Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 75/2014 የተቋቋመ ነው።
(1)

04/08/2026
ከ14ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለን፤ ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ የበኩላችንን ድርሻ ተወጥተናል።ሐምሌ 27 /2018  አ/አ/ስ/ፀ/ሙ/ኮኢትዮጵያ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል 8ኛው አረንጓዴ ...
03/08/2026

ከ14ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለን፤ ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ የበኩላችንን ድርሻ ተወጥተናል።

ሐምሌ 27 /2018 አ/አ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ

ኢትዮጵያ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል 8ኛው አረንጓዴ አሻራ የማኖር ዘመቻ ላይ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ተክላለች።

ኮሚሽናችን ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች ጋር በጋራ ከ14ሺህ በላይ ችግኞች በመትከል ለሀገራዊ ስኬት የበኩሉን ተወጥቷል።

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”

የኮሚሽኑ መረጃና የጥቆማ መስመሮች፦📞

በነፃ የስልክ መስመር፦ 8887

📧 ኢሜል፦ [email protected]

👉 ቴሌግራም፦ https://t.me/aaethics2015

👉 ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/.ababa.ethic?_t=ZM-8tqgdUzDifn&_r=1

👉 ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=KYuB2L8_rwYnrtQK

03/08/2026

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት መልእክት

ተስፋን እንትከል!

የአዲስ አበባና የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባየአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን...
03/08/2026

የአዲስ አበባና የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለጹት ሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ እያካሄደች በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዘንድሮው የትኩረት አቅጣጫ ለምግብነት የሚያገለግሉ የችግኝ ዝርያዎችን በመምረጥ መትከል፣ ከጽደቃቸው ባለፈም ተንከባክቦ ለውጤት ማብቃት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የመርሃ-ግብሩ መካሄድ የሰላም፣ የእድገትና የህብረ-ብሄራዊ ተስፋን በማለምለም «ችግኝ በመትከል ችግርን መንቀል» የሚለውን ታላቅ ዓላማ ያነገበ መሆኑን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው ሀገራችን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የላቀ ድልና ተስፋ ማስመዝገቧን ገልጸዋል። አያይዘውም በኮሚሽኑ ደረጃ 14 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን በመጥቀስ፣ ለዚህ አገራዊና ተቋማዊ ስራ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አካባቢ በመገኘት ከ4 ሺህ በላይ ችግኞችን መትከላቸው ተገልጿል።

“ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”

የነገው አሻራችን የፅናት፣ የሕዝባዊ አገልጋይነት እና የላቀ ስነ-ምግባራችን መግለጫ ነው! -  እኛ ዝግጁ ነን!የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና መ...
02/08/2026

የነገው አሻራችን የፅናት፣ የሕዝባዊ አገልጋይነት እና የላቀ ስነ-ምግባራችን መግለጫ ነው! - እኛ ዝግጁ ነን!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና መላው ሠራተኞች ነገ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ታሪካዊውን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለመፈጸም በከፍተኛ ዝግጅት እና ተነሳሽነት ላይ እንገኛለን።

ለልጅ ልጅ የሚሻገር ጽዱ እና በሙስና ያልተበላሸ ተቋማዊ እሴት እንደምንገነባው ሁሉ አካባቢያችንን በችግኝ በማልማት ለተተኪው ትውልድ ለም እና አረንጓዴ ሀገር የማስረከብ የዜግነትና እና ሙያዊ አደራችንን እንወጣለን።

"በፅኑ ስነ-ምግባር፣ አረንጓዴ ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ እየታተረች ያለች ሀገር — ኢትዮጵያ!" 🌳⚖️

የሙያ ስነምግባርና ከሙስና የፀዳ ህሊና!ሙያ  ከመተዳደርያነት ባለፈ ለወገንና ለሀገር ትልቅ ውለታ የሚዋልበት እንጂ የግል ጥቅምን ማሳደጃ ሊሆን አይገባም።የሙያ ስነምግባር  ጥቅምን ለማግኘት ...
01/08/2026

የሙያ ስነምግባርና ከሙስና የፀዳ ህሊና!

