Kolfe Woreda 09 Communication

Kolfe Woreda 09 Communication Govermen organizashion

የኮልፌ ቀራኒዮ  እና የፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የፊርማ ስነ_ ስርአት ተካሔደ፡፡ ግንቦት 18ቀን 2015 ዓ.ምሁለቱ ክፍለ...
26/05/2023

የኮልፌ ቀራኒዮ እና የፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የፊርማ ስነ_ ስርአት ተካሔደ፡፡

ግንቦት 18ቀን 2015 ዓ.ም

ሁለቱ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ማለትም በከተማ ጽዳት፤ በመሰረተ ልማት እና በመሰል ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት የሁለቱም ክ/ከተሞች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፣ ዋና ስራ አስኪያጆች እና የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የፊርማ ስነ ስርአት ተካሒዷል።

አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ክፍለ ከተሞቹ አጎራባች በመሆናቸው የጋራ አገልግሎት መስጠት ስለሚገባ ሕዝቡን የሚያስተሳስር ስራ በልማት ፤በፅዳትና በሌሎች ስራዎች ላይ እንደ አስተዳደር ከእናንተ ጋር ተቀናጅትን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የፉሪ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሸት ግዛው በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት ያለንን አቅም በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ያጋራ አላማችንን ማሳካት አለብን ለዚህም በቀጣይ ዕቅዶቻችን ውስጥ አካተን በልማትና በሌሎች ዘርፎች አብረን ተባብረን አንሰራለን ያሉ ሲሆን እናንተም ይህን ተረድታችሁ እዚህ በምጣታችሁ በክፍለ ከተማው ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

አመራርነት ሁሉንም ህዝብ በእኩልበማገልገል ያሉትን ችግር በመካፈል መፍትሄ ለመስጠት ነው ያሉት አቶ አዱኛ ማሩ የሸገር ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ዛሬ የጀመርነውን ስራ በከተማ ደረጃ ማስፋት አለብን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማና ክፍለ ከተማዎቿ ጋር በአንድነት ለጋራ እድገት መስራት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ አስተዳደሮቹ በጋራ በሚሰሩባቸው ተግባራት ላይ ገለጻ በማድረግ የተወያዩ ሲሆን ከመድረኩም በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡን አስተባብረን በማሳተፍ በአንድነት ለማደግ እንሠራለን ሲሉም ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰተዋል፡፡

"በጎ ፈቃደኝነት ለዘላቂ አብሮነት መሰረት ነው።"የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የ2015 ዓ/ም የበጎ ፈቃድ የእውቅናና ምስጋና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈቻ ፕሮግራም በክፍለከተማው ተካሄ...
25/05/2023

"በጎ ፈቃደኝነት ለዘላቂ አብሮነት መሰረት ነው።"
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የ2015 ዓ/ም የበጎ ፈቃድ የእውቅናና ምስጋና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈቻ ፕሮግራም በክፍለከተማው ተካሄደ።
በ2015 ዓ/ም በክፍለ ከተማው ስር ካሉ 10 ወረዳዎች የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ፅ/ቤት 2ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ ውጤቱ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።

"በአብሮነት የህብረተሰቡን ጤና እንጠብቃለን"። በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎች ውይይት እያደረጉ ነው።ግንቦት 17/2015በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ /ቤት አዘጋጅነት የጤና ባለሙያዎ...
25/05/2023

"በአብሮነት የህብረተሰቡን ጤና እንጠብቃለን"። በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎች ውይይት እያደረጉ ነው።

ግንቦት 17/2015

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ /ቤት አዘጋጅነት የጤና ባለሙያዎች፣ የፋርማሲ ባለሙያዎች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት በሀገራዊ ጉዳዮች በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን የሚዳስስ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተወያዩቹ በ5 ዓመት የለውጥ ጊዜያትን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦችን አስመልክቶ መወያየት ጀምረዋል።

ለውይይቱ መነሻ “በአብሮነት የህብረተሰብን ጤና እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቧል።

አንዲትም የኢባዱረህማን መስጂድ ህጋዊ ይዞታ እንደማይነካ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አረጋገጡ።የክፍለ ከተማው አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተ...
25/05/2023

አንዲትም የኢባዱረህማን መስጂድ ህጋዊ ይዞታ እንደማይነካ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አረጋገጡ።

