የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማው ህግ አውጪ ተቋም ነው!
(2)

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጋር የልምድ ለውጥ አደረገ::የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ በቀለ የተመራው የሀረሪ  ክልል ምክር ቤ...
28/08/2026

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጋር የልምድ ለውጥ አደረገ::

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ በቀለ የተመራው የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አመራሮች በአዲስ አበባ ምክር ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አድርጏል::

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጀዋሪያ ቀሊ አማካኝነት ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በቆይታቸውም ምክር ቤቱ የሰራቸውን የተለያዩ ሪፎርም ስራዎች ተዘዋወረው ጎብኝተዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ በምስል
27/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ በምስል

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት  የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ አካሄደ።በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና ...
27/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ከተማችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያረጋግጡ ልማቶችን፣ በነዋሪዎቿ ተሳትፎ በማከናወን፤ በሂደቱም በውጤቱም ነዋሪዎቿን ቀጣይነት ባለውና ዘላቂ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ አድርጋለች ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፉት ለውጥ ዓመታት በቋሚ ኮሚቴው ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር አማካኝነት አስፈጻሚ አካላት በህግ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባራት ቆጥረው እንዲፈጽሙ፤ የተመደበላቸው በጀት ለተመደበለት ዓላማ ጥቅም ላይ ውሎ ልማት እንዲረጋገጥ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲረጋገጥ ማድረግ መቻሉንም ጨምረው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በተጠሪ ተቋማትና የክፍለ ከተማ ምክር ቤቶችም ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለው አመኔታ እንዲጠናከር፣ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት እንዲያድግ፣ የተደራጀ ሌብነትና ሙስና እንዳይስፋፋ እና የከተማዋ ነዋሪዎች ወቅታዊና ታማኝነት ያላቸውን መንግስታዊ መረጃዎች እንዲያገኙ እንዲሁም የህብረተሰቡ ቅሬታና አቤቱታ እንዲደመጥ በማድረግ ረገድ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ክብርት አፈ ጉባኤ ተናግረው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለነበራቸው ጠንካራ አፈጻጸም ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ተጠሪ ተቋማትና የክፍለ ከተማ ምክር ቤቶች፣ እውቅናና ምስጋና ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ከተጠሪ ተቋማት:-

1. አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት
2. አዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት
3. አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን
4. አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN)
5. አዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ
6. አዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ሰሚ ጉባኤ

ከክፍለ ከተሞች:-

1. ለቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
2. ለአራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
3. ለየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
4. ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
5. ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
6. ለልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
7. ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
8. ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
9. ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት
10. ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት

ከምክር ቤት:-
1. የንግድ፤ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
2.የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
3. የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
4. የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
5. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም
6.የመንግስት በጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የእውቅናና ምስጋት ምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የጽ/ቤቱ ረቂቅ እቅድ ላይ ከጽ/ቤቱ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
11/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የጽ/ቤቱ ረቂቅ እቅድ ላይ ከጽ/ቤቱ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አሻራቸውን አሳረፉ፡፡ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙ...
03/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አሻራቸውን አሳረፉ፡፡

ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ዛሬ በተካሄደው ሀገራዊ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በንቃት በመሳተፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በመርሃ ግብሩ ወቅት የተገኙት አመራሮችና ሠራተኞች፣ በመላው ሀገሪቱ የታለመውን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመትከል ሀገራዊ ግብ ለማሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"በጋራ ተስፋን እንትከል" በሚል ጥልቅ ትርጉም ባዘለ መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ ሀገራችን የተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት በተጨባጭ የሚያሳይ ልዩ አውድ ነው።

ጉለሌ፣ አራዳ፣ የካ እና ልደታ ክፍለከተሞች የ13ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ እና የበጀት አመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ እንዲሁም የእውቅና መርሐ ግብሮችን አካሂደዋል::
31/07/2026

ጉለሌ፣ አራዳ፣ የካ እና ልደታ ክፍለከተሞች የ13ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ እና የበጀት አመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ እንዲሁም የእውቅና መርሐ ግብሮችን አካሂደዋል::

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በ7ኛው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አበበች ጎበና ሆስፒታል አከባቢ ችግኝ ተከሉ። መርሀ ግብ...
31/07/2026

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በ7ኛው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አበበች ጎበና ሆስፒታል አከባቢ ችግኝ ተከሉ።

መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት የም/ቤቱ ም/ክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ መሐመድ ዛሬ የምንተክላት እያንዳንዷ ችግኝ የነገዋን አረንጓዴ፣ ለም እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን የመገንባት ትልቅ መሠረት ናት ብለዋል።

አያይዘውም የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄያችን የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅማችንን ከማሳደጉም በላይ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የምናስረክበውን ተፈጥሯዊ ሀብታችን ነው ያሉት ምክትል አፈጉባኤዋ የምክርቤታችን አመራሮችና ሠራተኞች አሻራችንን ከማኖር ባለፈ የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብና ጥበቃ በማድረግ ሀላፊነታችንን በመወጣት ታሪክ እንሥራ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2019 - 2023 ስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተካሔደ።ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት።የስትራቴጂክ ዕቅ...
27/07/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2019 - 2023 ስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተካሔደ።

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት።

የስትራቴጂክ ዕቅዱን ግምገማ መድረክ የመሩት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ት ፋዒዛ መሐመድ እንደገለጹት፣ በተቋም ግንባታ ላይ አተኩሮ እየሠራ ያለው ምክር ቤቱ፥ በቀጣዩ ዙርም በሕግ የተሠጡትን ስልጣንና ተግባራት ያለመቆራረጥ ማስቀጠል እንዲችል የስራ ዘመኑ ስትራቴጂክ ዕቅድ ቀድሞ መዘጋጀቱ ፋይዳው የላቀ ነው። ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም የዕቅዱ ዝግጅት የምክር ቤቱ የክረምት ዘጠና ቀናት ሥራዎች ዕቅድና የ2019 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች አካል መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም በየደረጃው ለሚገኙ አካላት ቀርቦ በግብዓት እንደሚዳብር፤ ከምስረታ በኋላም አባላቱም ተወያይተውበት የመጨረሻውን ቅርጽ የሚይዝ መሆኑን አብራርተዋል። የመድረኩ ተሳታፊ የክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችም፣ የዕቅዱ አዘገጃጀት አሳታፊ፣ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ እንዲሁም ተቋማዊ ትውስታን የሚያስቀጥል መሆኑን በመጥቀስ መላ የመዋቅሩ አካላት የተሟላ ግንዛቤ ይዘው እንዲተገብሩት የአስተያየት መስጫ፣ የኦረንቴሽንና የካስኬዲንግ ስራዎች በቀጣይ በትኩረት መሠራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ የ2014-2018 ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በምክር ቤቱ የሥራ ዘመን ማጠቃለያ ጉባኤ ቀርቦ መገምገሙና በሙሉ ድምጽ መጽደቁ ይታወሳል።

ጽ/ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ።የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የምክር ቤቱ ሰራተኞ...
20/07/2026

ጽ/ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የምክር ቤቱ ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት አከናውኗል::

በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጀዋሪያ ቀሊ የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር የሚደረግበት፣ ተሞክሮና የህይወት ልምድ የምንለዋወጥበት፣ የስራ ተነሳሽነትን የምንፈጥርበት ነው ያሉ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመትም ይሄው ልምምድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል::

13/07/2026

Address

ካዛንቺስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ECA ጎን
Addis Ababa
55698

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council:

Shortcuts

Share