Bekalu Wondimu

Bekalu Wondimu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bekalu Wondimu, Government Website, Ethiopian, Addis Ababa.

15/04/2025

ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ 10 የሕይወት መርሆዎች!

1."እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር!"

ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።

2."አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው!"

የጎደለህ ምንድን ነው?
☞ያለህስ ምንድን ነው?
☞ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3."እራስህን ሁን!"

በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤

4."ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር!"

አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5.የውሸት ደስታን አትፈልግ!"

በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤

6."ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅንሁን!"

ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤

7."መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው!"

ብዙሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው።

8. "የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን!"

ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

9."መልካም አስብ መልካም ተናገር!"

10."ለምን እንደምትኖር እወቅ!"

15/04/2025

🌎 ለጠቅላላ ዕውቀት 🌎 ያንብቡት

1- የአለማችን ትልቋ ሀገር ሩስያ ስትሆን 17.09 ሚሊየን km2 የሆነ የቆዳ ስፋት አላት።

2- በአለማችን ላይ በርሀማዋ ሀገር ሊቢያ ስትሆን ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 99% የሚሆነው በረሀማነት የሚፈረጅ ነው:።

3- በአለማችን ላይ ምንም አይነት ወንዝ የሌላት ሀገር ሳውድ አረቢያ ነች።

4- ለሴቶች የመምረጥ መብትን ቀድማ የሰጠች ሀገር ኒውዝላድ ነች።

5- አሜሪካ በአለማችን ላይ ብዙ ክርሰቲያኖች የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 245.9 ሚሊየን የሚሆኑት ክርሰቲያኖች ናቸው።

6- ብዙ የሆነ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ህዝብ ያላት ሀገር ኢንዶኔዢያ ስትሆን ከ209 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊሞች ናቸው።

7- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀይቅ ብዛት ያላት ሀገር ካናዳ ስትሆን ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ሀይቆች ሲኖራት ይህም በአለማችን ላይ ካሉት የሀይቆች ብዛት 60% ይሸፍናል።

8- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኤል ሳልቫዶር ስትሆን በአማካኝ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 55.5% የሚሆኑት ግድያ ይፈፀምባቸዋል።

9- በሀገሯ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴቶች ቁጥር ያላት ሀገር ሩዋንዳ ስትሆን በፓርላማዋ ካሉት ጠቅላላ መቀመጫዎ ውስጥ 56.3% (50/80) የሚሆነው የተያዘው በሴቶች ነው።

10- ዴንማርክ በአለማችን ላይ አነስተኛ የሆነ የሙስና ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ናት።
በየቀኑ አስተማሪ መረጃዎችን እናደርሳችሁዋለን
ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው ሼር ያድርጉ
እውእውነታ ሚዲያ\Reality Media

15/04/2025

እድሜያችሁ አሁንም በ20ዎቹ እና 30ዎቹ ውስጥ ከሆነ፣ እባካችሁ ይህንን አንብቡ...

1. በየቀኑ ማታ 9:00 ሰዓት (3 ሰዓት) ተኝታችሁ ጠዋት 4:00 ሰዓት (10 ሰዓት) የመንቃት ልምድ አዳብሩ። የ7 ሰዓት እንቅልፍ በትኩረት የተሞላ ቀን እንዲኖራችሁ ያደርጋል።

2. በጠዋት ለ100 ደቂቃዎች የማንበብ፣ የመጻፍ እና የተረዳችሁትን የማዋሃድ (𝙞𝙣𝙩𝙚𝙧𝙣𝙖𝙡𝙞𝙯𝙚) ልምድ ይኑራችሁ።

3. ገንዘብ ከሌላችሁ፣ አካላዊ ቅርጻችሁ ጥሩ ካልሆነ ወይም ህይወታችሁ የተመሰቃቀለ ከሆነ የፍቅር ግንኙነት ከመጀመር ተቆጠቡ። መጀመሪያ ህይወታችሁን በሥርዓት አደራጁ።

