Commercial Nominees PLC

Commercial Nominees PLC Commercial Nominees P.L.C (CN) was established in 1965 by the then Commercial Bank of Ethiopia.

Undertaking Outsourced Business Services on behalf of our customers.

27/08/2026

የቡሄ ትውስታ

26/08/2026

ንግድዎን ለማሳደግ የተሻለ ቦታ እየፈለጉ ነው?
እንግዲያውስ ወደ እኛ ይምጡ
ኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽንና ኢንተርፕረነርሺፕ ሀብ
 ለካፌ እና ሬስቶራንት
 ለፋርማሲ እና ሱቆች
 ለቢሮዎች እና ለሲኒማ
 ለጂምና ለሱፐርማርኬት
 ለባንክና ኢንሹራንስ
ለሬዲዮ ስቱዲዮ እና ለስልጠና ማዕከል በኪራይ አቅርበንልዎታል
ይምጡና ለሥራዎ አመቺ የሆነውን ቦታ መርጠው ይከራዩ
ሰፊ እና ምቹ የመኪና ማቆሚያ ያለው
ደህንነቱ የተጠበቀ የንግድ ማዕከል
አድራሻ፡- ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ
ፈጥነው ይደውሉ፡ በነጻ የስልክ መስመር 6630 ወይም በ 011-1564350

24/08/2026
ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 “የልጆቻችን ኢትዮጵያ” የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቆይታ  ምዕራፍ ሁለት
22/08/2026

ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 “የልጆቻችን ኢትዮጵያ” የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቆይታ ምዕራፍ ሁለት

Commercial Nominees PLC (CN) is an Ethiopian company with a long-st...

ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 “የልጆቻችን ኢትዮጵያ” የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቆይታ ምዕራፍ አንድ
21/08/2026

ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 “የልጆቻችን ኢትዮጵያ” የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቆይታ ምዕራፍ አንድ

Commercial Nominees PLC (CN) is an Ethiopian multi-service company ...

አራዳ ሌግዠሪ ሞል፦ በአዲስ አበባ መሀል የሚገነባው የንግድና መዝናኛ ማዕከል የግንባታ ሂደት ተጎበኘ****አዲስ አበባ (ሲኤን) ፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት በአቶ አቤ ሳኖ የተመራ ...
20/08/2026

አራዳ ሌግዠሪ ሞል፦ በአዲስ አበባ መሀል የሚገነባው የንግድና መዝናኛ ማዕከል የግንባታ ሂደት ተጎበኘ
****

አዲስ አበባ (ሲኤን) ፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት በአቶ አቤ ሳኖ የተመራ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን፣ በአዲስ አበባ ከተማ እያደገ ከሚገኘው የኮሪደር ልማት ጋር ተናብቦ እየተገነባ የሚገኘውን የ“አራዳ ሌግዠሪ ሞል” የግንባታ ሂደት ጎበኘ።

ከታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ከአራዳ ፓርክ እና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተቀናጅቶ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፤ የከተማዋን ውበት የሚያሳድግ፣ የንግድ እንቅስቃሴዋን የሚያነቃቃ እና ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ዘመናዊ የንግድ ማዕከል እንደሚሆን ተገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፤ ባንኩ ለፕሮጀክቱ የሚያደርገውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በማጠናከር፣ ሞሉ በተያዘለት ጥራት እና የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ እያደረገ ያለውን ጥረት በቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል።

በጠቅላላው 115 ሺህ ካሬ ሜትር የህንፃ ስፋት ያለው አራዳ ሌግዠሪ ሞል በውስጡ፦

ዓለም አቀፍ የፋሽን ብራንዶችን እና ሱፐር ማርኬቶችን

የሲኒማ እና የጂምናዚየም ማዕከላትን

የባንክ፣ የውጭ ምንዛሪ እና የክሊኒክ አገልግሎቶችን

የሬስቶራንት፣ ካፌ እና የዱቲ ፍሪ (Duty-Free) መሸጫዎችን በአንድ ስፍራ ያካተተ ሁለንተናዊ የንግድና የመዝናኛ ማዕከል ይሆናል።

የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ  በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት በጀት ዓመት ዕቅድ የውይይት መድረክ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
19/08/2026

የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት በጀት ዓመት ዕቅድ የውይይት መድረክ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

In 2018 EFY, Commercial Nominees PLC (CN) generated more than ETB 6...

ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ-----------------ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ..ማህ እና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽ...
18/08/2026

ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
-----------------
ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ..ማህ እና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተለያዩ የሦስተኛ አገልግሎቶችን፣ የኢንጂነሪንግ፣ የመሰረተ ልማት እና የቢዝነስ አገልግሎቶችን በትብብር እና በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ እንደገለጹት ኮሜርሺያል ኖሚኒስ በሪል ስቴት ዘርፍ ለመሰማራት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር በኮንስትራክሽን እና የማማከር መስኮች በጋራ ለመስራት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሜርሺያል ኖሚኒስ የረጅም ጊዜ ደንበኛ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የመግባቢያ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ኃብት እና እውቀት በጋራ በመጠቀም ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበርክቱ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱ ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ሲያቀርባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ለማጠናከር እና በአዳዲስ የቢዝነስ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በኮንስትራክሽን እና ማማከር አገልግሎቶች መስክ ከኮሜርሺያል ኖሚኒስ ጋር በቀጣይ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በራዲሰን ብሉ ሆቴል በተከናወናው የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት መሰረት ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የንብረት እና ኃብት አስተዳደር፣ የሰው ሀይል አቅርቦት፣ ስልጠና፣ በባቡር ውስጥ ሚቀርቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን፣ የካሳ ክፍያዎችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለኮርፖሬሽኑ ለማቅረብ የሚያስችለው ነው፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያሉ የኢንጂነሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎችን፣ የአዋጭነት ጥናቶች፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኒክ ስልጠናዎችን፣ የማማከር ሥራዎችን፣ ኃብትን በጋራ በመጠቀም የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ጣቢያ ማቋቋም እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጥገና ሥራዎችን እና ሌሎች ተግባራትን በጋራ እና በትብብር ለማከናወን ያስችለዋል፡፡

ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የጥበቃ አገልግሎት በማቅረብ እና የካሳ ክፍያዎችን በመፈጸም ከኢትዮጵያ ምድር ባር ኮርፖሬሽን ጋር እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Follow our Social media pages:
Facebook: https://web.facebook.com/cnplcnew
Telegram: https://t.me/+XIeQ65489xw1NmNk
Instagram: https://www.instagram.com/p/DTKgLryDPbm/?utm_source=ig_web_copy_link&igsh=NTc4MTIwNjQ2YQ==
Linked in: https://www.linkedin.com/.../admin/page-posts/published/
Youtube:https://www.youtube.com/
Tiktok:https://www.tiktok.com/?lang=en
x:https://x.com/Cnominees

Address

Bole Behind Dembel City Center, Seid Yassin Building
Addis Ababa
251

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Commercial Nominees PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Commercial Nominees PLC:

Shortcuts

Share