እውቀት ያለው ዜጋ መፍጠር አስፈላጊ ነው፣ ታክስ የሀገር ልማት መሠረት ሲሆን ሀገር እንድትገነባ የሚያግዝም ዋና ኃይል ነው" በማለት የመደረኩ ዓላማም "ትውልዱ የታክስ እና ቀረጥ እውቀት እንዲያገኝና ኢትዮጵያ የሀገር ወጭ በሀገር ገቢ ለመሸፈን የምትሄድበትን ጉዞ አጋር እንዲሆን ያስችላል" ብለዋል ፡፡
በክላስተር ሁለት አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማጣመር ውድድሩን በምስራቅ ቅርጫፍ አስተባባሪነት የተካሄደ ሲሆን የምስራቅ አዲስ አበባ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ወክሎ የየካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ኃይለ ልዑልየማነ፣ የሰሜን ምዕራብ አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ፅ/ቤትን በመወከል ፤ትብለጥ ተገኝ ከእቴጌ መነን የልጃገረዶች 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ቃል ኪዳን አዲሱ ደግሞ ከለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት, (ቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ እንዲሁም አሜን እስክንድር ቅዱስ ዮሴፍ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ወክሎ ከመካከለኛ ቁ.1 ግ/ከ/ቅ/ፅ/ቤት ተወዳድረዋል፡፡በዚህም መሰረት ከየካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ኃይለ ልዑል የማነ በአንደኛ ደረጃ በማጠናቀቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ክላስተሩን ወክሎ አሸንፏል፡፡የየቅርጫፍ ጽ/ቤት ኋላፊዎች ቅርጫፋቸውን በመወከል ለትምህርት ቤቶች፣ለተማሪዎች ፣ለርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ለአብቂ መምህራን እንደየደረጃቸው የሞባይል፣የገንዘብ፣የሞንታርቦ እንዲሁም የዕወቅና ሰርተፍኬት ሽልማት አበርክተዋል፡፡መድረኩን በተመለከተ የማጠቃላያ ንግግር ያደረጉት በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሲሳይ " በየቅርጫፍጽ/ቤቶች የሚገኙ የታክስ ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ስራ ክፍሎች ግብር ከፋዮችን በማስተማር የታክስና ቀረጥ ዕውቀት በማስጨበጥ እንደ ሀገር መንግስት የሰጠውን ትኩረት ተግባራዊ እያደረጉ እንደሆነ እና ትውልድን በመቅረጽ በርካታ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ክላስተሩን ወክሎ በአንደኛ ደረጃ ላጠናቀቀው ተማረ ኋይለ ልዑል የማነ በቀጣይ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቀው በመግለጽ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ከዚህ ጋር አያይዘው ከሽልማት ባሻገር ተማሪዎች የታክስና ቀረጥ ምንነትን ከሀገር ዕድገትና ፍቅር ጋር በማስተሳሰር በሚሰማሩበት መስክ ሁሉ ከውዲሁ ስለ ታክስና ቀረጥ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያግዛል ብለዋል፡፡