በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን, Government Organization, 4 kilo behind ministry of Education, Addis Ababa.

24/08/2026
24/08/2026
የግል ጤና ተቋማት ለምገባ ማዕከላት የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ነው።--------------------------ነሐሴ 14 2018 ...
20/08/2026

የግል ጤና ተቋማት ለምገባ ማዕከላት የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ነው።
--------------------------
ነሐሴ 14 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የግል ጤና ተቋማትን በማስተባበር በክፍለ ከተማው ወረዳ 9 እና 10 ለሚገኙ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠቃሚዎች ነፃ የህክምና ድጋፍ አድርጓል።
የቂርቆስ ምግብ መድሃኒት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ ሲ/ር አለምነሽ አባይ በዚህ ነፃ ህክምና የበጎ አድራጎት ስራ በ11 የግል ጤና ተቋማት 38 የጤና ባለሙያዎችን በማሳተፍ 2100 ለሚሆኑ ለምገባ ማዕከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የአይን፣ የጥርስ፣ የቆዳ እንዲሁም አጠቃላይ የውስጥ ደዌ ነፃ የጤና ምርመራና የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በስፍራው የተገኙት የባለስልጣኑ የብቃት ማረጋገጥ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ ባለስልጣን መ/ቤቱ የግል ጤና ተቋማትን በማስተባበር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
አያይዘውም ለምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚዎች ተገቢው የህክምና ክትትል ተደርጎ ለወደፊትም የዘላቂ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።
ምክትል ስራ አስኪያጇ አክለውም ለበጎ ስራው ስኬታማነት አስፈላጊውን ትብብር ላደረጉ የጤና ተቋማት እና ለጠቅላላ አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበው እንዲህ ያሉ ተግባራት በጤና ተቋማት እና በምገባ ማዕከላት መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር ዘላቂ የማህበረሰብ አቀፍ የድጋፍ ስራ እንደሚገነቡ አመላክተዋል።
ለበለጠ መረጃ
https://web.facebook.com/facebook.comAAFDA https://whatsapp.com/dl/ https://www.youtube.com/channel/UC_Oc0F_MUGBV2UcyiKtvijw
https://t.me/AAFMHAC
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

በህገ -ወጥ መልኩ   ተከማችቶ  የነበረ ግምታዊ ዋጋው  8,664, 495  ብር የሚያወጣ የተበላሸና የመጠቀሚያ ግዜው ያለፈ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል ተወገደ።11/12/2018ዓ.ምበባለስልጣኑ...
17/08/2026

በህገ -ወጥ መልኩ ተከማችቶ የነበረ ግምታዊ ዋጋው 8,664, 495 ብር የሚያወጣ የተበላሸና የመጠቀሚያ ግዜው ያለፈ የኩላሊት እጥበት ኬሚካል ተወገደ።

11/12/2018ዓ.ም

በባለስልጣኑ በተደረገ ቅኝትና ክትትል በየካ ክ/ከተማ ልዩ ቦታ ሾላ ገበያ አካባቢ በግለሰብ የመኖሪያ ቤት ቤት ውስጥ የተከዘነ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው ለኩላሊት እጥበት የሚውሉ ኬሚካሎች እና የህክምና መሳሪያዎች ተገኝተዋል።

የተከማቸው የህክምና መገልገያ መሳሪያም ሆነ ኬሚካል በኩላሊት እጥበት ክሊኒክ ስር እስቶር ነው የሚል ሽፋን ያደረገ ሲሆን ፣ ከስታንዳርድ በታች የሆነ እንዲሁም በየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እውቅናና እና የብቃት ማረጋገጫ የሌለው መሆኑን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ቁጥጥር ዳሬክቶሬት አቶ ሲሳይ ሁንዴ ገልጸዋል። አክለውም የተገኙት ኬሚካሎች ለኩላሊት እጥበት ህክምና የሚያገለግሉ (Hemodialysis A) እና (Hemodialysis B) መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመጋዘኑ ውስጥ በአጠቃላይ 34 ዓይነት የሕክምና መሳሪያዎችና የኩላሊት እጥበት ኬሚካሎች የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 14 ዓይነት ሙሉ በሙሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሲሆኑ ፣ ሁለት ዓይነቶች የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው ባይሆኑም በተገቢው ሁኔታ ባለመከማቸታቸው ለአገልግሎት ብቁ እንዳልሆኑ ተረጋግጦ በአለርት ኮፕሬንሲቭ ስቴሻላይዝድ ሆስፒታል በህክምና ኬሚካሎች እና መድኃኒት ማቃጠያ እንዲወገድ ተደርጓል። ቀሪዎቹ 18 ዓይነት የሕክምና መሳሪያዎች ለአገልግሎት የሚያበቃቸው ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ሳይወገዱ ቀርተዋል።

በአጠቃላይ የተወገዱት ምርቶች ግምታዊ ዋጋቸው 8 ሚሊዮን 664 ሺህ 495 ብር ሲሆን ጊዜያቸው ያለፈባቸው 14 ዓይነት የኩላሊት እጥበት ኬሚካሎች ግምታዊ ዋጋ 8 ሚሊዮን 615 ሺህ 495 ብር የሚገመት ሲሆን፣ በአቀማመጥ ጉድለት ምክንያት ለአገልግሎት የማይውሉት ሁለት ዓይነት ኬሚካሎች 49 ሺህ ግምታዊ ዋጋ እንዳለቸው ተገልጻል። በተጨማሪም በምርቶቹ ላይ በተደረገው የአገልግሎት ጊዜ ምርመራ ከ2021 እስከ 2026 ድረስ ያሉ ቀናትን ያሳየና የአገልግሎት ጊዜ ካለፈባቸው ረጅም አመታትን ያስቆጠሩ መሆናቸው ተገልጻል።

በተወሰደ እርምጃ የተገኙት ምርቶች እንዲወገዱ የተደረገ ሲሆን ከግኝቱ ጋር ተያያዥነት የነበረው ክሊኒክም አገልግሎት እንዳይሰጥ መደረጉን ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።

የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ታደሰ በመልዕክታቸው፣ ባለስልጣኑ ባደረገው ቅኝትና ክትትል ኃላፊነት የጎደለው የጤና ግብዓት ክምችት ሊያስከትለው ከሚችል የጤና ስጋት ቀድሞ መከላከል የተቻለ መሆኑን ገልጸው ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ተባባሪ በመሆን ጥቆማ እንዲሰጥና ከጤና ቁጥጥር አካላት ጎን በመቆም በጋራ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉ እመቤት ታደሰ ጉዳዩን ባለስልጣኑ በጥብቅ እንደተከታተለው እና በጤና ተቋማት፣ በማስወገጃ ቦታዎች እና በተቋማት ውስጥ ባሉ የመድኃኒትና የሕክምና ምርቶች ማከማቻዎች ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ ሕገወጥ የሕክምና ምርቶች ለሕብረተሰቡ እንዳይደርሱ ኃላፊነት ወስዶ እንደሚሠራ ገልጸው ተቋማትም ለሚሰሩት ስራ ህጋዊነትን እና እስታንዳርድን አስጠብቀው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ወስደው መስራት እንዳለባቸው ጥሪ አስተላልፈዋል ።

17/08/2026

Address

4 Kilo Behind Ministry Of Education
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን:

Shortcuts

Share