03/09/2020
አስተውል ይሄ እውነታ ነው ‼
️ •| ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለትአይደለም!ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ ።
•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ ።
•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ ።
•| አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም !ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ ።
•| ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም ! በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ ።
•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም !ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ ።
•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ ።
•| ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ :: በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇 😷😷😷😷