ሙያ ከመተዳደርያነት ባለፈ ለወገንና ለሀገር ትልቅ ውለታ የሚዋልበት እንጂ የግል ጥቅምን ማሳደጃ ሊሆን አይገባም።

የሙያ ስነምግባር ጥቅምን ለማግኘት ህዝብን ማንገላታት ሳይሆን ከሙስና በጠራ ህሊና ሀቀኛ አገልግሎትን መስጠት ነው።እውነተኛ የሙያ ስነምግባር የሚለካው በተጣለብን ኃላፊነት ልክ በምናሳየው አገልጋይነት መንፈስ ነው።

ሙስና አገርን የሚያደኸይ እምነትን የሚያጠፋ እና የሙያ ክብርን የሚያረክስ በመሆኑ በአገልጋይነት ስሜት ራስን ዝቅ አድርጎ፣ ህዝብን በማክበር፣ የሰውን እንባ በማበስ፣ የተሰጠንን አደራ በንጹህ ልብ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በመቆጠብ በታማኝነት ለማገልገል በቁርጠኝነት መነሳት ይገባል።

ዛሬ በየተሰማራንበት የስራ መስክ በፍቅር ለማገልገል፣ ኃላፊነታችንን በታማኝነት ለመወጣት እና ሙስናን በጋራ ለመዋጋት ቃል እንግባ!

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”

የኮሚሽኑ መረጃና የጥቆማ መስመሮች፦

📞 በነፃ የስልክ መስመር፦ 8887

📧 ኢሜል፦ [email protected]

👉 ቴሌግራም፦ https://t.me/aaethics2015

👉 ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/.ababa.ethic?_t=ZM-8tqgdUzDifn&_r=1

👉 ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=KYuB2L8_rwYnrtQK

በኪቦርድ ስር የተደበቀው ጥቁር ሀብት፤ ሙስናን በተግባር የተጋፈጡት የፀረ ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ***************በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን ማስ...
31/07/2026

በኪቦርድ ስር የተደበቀው ጥቁር ሀብት፤ ሙስናን በተግባር የተጋፈጡት የፀረ ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ
***************
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን ማስወገድ ለበርካታ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች አሁንም ትልቅ ፈተና እንደሆነ ይነገራል። በተለይም በታችኛው የመንግስት እርከን አካባቢ አገልግሎትን በጥቅም ከመለወጥ ፍላጎት ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ስውር ሙከራዎች የስራ አካባቢን ከማበላሸታቸውም በላይ የህዝብን እምነት የሚያሸረሽሩ ናቸው።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የተከሰተው አጋጣሚ ግን ለሙስና አሰራር እጅ ላለመስጠት የተደረገ ግልጽ የማንቂያ ደወል እና የጽናት አርአያ ሆኖ ይገኛል።

የወረዳው የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ አቶ ኢቢሳ ረፊሳ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን ወደ ቢሯቸው በገቡበት ወቅት ኮምፒውተራቸውን አብርተው ኪቦርዳቸውን ከፍ ሲያደርጉ ያልጠበቁትን ነገር ተመለከቱ፦ ከኪቦርዱ ስር የተሸሸገ 5,000 ብር!

ይህ አጋጣሚ ለብዙዎች ፈተና ሊሆን ቢችልም ለአቶ ኢቢሳ ግን የተጣለባቸውን የህዝብና የመንግስት አደራ የማስከበር መነሻ ሆነ። ጉዳዩን ወዲያውኑ ለስራ ባልደረቦቻቸው በመጠየቅ ማጣራት የጀመሩ ሲሆን፣ የገንዘቡ ባለቤት አለመገኘቱን ሲረዱም ለአመራሮች አስረክበዋል።

የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድኑ በወረዳው የሚሰሩ አሰራሮችን ግልጽና ከብልሹ አሰራር የጸዱ ለማድረግ የሚያደርገውን ቁርጠኛ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ እና ተቋሙን ወዳልተፈለገ አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት ሆን ተብሎ የተሸረበ ስውር ሴራ እንደነበር ይገመታል።

ለተወሰነ ጊዜ “በስህተት ነው ያስቀመጥኩት” የሚል ወይም የገንዘቡ ባለቤት ነኝ ባል የሚመጣ ቢሆንም ምንም አይነት ጥያቄ ሳይቀርብ በመቅረቱ ገንዘቡ በህጋዊ ደረሰኝ ለወረዳው ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ገቢ ሆኖ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ አጋጣሚ ዛሬም ቢሆን ለአገልግሎት ሰጪውም ሆነ ለተቀባዩ ማህበረሰብ ትልቅ አስተምህሮ አለው። አቶ ኢቢሳ እንደገለፁት “ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራችን አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል አገልግሎትን በጥቅም ለማግኘት የሚፈልጉ አካላትም ከእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል።”

ይህ ክስተት የሚያሳየን፣ የታማኝነትና የጽናት አርአያ የሆኑ አመራሮችና ሰራተኞች ባሉበት ተቋም ውስጥ፣ ስውር የሙስና እጆች ተቀባይነት እንደሌላቸውና መጨረሻቸውም ውድቀት መሆኑን ነው።

ምንጩ :- የወረዳው በኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው።

ግብር ማጭበርበር እና ሙስና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች! በትክክል የምንከፍለው ግብር ለሀገር ልማት የሚውል ትልቅ የህዝብ ሃብት ነው። ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች፣ ጥራት ያላቸው ሆስፒታሎች፣...
28/07/2026

ግብር ማጭበርበር እና ሙስና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች!

