የካ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን _ Yeka woreda 1 communication

የካ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን _ Yeka woreda 1 communication የመንግስት የህዝብ ግንኙነት

17/08/2026

የመዲናችን አዲስ አበባ ያሳለፍነው ሳምንት ዐበይት ተግባራት:-

በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ  ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ያሳደግን ሲሆን፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በቀን 525...
16/08/2026

በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ያሳደግን ሲሆን፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማምረት አቅማችን አሁን ላይ ወደ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ ችለናል፡፡

በተለይ ዛሬ የመረቅናቸዉ ደግሞ የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር አለም የደረሰበትን እጅግ የረቀቁ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዘላቂነት ፈርቀዳጅ ሚና አላቸዉ።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ አዲስ ፥ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ በማድረግ እና አገልግሎትን የሚያሳልጡ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ከዛሬ አልፎ ለትውልድ የምታሸጋግር ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

16/08/2026

ለነዋሪዎቻችን ተጠቃሚነት በተከታታይነት ያልተቋረጠና አዳዲስ ብስራት ማብሰር ያስቻለን ፈጠሪ አምላክ የተመሰገ ይሁን !!

የንፁህ መጠጥ ዉሃ እና የዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ምርቃት ላይ በመገኘት ያስተላለፍኩት መልዕክት

ዛሬ እሁድን የት ለማሳለፍ አስበዋል?ምርጫዎ በቀበና ካደረጉ ይደሰታሉ። ቤተሰብዎን ይዘው ይምጡ! ለእርሶ የቀረበ ልዩ የመዝናኛ አማራጭ ነው !ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
16/08/2026

ዛሬ እሁድን የት ለማሳለፍ አስበዋል?
ምርጫዎ በቀበና ካደረጉ ይደሰታሉ። ቤተሰብዎን ይዘው ይምጡ! ለእርሶ የቀረበ ልዩ የመዝናኛ አማራጭ ነው !

ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

እንኳን ደስ አለን!!ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ  ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት  እና በቀን 20 ሺህ  ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክ...
16/08/2026

እንኳን ደስ አለን!!

ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን አልምተን በከተማችን ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ አድርሰናል፡፡

በተመሳሳይ ለረጅም ዘመን በከተማችን የሚገኙ ወንዞች በፍሳሽም፤ በደረቅ ቆሻሻም ሲበከሉ ቆይተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የፍሳሽ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት በ2009 ዓ .ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ችለናል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎቻችንን ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞቻችንን ብክለት የሚቀንሱ፣ የአካባቢ ጥበቃችንን የሚያጠናክሩ ናቸው። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ውብ፣ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ ዘመናዊና ለትውልድ የምትመች ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ላደረጋችሁ፤ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠን ያለውን የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ከሁሉ በላይ ዘላቂ ኑሯቸውን ሲመሩበት የነበረውን መሬት ለዚህ ታላቅ ልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች እና ለፕሮጀክቱ ስኬት ሌት ተቀን ያለእረፍት የተጉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

16/08/2026

በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ያስመዘገብናቸው ተጨባጭ ለውጦች

Jijjiiramoota qabatamaa dhiyeessii bishaan dhugaatii qulqulluu fi dhabamsiisa dhangala'aa ammaayyaan galmeessine

አስተማማኝ ጥራት!ተመጣጣኝ ዋጋ!የየካ ወረዳ 01 የሰንበት ገበያ
16/08/2026

አስተማማኝ ጥራት!
ተመጣጣኝ ዋጋ!
የየካ ወረዳ 01 የሰንበት ገበያ

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ!የካ ወረዳ 01 አስተዳደር የሰንበት ገበያ በኢዩሱስ 41 እና በኬላ መዳረሻዎች በጥራት የቀረቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።🛒🌾  የየካ ወረዳ...
16/08/2026

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ!

የካ ወረዳ 01 አስተዳደር የሰንበት ገበያ በኢዩሱስ 41 እና በኬላ መዳረሻዎች በጥራት የቀረቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

🛒🌾 የየካ ወረዳ 01 ሞዴል የሰንበት ገበያዎች የነዋሪውን ሸክም እያቃለሉ ይገኛሉ።
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ወቅታዊውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል በማሰብ ያዘጋጃቸው ሞዴል የሰንበት ገበያዎች፣ ለኅብረተሰቡ አቅም ያገናዘበና አስተማማኝ የግብይት አማራጭ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

መንግሥት የሕዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የጀመረውን ጥረት ወደ ታች በማውረድ፣ ወረዳው እነዚህን የሰንበት ገበያዎች በስፋት በማደራጀት ነዋሪዎች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

(የካ ወረዳ 01 ኮሙኒኬሽን - አዲስ አበባ)
(ነሀሴ 10/2018 ዓ.ም)

👇👇👇በሁሉም የሚዲያ አማራጮች እንዲያገኙን ከታች የተቀመጠዉን ሊንክ ይጫኑ
https://heylink.me/Woreda01com/

ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባየመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት ተዋህደው አዲስ አበባን ምቹ የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርገዋታል...
15/08/2026

ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ

የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት ተዋህደው አዲስ አበባን ምቹ የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርገዋታል፡፡

የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ፣ በ2018 ዓ.ም በርካታ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችንና ስብሰባዎችን በደመቀ ሁኔታ አስተናግዳለች።

