31/08/2026
በወረዳው የተቋቋመው የሰንበት ገበያ የኑሮ ዉድነትን ከመዋጋት አኳያ ትልቁን ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ተገለፀ!
ነሐሴ 25/2018 /ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን/
በወረዳ 10 አስተዳደር የተቋቋመው የሰንበት ገበያ አምራቾችንና ሸማቾችን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ከመቋቋም አኳያ ትልቁን ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ።
የሰንበት ገበያው ለወረዳው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ከወረዳው ውጭ ካሉ አጎራባች አካባቢዎች ለሚመጡ ሸማቾችም ምቹ የግብይት አማራጭ ሆኖ እያገለገለ መሆኑ ታውቋል። በዚህም በገበያው ላይ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ ሲሆኑ፣ ሸማቾችም የሚፈልጓቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ዕድል ፈጥሯል።
በተለይም በገበያው የሚሸጡ ምርቶች ከመደበኛው የገበያ ዋጋ አንፃር በቅናሽ መቅረባቸው የሸማቾችን የግዢ አቅም ለማጠናከር እና የኑሮ ውድነት የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ህብረተሰቡ የሰንበት ገበያውን የመጠቀም ልምዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል። ይህም ገበያው በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱንና ለተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ለማቅረብ ያለውን ሚና እያጠናከረ መሆኑን ያሳያል።
የሰንበት ገበያው አምራችና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት፣ የመካከለኛ ደላላ ሰንሰለትን በመቀነስ እና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን በመቋቋም ረገድ ያለውን አስተዋፅኦ እያጠናከረ መሆኑ ተገልጿል።