Gumer View

Directions Website

Gumer View city developer project arekit city developer project

በዚህ ተፈጥሮ ሰላም ካልተሰማህ መቼም ሰላምህን አታገኝም  #ጉራጌ  #አረቅጥ
20/10/2026

በዚህ ተፈጥሮ ሰላም ካልተሰማህ መቼም ሰላምህን አታገኝም
#ጉራጌ #አረቅጥ

ተፈላጊ ሳሮን  ኢሳኮር  ትባላለች ከምትኖርበት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አረቅጥ ከተማ ጥቅምት 4/02/2019 ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም ብንፈልጋትም እስካሁን ልናገኛት አልቻልንም። ያያ...
19/10/2026

ተፈላጊ ሳሮን ኢሳኮር ትባላለች ከምትኖርበት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አረቅጥ ከተማ ጥቅምት 4/02/2019 ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም ብንፈልጋትም እስካሁን ልናገኛት አልቻልንም። ያያችዋት ያለችበት የምታቁ እንድትጠቁሙን ለሁላችሁም በአክብሮት እንጠይቃለን።
ፈላጊ ቤተሰብ :-
ስልክ ቁጥር
0916043639
0916020200

ወንድማችን  አፍያ አምደብርሀን እንተማመንብሀለን በርግጠኝነት  በEtfc  ትወዳደራለህ እስከዚያ ራስህን በደንብ አዘጋጅ አንዴ መድረኩን ካገኘህ እስከ አለማቀፍ ውድድር መሸጋገሪያ ድልድይ ስለ...
19/08/2026

ወንድማችን አፍያ አምደብርሀን እንተማመንብሀለን በርግጠኝነት በEtfc ትወዳደራለህ እስከዚያ ራስህን በደንብ አዘጋጅ አንዴ መድረኩን ካገኘህ እስከ አለማቀፍ ውድድር መሸጋገሪያ ድልድይ ስለሚሆንህ አንዴ ሪንግ ውስጥ እስክትገባ ትግል ስለሚፈልግ ሁላችንም ከጎንህ ነን
ሁላችሁም ይሄን ፖስት like share comment
አርጋቹ አቅም ስጡት በርታልን

ከታገዘ ጉራጌን ከዚያም አልፎ ኢትዮፒያን ማስጠራት ይችላልወጣት ሳቦም ዳርፈታ አምደ_ብርሃን – በስፖርት ትጋትና በወጣቱ ልማት የሚታይ ተስፋ። ይህ የምትመለከቱት ወጣት ሳቦም ዳርፈታ አምደ ብ...
21/07/2026

ከታገዘ ጉራጌን ከዚያም አልፎ ኢትዮፒያን ማስጠራት ይችላል
ወጣት ሳቦም ዳርፈታ አምደ_ብርሃን – በስፖርት ትጋትና በወጣቱ ልማት የሚታይ ተስፋ።

ይህ የምትመለከቱት ወጣት ሳቦም ዳርፈታ አምደ ብርሃን ሲሆን ተወልዶ ያደገው በጉራጌ ዞን ከሚገኙ መዋቅሮች በአንዱ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ ለአካል ብቃትና ለስፖርት ያለውን ፍቅር በተግባር በማሳየት ራሱን ከማብቃት ባሻገር በአካባቢው ያሉ ወጣቶችንም በስፖርታዊ ሥነ-ምግባር፣ በዲሲፕሊን እና በአካል ብቃት እያነጸ ይገኛል።

በፋይት ስፖርት ዘርፍ እንደ ተወዳዳሪ፣ እንዲሁም እንደ ዳኛና አሰልጣኝ የሚያገለግል ሲሆን፣ በዘርፉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና የሙያ ማረጋገጫ (Certificate) አግኝቷል። ይህም በስፖርቱ ውስጥ በብቃት እንዲያገለግልና ትውልድ የሚገነባ ስራ እንዲሰራ አስችሎታል።

በአሁኑ ወቅት በወላይታ ሶዶ በሚሰጠው የሞይታይ (Muay Thai) ስልጠና እየተሳተፈ ይገኛል። ይህ ስልጠና በኢትዮጵያ የሞይታይ ስፖርትን ለመጀመሪያ ጊዜ ካስተዋወቁት አሰልጣኝ ማስተር ተሾመ እንሰማ አዘጋጅነት የሚሰጥ በመሆኑ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የስፖርት እውቀትና ልምድ እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል።

ወጣት ሳቦም ዳርፈታ ከዚህ ስልጠና የሚያገኘውን እውቀትና ልምድ በመጠቀም ራሱን ለተወዳዳሪነት በተሻለ ሁኔታ ለማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን፣ የሚያሰለጥናቸውን ልጆችና ወጣቶች በዘመናዊ የስልጠና ዘዴዎች በማብቃት በቀጣይ ውድድሮች ተፎካካሪ እንዲሆኑ ጠንክሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው።

ስፖርት የአካል ብቃትን ከማሳደግ በላይ ዲሲፕሊን፣ መተባበር፣ ራስን መቆጣጠር፣ መሪነት እና ጽናትን የሚያጎለብት አስፈላጊ መሳሪያ ነው። በተለይም እንደ ሞይታይ እና ሌሎች የፋይት ስፖርቶች ወጣቶችን ከጎጂ ልማዶች በማራቅ ወደ ጤናማ የኑሮ ዘይቤ እንዲመሩ ያግዛሉ።

