የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት It's a governmental organization which works on women's,children's and gender equalities issues.

29/08/2026
29/08/2026
29/08/2026
ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር «ከተረጂነት ወደ ምርታማነት» የሰብዓዊ ድጋፍ ማብሰሪያና የእስከሁን አፈጻጸም መድረክ አካሄደ!!!የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡን ከተረጂነት አስተሳሰ...
29/08/2026

ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር «ከተረጂነት ወደ ምርታማነት» የሰብዓዊ ድጋፍ ማብሰሪያና የእስከሁን አፈጻጸም መድረክ አካሄደ!!!

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡን ከተረጂነት አስተሳሰብ በማላቀቅ የራስ አቅምን በማጎልበት ምርታማነትን ለማሳደግና ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለመ የሰብዓዊ ድጋፍ ማብሰሪያ ንቅናቄና የእስካሁን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄዷል።

መድረኩን አስመልክቶ የዕለቱን መወያያ ሰነድ እና የእስካሁን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ኑሪዬ አቅርበዋል።

የንቅናቄው ዓላማ ጊዜያዊ የእርዳታ መፍትሔዎችን በማስቀረት ዜጎች የራሳቸውን አቅም ተጠቅመው ምርታማ እንዲሆኑና ከድጋፍ ተቀባይነት ወደ ራስ አቅም እና ገቢ ፈጠራ እንዲሸጋገሩ የሚያስችል ሥርዓት መገንባት መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ ገልጸዋል።

የከተማችን ማህበረሰብ ከእጅ አዙር እርዳታ ወጥቶ በራሱ አቅም እንዲቆም እና የልማቱ ባለቤት እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲልመጂድ ፊጣሞ በበኩላቸው የተረጂነት አስተሳሰብን ሰብሮ በምርታማነት ለመተካት የሚደረገው ጥረት የነገ ብልጽግናችን መሠረት በመሆኑ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር አበክረን ሊሰራበት የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

 #የሀላባ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ለጋለቶ ጤና ጣቢያ የእናቶች ማቆያ ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ነሀሴ ቀን 22/2018 ዓ ም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀ...
28/08/2026

#የሀላባ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ለጋለቶ ጤና ጣቢያ የእናቶች ማቆያ ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ነሀሴ ቀን 22/2018 ዓ ም

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሀላባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጤና ጣቢያ ሀላፊ አስተባባሪነት ለጤና ጣቢያ የእናቶች ማቆያ ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉም የብርድ ልብስ፣ሸራና ሶላር እንድሁም ውሃ መያዣ ባልዲና ሌሎች መሰል ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ ተችሏል።

በድጋፍ መርሃግብር ላይ የጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ በሀይሉ ስንታየሁ፣የጤና ጣቢያ ማኔጅመንት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣የሀላባ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰበሃ አወል ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

"ከምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ትልቁ ሥራ በሰው ላይ የምንሠራው፣ በተለይም በሴቶች ላይ የምንሠራው ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
28/08/2026

"ከምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ትልቁ ሥራ በሰው ላይ የምንሠራው፣ በተለይም በሴቶች ላይ የምንሠራው ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠንካራ የስራ ባህልን በማጠናከር ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የምናደርገውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፦ አቶ ገመዳ መሀመድ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የማዕከ...
28/08/2026

ጠንካራ የስራ ባህልን በማጠናከር ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የምናደርገውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፦ አቶ ገመዳ መሀመድ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ያሰመረው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተያዘውን ዕቅድ ትግበራ ድጋፋዊ ክትትል አደረገ።

የቡድኑ አባላት እስከ ቀጠና ድረስ በመውረድ የተጀመረውን የልማት ስራዎች በመመልከት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስፋት እና ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል ማጠቃለያ ግብረመልስ ሰጥተዋል።

ጠንካራ የስራ ባህልን በማጠናከር ልመናንና ተረጂነትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የሚቻለው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የተጀመረውን ስራ ስኬታማ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል።

ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነትን በማሳደግ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ችግር በራስ አቅም ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ በመተግበር በዐቢይ ኮሚቴ እየገመገመ ፍጥነት መጨመር መስራት እንደሚገባም አብራርተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ በበኩላቸው ሕዝቡ ከተረጅነት ወጥቶ በራሱ አቅም እንዲቆም የተጀመረውን ስራ ስኬታማ ለማድረግ የህብረተሰቡን የስራ ባህል አጠናክሮ ማስቀጠል ከምንም ጊዜ በላይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ገልጸው የሱፐርቪዥን ቡድኑ ያደረገው ድጋፍ ለቀጣይ ስራዎች ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የሱፐርቪዥን ድጋፍና ክትትል ተካሄደ‎‎ከሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስ...
28/08/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የሱፐርቪዥን ድጋፍና ክትትል ተካሄደ

‎ከሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ግንባሮች በ2019 በጀት ዓመት እስከአሁን የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም ድጋፍና ክትትል አካሂዷል።

‎የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተለይም በፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር ብልጽግና ቤተሰቦች በነዋሪው ግንባር እና በኢንተርፕራይዝ ግንባር የተከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎችን በቦታው በመገኘት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ምልከታ አድርጓል።