4. ርካሽ/ቀላል የዶፓሚን ፍላጎትን (𝙘𝙝𝙚𝙖𝙥 𝙙𝙤𝙥𝙖𝙢𝙞𝙣𝙚) የመከተል ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ። ይህ ወደ ድብርት እና አሳዛኝ ህይወት የሚወስድ በጣም ቀላሉ መንገድ ነው።

5. በህይወታችሁ ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር፣ በሳምንት 7 ቀናት ስፖርት ስሩ። ለአዕምሮ ጤናችሁ ታላቅ ህክምና ነው።

6. በየጠዋቱ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብን የዘወትር ልማድ አድርጉት። ሰውነታችሁን ይፈውሳል እና ለአዲስ ቀን ያዘጋጃችኋል።

7. ኢንተርኔትን የገቢ ምንጫችሁ ለማድረግ እንዳያመልጣችሁ። በእንቅልፍ ሰዓታችሁ እንኳ ገንዘብ ለመስራት የሚያስችሉ ማለቂያ የሌላቸው እድሎች አሉ።

8. ለህይወታችሁ 100% ሃላፊነት ውሰዱ። ለችግሮቻችሁ ወላጆቻችሁን፣ ሁኔታዎችን ወይም ማንንም አታማርሩ/አትውቀሱ።

9. ጥሩ የአለባበስ ስብስብ (𝙬𝙖𝙧𝙙𝙧𝙤𝙗𝙚) ላይ ገንዘብ አውጡበት፣ ጥሩ መዓዛ ይኑራችሁ እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ተማሩ። ይህ የስኬት መጠናችሁን በ94% ያሳድገዋል።

10. ከተፈጥሮ ጋር ተወዳጁ። በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች የእግር ጉዞ አድርጉ። በፀሐይ ብርሃን የእግር ጉዞ ማድረግ አዕምሯችሁን ያጠራል፣ ስሜታችሁን ያነቃቃል እንዲሁም የፈጠራ ችሎታችሁን ያዳብራል።

11. ታላቅ ምኞት ካላቸው፣ ተነሳሽነት ካላቸው እና ህይወታቸውን ለማሻሻል ከፍተኛ ፍላጎት ካላቸው ሰዎች ጋር ጊዜ አሳልፉ። የእርስዎ የጓደኞች ክበብ በአብዛኛው ስለ ገንዘብ፣ ንግድ እና ስኬት መወያየት አለበት።

12. ከምትመገቡት ምግብ 70% ፕሮቲን እንዲሆን አድርጉ። ይህ ሰውነታችሁን እና አዕምሯችሁን ለመጠገን፣ ለመገንባት እና ለማጠንከር ይረዳል።

13. ክህሎት ከትምህርት ውጤታችሁ በ10 እጥፍ የበለጠ ዋጋ እንዳለው ተገንዘቡ። የገንዘብ ችግሮቻችሁን ለመፍታት የሚረዳ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ክህሎት ተማሩ።

14. የብልግና ምስሎችን/ፊልሞችን መመልከት እና ራስን በራስ የማርካት ልምድ ህይወታችሁን ለማበላሸት ቀላሉ መንገድና የስኬታችሁ ትልቁ ገዳይ መሆኑን ለመገንዘብ ብልህ ሁኑ።

15. የራሳቸውን ፍላጎት ከእናንተ ፍላጎት በላይ ከሚያስቀድሙ ሰዎች ራቁ፤ በህይወታችሁ ያላቸው ሚና ምንም ይሁን ምን። እነሱ ለስኬታችሁ ትልቁ እንቅፋት ናቸው።

ከወደዳችሁት ይህንን ገጽ ተከተሉ።

ተዋነይ - Tewanay

የስርቆት ዜዴ ተጠንቀቁ ‼️================ሌባው ፏ ፈሽ ብሎ ገዢ መስሎ ከች ይልልሀል። ከዛ የሚገዛውን ዕቃ ዋጋ ጠይቆ ይሰማል ፤ ተከራክሮም ሆነ ሳይከራከር በዋጋው ይስማማል። ከዛ...
12/04/2023