የክፍለ ከተማው አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስልምና ጉዳዮች ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የነበረ በክፍለ ከተማው ወረዳ 05 የሚገኘው ኢባዱረህማን መስጂድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ስራ አሰፈፃሚ ሰብሳቢ ኡስታዝ ሀሽም ሀምዛ
መስጂዱ እድሜ ጠገብና ታሪካዊ እንደሆነና በትላንቶናው እለት የተከናወነው ተግባር ተገቢ አለመሆኑን አስተዳደሩም መረጃውን አጥርቶ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ሲሆን ይዞታውን እንዲያስጠብቅ ጠይዋል።

አስተዳደሩ ተቀራርቦ በጉዳዮ ለይ በመወያየቱ ያመስግኑት ሰብሳቢው ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ ተቀራርበው እደሚሰሩም አስታውቀዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልፀው ክስተቱ በአስተዳዳሩ እውቅና እንደሌለውና ተቋማዊ አሰራርን ያልጠበቀ ሲሆን አስተዳዳሩ መረጃውን አጥርቶ ተጠያቂ እንደሚያደርግና አንዲትም የመስጂዱ ህጋዊ አካል እንደማይነካ አረጋግጠዋል።

አስተዳዳሩ ከመጂሊሱ ጋር በማህበራዊና የልማት ስራዎች ላይ ተቀራርቦ እየሰራ መሆንና ይህንንም እንደሚያስቀጥል አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ህዝበ ሙስሊሙ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ማህበረሰቡም ትክክለኛ መረጃ ከአስተዳዳሩ እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በስራ ዕድል ፈጠራና የመስሪያ ቦታዎች  ዙሪያ የኦዲት ሥራ የተሄደበት የስራ አፈፃፀም በአጠቃላይ አመራሩ ተገመገመ።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨በኮልፌ ቀራንዮ  ክ/ከተማ ወረዳ 09...
25/05/2023

በስራ ዕድል ፈጠራና የመስሪያ ቦታዎች ዙሪያ የኦዲት ሥራ የተሄደበት የስራ አፈፃፀም በአጠቃላይ አመራሩ ተገመገመ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በ10 ወራት ጊዜያት ውስጥ በተከናወኑ በስራ ዕድል ፈጠራና የመስሪያ ቦታዎች አስተዳደር ዙሪያ የኦዲት ሥራ በከተማው አስተዳደር የተዋቀረ አጣሪ ኮሚቴ አማካኝነት ዛሬም የማጥራት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዛሬው እለት በአጠቃላይ አመራሩ ውይይት ተደርጎበታል በውይይቱ ወቅት የስራ እድል ፈጠራ ኦዲት መነሻ በማድረግ መስተካከል የሚገባቸውን በቁርጠኝነት መስራት ስለሚገባቸውና በቀጣይ ለውጤታማነት በትኩረት መሰራት ስለሚገባ ጉዳዮች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተደረጎባቸዋል።
በመጨረሻ የኦዲት ስራው የመስክ ምልከታ እየተካሄደ በመሆኑ ስራ እድል የተፈጠረላቸውን ማረጋገጥ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ተቀምጧል።
በተጨማሪ በቀጣይ 5ወር የስራ እድል ፈጠራ ስራ እቅድ ላይ ኦረንቴሽን መስጠት ተችሎአል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2015 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግ...
25/05/2023

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2015 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 17/2015 ዓ.ም

በወረዳ 2 ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ባለ 6 ክፍል የመኖሪያ ቤት አፍርሶ ለመገንባት በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብርን የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባባሪያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል።

ክፍለ ከተማው በክረምት በጎ ፍቃድ 14 መርሀ ግብሮች ለማከናወን አቅዷል።

የተገልጋዩን ፍላጎት በማሟላት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠ ትዝግጁ ነን የኮልፌ ክ/ከተማ  ወረዳ 09 ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ለአገልግሎት አሰጣጥን በእዉቀት ላይ በተመሰረተ እና አገልግሎት አሰ...
24/05/2023

የተገልጋዩን ፍላጎት በማሟላት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠ ትዝግጁ ነን የኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት
ለአገልግሎት አሰጣጥን በእዉቀት ላይ በተመሰረተ እና አገልግሎት አሰጣጡን በጥናት በማረጋገጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በታች በላይ እና በስታንዳርዱ ዙሪያ ያሉትን ከማሻሻል ጀምሮ ሞደል ተቋም ለመፍጠር ለአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋነት በተመለከት ለፅ/ቤት ሀላፊ እና ለስራ ሂደት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ በውይይቱ ለቀጣይ አገልግሎት አሰጣጥ ለይ ለሚመጣ ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ።
ሲሉ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጄ በአፅንኦት ተናገሩ።

በክፍለ ከተማው የቆሙ ህንፃዎች ግንባታቸው የሚያልቅበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሔደ፡፡ኮልፌ ቀራኒዮ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015ዓ.ምበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር   የተቋቋመ ቡድን የቆሙ ...
24/05/2023