እንደ ወጣት ሳቦም ዳርፈታ ያሉ ወጣቶች በግላቸው የሚያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደ ማህበረሰባቸው በማምጣት ሌሎችን ሲያሰለጥኑ የስፖርት ባህል እንዲስፋፋ፣ ተተኪ ተወዳዳሪዎች እንዲፈጠሩ እና አካባቢያቸው በስፖርት ዘርፍ እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

ይህ ትጋት ለግል ስኬት ብቻ ሳይሆን ለጉራጌ ዞን፣ ለክልሉ እና ለኢትዮጵያ የስፖርት እድገት የሚያበረክት ጠቃሚ እርምጃ ነው። ወጣት ሳቦም ዳርፈታ የጀመረው ጉዞ ወጣቶች በትጋት፣ በሥነ-ምግባር እና በቀጣይነት ሲሰሩ በአገር ደረጃ የሚያስመሰግን ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው። via Ashenafi Bireda Abeza

09/07/2026

Celebrating my 7th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

በጉመር ቪው ስም አንድ ክለብ ለሚያቋቁም ሰው ስፖንሰር እናደርጋለን Tame Gebre
09/07/2026

በጉመር ቪው ስም አንድ ክለብ ለሚያቋቁም ሰው ስፖንሰር እናደርጋለን Tame Gebre

25/06/2026

ጫትም መወገድ አለበት

25/06/2026

እጅግ በርካታ ሰዎች
በውስጥ በከተማችን በመንግስት
የታገደው አረቄ በድብቅ እየተሸጠ እንደሚገኝ ጠቁመውናል የመንግስት አካላት ድርጊቱ አውቀው እያለፉት ነው ተብሏል

01/06/2026

“ንጉሡ አይበድሉ፣ በዙሪያቸው ያሉ ግፈኞች እንጂ…” የዘመናችን የፖለቲካ ድንቁርና

በየማህበራዊ ሚዲያውና በየቡና ቤቱ ስታወሩ ጣልቃ እየገቡ፣ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድማ የለውጥ መሪ ናቸው፤ ሀገሪቱን በእኩል ማልማት ይፈልጋሉ፤ ችግሩ ግን ማህበረሰቡን የሚበድሉት ከበታች ያሉ ሹማምንቶች ናቸው” የሚሉ ሰዎችን ገጥሟችሁ ያውቃል?

እነዚህ ሰዎች ሲበዛ ራስ ወዳዶች ከመሆናቸውም በላይ፣ ፖለቲካዊ የውሸት ትረካ (Narrative) የፈጠረባቸው እውሮች ናቸው።ሀገር ለመምራት ይረዳኛል ያለውን ርዕዮተ-ዓለም መርጦ፣ ፖሊሲውን ነድፎ፣ ካቢኔውንና መዋቅሩን የዘረጋው ራሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑን ማመን አይፈልጉም።

ሕዝብ በግፍ ቢፈናቀል፣ ቢራብ፣ ንብረቱ ቢዘረፍ፣ ፍትህ አጥቶ ቢንገላታ፣ ቢገ ደልና ቢሰደድ ለእነሱ ምናቸውም አይደለም። ሕዝብ “ተበድለናል” ብሎ የፍትህ ጥያቄ ሲያነሳ፣ የእነሱ ምላሽ ሁልጊዜም “አብይ ብቻውን ምን ያድርግ?” የሚል የተለመደ ሰበብ ነው።

አብይና ካቢኔው በትብብር ሕዝብን እየቦጠቦጡ መሆኑን ስትነግራቸው፣ እነሱ የሚመልሱት አንድና አንድ ዜማ ብቻ ነው፦ “ኮሪደር ማማሩን፣ ከተማው መለወጡን አታይም እንዴ?” ይሉሃል።እነዚህ ሰዎች ከኮሪደር ውጪ ሌላ እውነታ ማየት የማይችሉ፣ ከከተማ አስፓልት ጀርባ ያለውን የሕዝብ ዕንባ የማይታያቸው እውነተኛ ጨለምተኞች ናቸው።

ለመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ማሽን በየሚዲያውና በየመድረኩ የሐሰት ምስክርነት የሚሰጡት፣ የሕዝብን ስቃይ በሽንገላ ለመሸፈን የሚሞክሩት እነዚህ የጥቅምና የዕውር ድንብሩ ደጋፊዎች ናቸው።

ሀገር በኮሪደር ልማት ብቻ አትገነባም፤ የሀገር መሠረቱ የዜጎች ሰላም፣ ፍትህና መከበር ነው!

ተደመርን ነው የምትሉኝ🙄?እና አዲስ አበባ ፊንፊኔ ትሁን ብላችሁ ወሰናችሁ ?ጉራጌ ክልል ነው 😁😁😁
21/05/2026

ተደመርን ነው የምትሉኝ🙄?
እና አዲስ አበባ ፊንፊኔ ትሁን ብላችሁ ወሰናችሁ ?
ጉራጌ ክልል ነው 😁😁😁

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gumer View posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category