07/09/2026
የጳጉሜን 2፦ማንሠራራት ቀን
የሀገራችንን ብሩህ ተስፋና የተገበሩ ትልልቅ እቅዶችን የምናስብበት፣ የታሪክ ጉዞአችንን አቅጣጫ የቀየሩ ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶቻችንን የምናመሰግንበት ልዩ ዕለት ነው።
በባለፉት ጥቂት ዓመታት ሀገራችን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፋ፣ በጽናትና በትጋት በሰራቻቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች አማካኝነት እውን ያደረገቻቸው የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን የማንሠራራት መንፈስ በግልጽ ያሳያሉ። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ፣ በግብርናው ዘርፍ በተመዘገበው የስንዴ ምርታማነትና በሌሎች ሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገራችን በራሷ አቅምና ጥረት ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ መሸጋገር እንደምትችል በተግባር ያረጋገጡ አበይት ማረጋገጫዎች ናቸው።
መዲናችን አዲስ አበባ የዚህ ሁለንተናዊ ማንሠራራት እና የለውጥ ጉዞ ዋነኛ ማዕከል በመሆን ድንቅ የልማት ምሳሌነቷን አስመስክራለች። የተቀናጀው የኮሪደር ልማት፣ የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የወንዝ ዳርቻ ማደስና የጽዳት ሥራዎች፣ የትራፊክና የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎች እንዲሁም የነዋሪዎችን ማኅበራዊ አገልግሎት ያደራጁ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።
አዲስ አበባ አሁን ላይ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለውጭ እንግዶችና ለቱሪስቶች ደግሞ ማራኪ፣ ዘመናዊና ጽዱ አፍሪካዊት መዲና ሆና በመገንባት ላይ ትገኛለች።
የየካ ክፍለ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት የጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀንን በማስመልከት የቀበና ወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክትና የቀበና ፕላዛ የመኪና ማቆሚያን ጎብኝቷል።
#የካ