በክፍለ ከተማው የቆሙ ህንፃዎች ግንባታቸው የሚያልቅበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሔደ፡፡

ኮልፌ ቀራኒዮ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመ ቡድን የቆሙ ህንፃዎችና የባዶ መሬት ልየታ ግኝት ለአመራሩ ማወያየቱ ይታወሳላ። ይህንን ተከትሎ በዛሬው እለት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለቤት የተገኘላቸው የቆሙ ሆንፃዎች ባለቤቶቻቻው ጋር ውይይት አድርገዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የቆሙ ህንፃዎች ግንባታቸው የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓ መግባባት መደረሱንና የአስተዳደሩ እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በልየታውም በክፍለ ከተማው አስሩ ወረዳዎች 494 የቆሙ ህንፃዎች የተለዮ ሲሆን 393 የባለቤትነት መረጃ ያቀረቡ መሆናቸው በጥናቱ መጠቆሙ ይታወሳል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር 170 ሺህ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ  ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራትን ለማከናወን  አቅደናል ሲል የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተ...
24/05/2023

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር 170 ሺህ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራትን ለማከናወን አቅደናል ሲል የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015 ዓ.ም

ጽ/ቤቱ በነገው ዕለት የበጋ በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር የመዝጊያ እንዲሁም የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት እንደሚያካሂድ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ እንደተናገሩት በነገው ዕለት የተለያዩ ማህበረሰ የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የበጋ በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር የመዝጊያ እንዲሁም የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት እንደሚያካሂድ ገልፀዋል፡፡

በበጋው የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በክፍለ ከተማችን በርካታ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ የቤት ዕድሳት፣የማዕድ ማጋራት፣የደም ልገሳ፣የችግኝ ተከላ እና ቁፋሮ፣የማጠናከሪያ ትምህር፣የትራፊክ ማስተናበርን ጨምሮ በ14 መርሀ ግብሮች ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

እነዚህን በጎ ተግባራት በክረምቱ በጎ ፍቃድ መርሀ ግብርም 170 ሺህ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ ከ 125 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በዕውቀት እና በጉልበት ከ 100 ሺህ በላይ ህብረተሰብ የሚጠቀምበት ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት አቅደናል ሲሉ ገልፀዋል።

ሀላፊዋ አክለውም በነገው እለት በበጋው የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር ተሳታፊ የነበሩትን በጎ ፍቃደኞች እንዲሁም ባለሀብቶች እናመሰግናለን ሲሉ አስታውቀዋ።

የኤች አይ ቪ ኤድስ  ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ  በመምጣቱ  ስርጭቱን ለመቀነስ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል  ሲል የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት  አስታወቀ፡፡ኮልፌ ...
24/05/2023

የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ስርጭቱን ለመቀነስ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲል የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከሁሉም ወረዳ ለተውጣጡ ለብሎክ አደረጃጀት ማህበራዊ ዘርፍ አመራሮች በ ኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መባባስ እና መከላከያ መንገዶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ሂሩት ባንጃው የስልጠናው አላማ ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በመዘናጋቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የሚያዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመራቸው የመድረኩ የተገኑ አካላት ለማህበረሰባችን ቅርብ በመሆናቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው መሰጠቱ ጥሩ ነው በሽታው አሳሳቢ ደረጃ በመድረሱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቀጣይነት ቢኖረው ሲሉ ገልፀው በተለያዩ አከባቢዎች ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ድርጊቶችን መንግስት ቁጥጥር ቢያደርግ እንዲሁም ኮንዶም በተገቢው መንገድ አግባብነት ባላቸው ቦታዎች ላይ ስርጭት ቢደረግ ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

በዴንቨር በነበረን ቆይታ በጋራ ለመስራት የለየናቸው ዘርፎች ወደ ተግባር በሚለወጡባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከንቲባ ማይክል ሃንኮክ፣ ከከተማው አመራሮች እና የንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋር ፍሬ...
24/05/2023

በዴንቨር በነበረን ቆይታ በጋራ ለመስራት የለየናቸው ዘርፎች ወደ ተግባር በሚለወጡባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከንቲባ ማይክል ሃንኮክ፣ ከከተማው አመራሮች እና የንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

ለዴንቨር ከተማ የንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች እና አባላት ስለ ከተማችን ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገንላቸዎል። ኃላፊዎቹ አዲስ አበባን ውብ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎችን አድንቀው ለከተማ እድገት የግሉን ዘርፍ ከመንግስት ጋር በቅንጅት መስራት ስላለው ትልቅ ፋይዳ ልምዳቸዉን አካፍለውናል።