ከተማዋ ከተለያዩ የዓለም ማዕዘናት የመጡ መሪዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቢዝነስ ሰዎችንና ባለሙያዎችን በክብር ተቀብላ፣ በብቃት በማስተናገድ በሰላም ሸኝታለች።

ይህ ስኬት ከተማዋ ያላትን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ከማሳየቱም በላይ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበቻቸውን ፈጣን የእድገትና የመዘመን ጉዞ ለዓለም ያበሰረ አጋጣሚ ሆኗል።

አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ለነበሩት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች አዲስ ፊትና ድምቀት ይዛ እንድትቀርብ ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል በከተማዋ የተተገበረው መጠነ-ሰፊ የኮሪደር ልማት ግንባታ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ሰፋፊና ንፁህ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መስመሮች፣ ዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና ውብ የአረንጓዴ ስፍራዎች የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።

ይህ የመሰረተ ልማት መዘመን በኮንፈረንሱ ወቅት የመጡ እንግዶች በከተማዋ ውስጥ ያለምንም እንግልትና በከፍተኛ ደህንነት እንዲንቀሳቀሱ ከመርዳቱም በላይ፣ ለአዲስ አበባ ዘመናዊና ማራኪ ውበትን አላብሷታል።

የትራፊክ ፍሰቱን በማቃለልና የእይታ ውበትን በመጨመር ረገድ የኮሪደር ልማቱ ለኮንፈረንስ ቱሪዝሙ ትልቅ አጋዥ ሆኗል።

ከተማዋ በቅርብ ጊዜያት የገነባቻቸው ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችና ዘመናዊ ፓርኮች ለስብሰባ የመጡ እንግዶች የትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ተመራጭ ስፍራዎች ሆነዋል።

እንደ አንድነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ እና ሌሎች አዳዲስ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች እንግዶችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

እነዚህ ስፍራዎች ከተማዋ ከመደበኛ የስብሰባ አዳራሾች ባለፈ፣ እንግዶች የሚዝናኑባቸው፣ ተፈጥሮን የሚያደንቁባቸውና የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በአንድ ቦታ የሚያዩባቸው የቱሪዝም ማዕከላት ሆነው አገልግለዋል።

ይህም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከባህላዊና ከተፈጥሮ ቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር የከተማዋን የቱሪዝም ገቢና ዝና ከፍ አድርጎታል።

ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ታዋቂ የሆቴል ብራንዶች በአዲስ አበባ መበራከታቸው ከተማዋ በ2018 ዓ.ም ላስመዘገበችው ስኬት ሌላኛው ምሰሶ ነው።

ሆቴሎቹ እንግዶችን በከፍተኛ የደህንነት፣ የፅዳትና የቅልጥፍና ደረጃ ከማስተናገዳቸውም በላይ፣ የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ የእንግዳ ተቀባይነት ጨዋነት ከዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር አዋህደው አቅርበዋል።

የስብሰባ አዳራሾች ዝግጁነት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችና የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖር ሆቴሎቹ ለኮንፈረንሶቹ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አስችሏቸዋል።

ከተማዋ በአንድ ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ እንግዶችን በምቾት የማሳደርና የማስተናገድ ሙሉ ብቃት እንዳላት በተግባር የታየበት ሆኗል።

በአጠቃላይ አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ያስተናገደቻቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ከተማዋ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላትን የማይተካ ሚና ዳግም ያረጋገጡ ነበሩ። ከተማዋ እንግዶቿን ተቀብላ፣ በከፍተኛ ፍቅር አስተናግዳ፣ በሰላም በመሸኘት ያሳየችው ብቃት የሚደነቅ ነው።

ይህ ስኬት ከተማዋ የገነባቻቸው ዘመናዊ የኮሪደር መሰረተ ልማቶች፣ ማራኪ የወንዝ ዳርቻዎችና የቱሪዝም ፓርኮች እንዲሁም የላቀ የሆቴሎች ዝግጁነት ጥምር ውጤት ነው።

አዲስ አበባ አሁን ላይ ስብሰባዎች የሚካሄዱባት ከተማ ብቻ ሳትሆን፣ የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት የተዋሃዱባት፣ አስተማማኝና ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል መሆኗን ለዓለም አስመስክራለች።

ይህ ተሞክሮ ወደፊትም ከተማዋ ይበልጥ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እንድትስብና እንድታስተናግድ በር የሚከፍት ነው።

ተመራቂ የፖሊስ  መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ  በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ  መኮንኖችን መርቀናል።  ተመራቂዎቹ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር  በጠ...
15/08/2026

ተመራቂ የፖሊስ መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ!

ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖችን መርቀናል።

ተመራቂዎቹ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር በጠንካራ ዲሲፕሊን ስልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ፤ በአካልና በመንፈስ ጠንክረው የወጡ በመሆናቸው በፖሊስ መኮንንነት ማዕረግ ተመርቀዋል።
ተመራቂዎች በቆይታችሁ ያገኛችሁት እውቀት ለላቀ ፖሊሳዊ ስብዕና የሚያበቃችሁ እንደመሆኑ ወደ ስራ ስትሰማሩም ያለአድልዎና ልዩነት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ በሰብዓዊነትና በክብር፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምታገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251913583624

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የካ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን _ Yeka woreda 1 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share