Agegnehu Teshager

Agegnehu Teshager Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Agegnehu Teshager, Government Official, Addis Ababa.

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

ኢትዮጵያ በታላቅ ውሳኔ ላይ ፤  የማይበገር ህዝብ ድምፁን እየሰጠ ነው!ዛሬ ግንቦት 24 የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እየሰራ ነው። በከተማም በገጠርም ጎህ ሳይቀድ ከየቤቱ በነቂስ የወጣው ህዝባችን...
01/06/2026

ኢትዮጵያ በታላቅ ውሳኔ ላይ ፤ የማይበገር ህዝብ ድምፁን እየሰጠ ነው!

ዛሬ ግንቦት 24 የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እየሰራ ነው። በከተማም በገጠርም ጎህ ሳይቀድ ከየቤቱ በነቂስ የወጣው ህዝባችን፣ የምርጫ ጣቢያዎች በራቸውን ከመክፈታቸው በፊት በረዣዥም ሰልፎች ተሰልፎ፣ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማስከበር ያለውን ቁርጠኝነት በአደባባይ አስመስክሯል። ይህ ህዝብ ተረድቷል። የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የተቀናጁ የሚዲያ ዘመቻዎች ሊያናውጡት የማይችሉትን ፅኑ አቋም አንግቧል።

አዎ ህዝባችን ለሀገሩ ቀጣይ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምዕራፍ ወሳኝ የሆነውን ድምፁን ለመስጠት በጋለ ስሜት እየተሳተፈ ነው። እያንዳንዱ ድምፅ የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይህ ታላቅ የዴሞክራሲ ልምምድ ሀገርን ከማፅናት ባለፈ ለመላው የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ተስፋና ተምሳሌት እንደሚሆን እናምናለን።

እኔም በጎንደር ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ተገኝቼ የዜግነት ግዴታዬን ተወጥቻለሁ። በህዝባችን ንቁ ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት እጅግ ኩራት ይሰማኛል። ይህ የዴሞክራሲ ልምምዳችን የኢትዮጵያን አንድነትና ብልጽግና የሚያረጋግጥበት ታሪካዊ ወቅት ነው።

#ኢትዮጵያእየመረጠችነው!
#በህዝብድምጽሀገርይጸናል!
#በምርጫብቻ!

26/05/2026

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቸ
እንኳን ለ 1447ኛው ኢድ አል አደሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ!!

ኢድ ሙባረክ🙏🙏

26/05/2026
26/05/2026
ሰላም ክቡራትና ከቡራን የፌዴሬሽን ምክርቤት በወልቃይት ጉዳይ  ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና በቅንብር ፎቶ የተሰራ መሆኑን እየገለፅኩ ይህን የተሳሳ...
20/05/2026

ሰላም ክቡራትና ከቡራን የፌዴሬሽን ምክርቤት በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና በቅንብር ፎቶ የተሰራ መሆኑን እየገለፅኩ ይህን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩት እነማን እንደሆኑ አጣርተን ለህግ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን

አገኘሁ ተሻገር

16/05/2026
11/05/2026
04/05/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agegnehu Teshager posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share