‎በምልከታው ወቅት በእያንዳንዱ ግንባር የተያዙ ዕቅዶች እስከአሁን የተፈጸሙ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በሂደት ላይ ያሉ ሥራዎች ተመልክተዋል።

‎በፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የሚገኙ የብልጽግና አባላት የሥራ ተነሳሽነት የአገልግሎት አሰጣጥ የተጠያቂነት ሥርዓት እና በተቋማት ውስጥ የሚከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች ተመልክተዋል።

‎በፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር በብልጽግና ቤተሰቦች የተያዙ የልማትና የማህበራዊ ተሳትፎ ተግባራት እንዲሁም ቤተሰቦች ና አባለት በተለያዩ የልማት ሥራዎች የሚያደርጉት ተሳትፎ ተገምግሟል።

‎የከተማው ነዋሪ በልማት በንጽህና በማህበራዊ ጉዳዮችና በሌሎች የከተማ አቀፍ ተግባራት የሚያደርገው ተሳትፎ ምልከታ አድርጓል

‎ የሕዝብ ተሳትፎን በበለጠ ማጠናከር የልማት ሥራዎችን በጋራ ማስፈጸምና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይም የተከናወኑ ተግባራት ድጋፍና ክትትል ተደርጓል።

‎በኢንተርፕራይዝ ግንባር የተከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምርታማነት ማሳደግ ጥረቶች ተመልክተዋል።

‎ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በከተማው በ2019 በጀት ዓመት እስከአሁን የተከናወኑ ሥራዎችን በቦታው በመመልከት የሥራ አፈጻጸም ሂደቱን ገምግሟል።

በሀላባ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተገመገመ‎‎ነሀሴ 22/2018 በሀላባ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አ...
28/08/2026

በሀላባ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተገመገመ

‎ነሀሴ 22/2018 በሀላባ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተገምግመዋል።

‎በግምገማ የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ዋና ሀላፊ ተወካይ፣ የመምሪያ ምክትልና የፕላን ዘርፍ ሀላፊና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሀብስሳ መሀመድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀርበው በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

‎በግምገማው ወቅትም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት የከተማ መሬት ውስን ሀብት በመሆኑ በሕጋዊ መንገድ በማስተዳደርና መምራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎በተለይም ህብረተሰብ በልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ አቢይና ቴክኒክ ኮሚቴዎች ሕገ-ወጥነቱን ለመከላከል በልዩ ትኩረት መስራት ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

‎ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት የልየታ ስራን ማጠናከር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና ትክክለኛ መረጃ መያዝ ይገባል ብለዋል።

‎ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግ እድገታቸው እንዲፋጠን ህገ ወጥነትን መከላከል ቀዳሚ ተግባር አድርጎ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎እስካሁን እየተሰሩ ያሉ በድክመት የታዩ ስራዎች በመቅረፍ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠል መሬት ላይ የሚስተዋሉ ህገወጥና ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል ይገባል ብለዋል።

‎በግምገማው በዋናነት በኢንቨስትመንት፣ በኢንተርፕራይዝ፣ በህብረት ስራ ማህበራት፣ በተለያዩ አካላት የተፈጸሙ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታዎች፣ ከምትክ ቦታ ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ህገወጥነት፣ በጥቅም ትስስርና በሌሎች ምክንያቶች መሬቶች ላይ እስከአሁን የተሰሩ ስራዎች በሰፊው ተመልክቶ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎በመድረኩም የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የቤት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አቶ ንጉሴ አቢሶ፣ የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች፣ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አባላት ተገኝተዋል።

 #‎አፈልጉኝ‎‎ተፈላጊ ህፃን ፦አሊፍ በረኩ ሀ/አወል‎ዕድሜ፦ 3 ዓመት ‎አድረሻ፦በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ዞቤቻሜ ቀበሌ ሆስፒታል ሰፈር ስሆን በዛሬው ዕለት ነሃሴ 22/2018 ዓ.ም ከ...
28/08/2026

#‎አፈልጉኝ

‎ተፈላጊ ህፃን ፦አሊፍ በረኩ ሀ/አወል
‎ዕድሜ፦ 3 ዓመት

‎አድረሻ፦በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ዞቤቻሜ ቀበሌ ሆስፒታል ሰፈር ስሆን በዛሬው ዕለት ነሃሴ 22/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ ከሚትኖርበት ቤት በማውጣት እስካሆን ወደ ቤት አልተመለሰም ።

‎ህፃኑ ከቤት ከወጣ ሰዓት ጀምሮ እናትና አባቷ እንዲሁም ቤተሰቦቿ ተጨንቀው በመፈለግ ላይ ይገኛሉ ።

ምንአልባት ህፃኑን የያ ወይም ያለበትን የሚያውቅ ከለ ከዚህ በታች በለው ስልክ ቁጥር ደውሎ ቢያሰውቀን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቹ ሼር ላይክ በማለት ይተባበሩን።

‎ስልክ ቁ፦0912454321 ወይም 0926454396

Address

Addis Abeba To Arbamichi Main Rod
Addis Ababa
HALABAZONE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share