በከተማችን አዲስ አበባ ብዛት ያለው የተማረ ወጣት እንደመኖሩ በዴንቨር ያሉ ተቋማትን በማስተባበር ለወጣቱ የስራ እድል የሚፈጥሩ አገልግሎቶቻቸውን ወደ አዲስ አበባ ማምጣትና ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም በተለዩ ዘርፎች ላይ በቅርበት መስራት ለሁለቱም ከተሞች በሚያስገኘው ፋይዳ ዙሪያ በዝርዝር ተወያይተናል።

በዴንቨር ከተማ ከአቀባበል ጀምሮ ለቆይታችን ስኬታማነት፣ በተለይም ለተደረገልን ልዩ መስተንግዶ ሁሉ ከንቲባ ሃንኮክን እና ባልደረቦቻቸውን በድጋሚ ላመሰግን እወዳለሁ።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ስለ የቤት ግብር ማሻሻያ ይሕን ያውቁ ኖሯል?የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደገ የመጣውን የህዝብ ፍላጎት እና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አ...
24/05/2023

ስለ የቤት ግብር ማሻሻያ ይሕን ያውቁ ኖሯል?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደገ የመጣውን የህዝብ ፍላጎት እና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አስፈልጓል፡፡ በዚህም ወሳኝ ከሆኑ የገቢ አይነቶች መካከል የቤት ግብር (የንብረት) ግብር አንዱ ነው፡፡

ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ለማሳደግ የተጻፉ ጽሁፎች እንደሚያስረዱት እያደገ የመጣውን የህዝብ ፍላጎት እና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የገቢ ምንጮች ማስፋት እና የክፍያ ተመንን ወቅታዊ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ በመሆኑም የግብር ከፋዩን አቅም ባገናዘበ የመሰረተ ልማት ጥያቄን የመለሰ እና የገንዘብ መግዛት አቅምን ከግምት ውስጥ ያስገባ የግብር ማሻሻያ ውሳኔ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

እስካሁን ድረስ አገልግሎት ላይ የነበረው የከተማ ቦታ ኪራይ እና የከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 አንቀጽ 6/2 መሰረት የሚጣለው የቤት ግብር መጠን የቤቱ ኪራይ ግምት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እንዲሁም የቤት ኪራይ ግምት በዋናነት የቤቱ አይነት፣ ስፋትና አገልግሎት እንዲሁም ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ደረጃ መሰረት የሚለያይ መሆኑን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህ መሰረት ዝቅተኛው በካሬ 148 ከፍተኛው 632 ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡

የክፍያ ጫናን ለማቅለል ሲባል የዚህ አመት ክፍያ ያልከፈሉ የቤት ግብር ከፋዮች በአንቀጽ 1 በጥናቱ በተለየው የአንድ ሜትር ካሬ ቤት ስፋት ወርሃዊ ኪራይ ግምት መጠንን ለመኖሪያ ቤት 50 በመቶ፣ ለመስሪያ ቤት ደግሞ 75 በመቶ ላይ ብቻ ግብሩን በማስላት እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን በቀጣይ በጀት አመት ለመኖሪያ ቤት እና ለመስሪያ ቤት የሚያገለግሉ ቤቶች በአንቀጽ 1 የቤት ኪራይ ግምት መሰረት ግብሩ እየተሰላ የሚከፈልበት ይሆናል፡፡ በዚህ አመት እንዲከፍሉ የሚጠበቁት የዚህ አመት ክፍያ ያልከፈሉ ብቻ ይሆናል፡፡

የቤት ግብር እንደሚከተለው ይሰላል
የቤት ግብር = የቤቱ ስፋት x ወርሃዊ ኪራይ ተመን x 12 x የግብር ምጣኔ
ለምሳሌ በአንደኛ ደረጃ ቦታ የሚገኝ እና 54 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ለመኖሪያ አገልግሎት የሚያገለግል ኮንዶሚኒየም ያለው ግብር ከፋይ እንደሚከተለው ይሰላል፡፡
የቤት ግብር = 54 x (247 x 12) x የግብር ምጣኔ ≈ 7097.52 በዚህ አመት የሚወስደው የግምቱ 50 በመቶ በመሆኑ የቤት ኪራይ ግምቱ ወደ 80 028 ዝቅ ይላል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በዚህ አመት የሚከፍለው የቤት ግብር ≈ 3769.26 ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለሁሉም ደረጃዎች 102 ብር ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913662589

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Woreda 09 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share