በትክክል የምንከፍለው ግብር ለሀገር ልማት የሚውል ትልቅ የህዝብ ሃብት ነው። ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች፣ ጥራት ያላቸው ሆስፒታሎች፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና ሰፋፊ መንገዶች እውን ሊሆኑ የሚችሉት ግብርን በታማኝነት ስንከፍል ነው።

በተቃራኒው፣ በሀሰተኛ ሰነዶች ማጭበርበር እና ደረሰኝ ባለመቁረጥ ግብርን ለመሸሽ መሞከር ሀገርን የመስረቅ ያህል ነው። ይህ ድርጊት ተራ ስርቆት ሳይሆን የሀገርን የልማት የሚያደናቅፍ እና ኢኮኖሚውን የሚያሽመደምድ ስር የሰደደ የሙስና አካል ነው።

ሙስና እና የግብር ማጭበርበር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ሁለቱም የህዝብን ሀብት በመዝረፍ የጥቂቶችን ኪስ ያደልባሉ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ግን ለችግርና ለኋላ ቀርነት ይዳርጋሉ።

ሰነድ በማጭበርበር ግብርን መሸሽ የሀገርን የጀርባ አጥንት መስበር ነው። ታማኝ ግብር ከፋይ መሆን የሀገር ልማት አጋር መሆን ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የከፈልነው ግብር ለታለመለት ዓላማ መዋሉን በንቃት መከታተልና ሙስናን በጋራ መታገል የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ሊሆን ይገባል።

ወደብ አልባነት እና የሙስና ስውር ትስስር**************ለአንድ ሉአላዊት ሀገር ወደብ ማጣት የኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ ፈተና ብቻ አይደለም፤ ሀገራዊ ክብርን የሚፈታተን፣ ለሙስና እና ለህ...
25/07/2026

ወደብ አልባነት እና የሙስና ስውር ትስስር
**************
ለአንድ ሉአላዊት ሀገር ወደብ ማጣት የኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ ፈተና ብቻ አይደለም፤ ሀገራዊ ክብርን የሚፈታተን፣ ለሙስና እና ለህገ-ወጥ አሰራሮች ሰፊ በር የሚከፍት የጥቁር ገበያና የደላሎች መናኸሪያ ነው።

ለእኛ ለኢትዮጵያውያንም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የባህር በር መብታችንን ህጋዊ ባልሆነና ባልተገባ ሁኔታ መነጠቃችን የሀገራችንን የንግድ መስመር ለውጭና ለሀገር ውስጥ መካከለኛ አካላት (ደላሎች) ጥገኝነት አሳልፎ ሰጥቶታል።

ይህም ሰንሰለቱ የተንዛዛ አሰራር ሀገርን ለጉቦ እና ለ "እጅ መንሻ " መረብ አሳልፎ በመስጠት የሀገርን ኢኮኖሚ ያዳክማል፡፡

ወጪ እና ገቢ ዕቃዎች በሰው ሀገር ወደብ ላይ በዘገዩ ቁጥር የሚከፈለው ከፍተኛ የዶላር ቅጣት (Demurrage) አስመጪ እና ላኪዎቻችንን ለከፍተኛ ስጋትና ለውጭ ኃይሎች መጫወቻነት ይዳርጋቸዋል።

ይህንን ኪሳራ ለማስቀረት በሚደረግ መሯሯጥም የሙስናና ያልተገባ ጥቅም አሳዳጆችን ኪስ ለማደለብ ይገደዳሉ ። የራስ ወደብ መኖር ግን ይህንን የባርነት ቀንበር ይሰብረዋል! አጠቃላይ የቁጥጥር ሥርዓቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ የቢሮክራሲ መወሳሰብንና የኮንትሮባንድ ንግድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅበር የሙስና ዕድሎችን በከፍተኛ ደረጃ ያጠባል።

የባህር በር ለሀገራችን የኢኮኖሚ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ ግልጽነት የሰፈነበትና ከሙስና የጠራ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለመገንባት የሚረዳ ትልቅ መሣሪያ ነው። ስለሆነም፣ ይህንን ታሪካዊ መብታችንን የማስከበርና የወደብ ባለቤት የመሆን ብሔራዊ ኃላፊነታችንን ተገንዝበን፣ ለተግባራዊነቱ በጋራ ልንቆም ይገባል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251948747575

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና:

Shortcuts

Share