24/07/2026
ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ሚዲያ አሳሳች መረጃዎች እንዳይሠራጩ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ
++++++++++++++++
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የውይይቱ የመጀመሪያ ደረጃዎች ስሜት የተሞላባቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አሳሳች መረጃዎች እንዳይሠራጩ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር (ፕ/ር) መስፍን አርዓያ የምክክሩን ሂደት አስመልክቶ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት፤ ተሳታፊዎች በውይይቱ ያለ ምንም ፍራቻና ገደብ ስሜታቸውን ሲገልጹ ነው ሂደቱ አካታች የሚሆነው።
ያልተባሉና ያልተሄደባቸው ጉዳዮች በስሜት እንዳይወጡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ለዚህም ተሳታፊዎቹ ስልክ ይዘው እንደማይገቡ ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ ተሳታፊዎቹም ተስማምተውበት እንደተደረገ አስረድተዋል።
#ፕሬስመረጃማጣሪያ #ሀገራዊምክክር