የስርቆት ዜዴ ተጠንቀቁ ‼️
================

ሌባው ፏ ፈሽ ብሎ ገዢ መስሎ ከች ይልልሀል። ከዛ የሚገዛውን ዕቃ ዋጋ ጠይቆ ይሰማል ፤ ተከራክሮም ሆነ ሳይከራከር በዋጋው ይስማማል። ከዛ የሚፈልገውን ብዛት፣ ዓይነት፣ ቀለም ምናምን ይናገርና ፤ "ግዢውን ከመፈጸሜ በፊት ለአለቃዬ ደውዬ መናገር አለብኝ"... ይልና ስልኩን አውጥቶ ይሞክራል። ከዛ "ስልኬ ዘጋብኝ" ወይ ደግሞ "ስልኬ ብር የለውም" or ሌላም ምክንያት ያቀርብና "ያንተን ስጠኝና ለአለቃዬ ልደውለት" ይላል። አንተ ዕቃውን መሸጡ ላይ ትኩረት ስላደረክ እሺ በማለት ስልክህን ትሰጠዋለህ።

ከዛ ይኼ ሌባ ወድያው ስልክህን ተቀብሎ የሆነ ቁጥር ጽፎ እንደሚደውል በማስመሰል የራሱን ስልክ ቁጥር ይጽፍና CBE ብሎ ሴቭ ያደርጋል። አለቃዬ አላነሳልኝም ወይ ደግሞ ስልኩ አልሰራልኝም ምናምን ይልህና ስልክህን ይመልስልሀል።

ከዛማ ፥ አንተ ላይ በሚፈጥረው ከፍ ያለ ዋቴ የሌለ ይሰካክስህና ፥ "በቃ እንደውም የባንክ ቁጥርህን ፃፍልኝና አለቃዬ ብሩን በአካውንትህ ሲያስገባ ዕቃውን እወስደዋለሁ" ይልሀል። አንተ ሀሳብህ ዕቃውን መሸጥ ስለሆነ ፤ እሺ ትለውና የባንክ አካውንትህን ትነግረዋለህ። ሌባው ካንተ ከተለየ ካንድ ከ10 ደቂቃ በኋላ CBE ተብሎ ሴቭ በተደረገው ቁጥር ከባንክ እንደተላከ አስመስሎ ዕቃው የሚያወጣውን ያህል ገንዘብ ሜሴጅ ይልክልሃል። ከዛ በደቂቃዎች ልዩነት ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ ሰው ይልክና "ገንዘቡ ደረሰህ ኣ?" ምናምን ብሎህ ፤ በጣም አጠዳድፎህ ዕቃውን በመኪና ወይ በባጃጅ ጭኖ ላሽ ይላል!

ድንገት ባንነህ text በተደረገልህ ቁጥር መልሰህ ስትደውል ሲም ካርዱ አይሰራም 😭

ከዚህ ዓይነት ሌብነት ራሳችሁን ጠብቁ! ተጠንቀቁ! ጽሑፉ ጠቃሚ ከሆነ ለሌሎችም አድርጉ
በንግድ አለም ያላችሁ ሰዎች ይኼን የስርቆት ዜዴ ተጠንቀቁ... [በተለያዩ ከተማዎች እየተሰማ ነውና...]

07/04/2023

የቦንጋ የት/ኮሌጅ ለቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ድጋፍ አደረገ።
ቦንጋ ፣ መጋቢት 26/2015 (ቦትኮ) የቦንጋ የት/ኮሌጅ ለቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ድጋፍ አድርጓል።
ለቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት የኮሌጁ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የጥርና የካቲት ወር ደመወዛቸው 322,005 ብር ገቢ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሌጁ ያሳዉቃል።

06/04/2023
05/04/2023

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bekalu Wondimu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bekalu Wondimu:

Share