Arada woreda 7 communication office

Arada woreda 7 communication office Government page

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።ለቤተሰቦቿ ፣...
06/09/2026

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።

አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።
ለቤተሰቦቿ ፣ለወዳጅ ዘመዶቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሷን በአፀደ ገነት ያኑር

Lubbuun darbuu Artistii fi Qabsooftuu Bilisummaa Ilfinash Qannoo kanan dhagahe gadda guddaa keessatti.

Artist Ilfinash weellistuu qofa osoo hin taane qabsooftuu mirga namummaa fi wal-qixummaa turte.
Maatii ishee, firoottan ishee fi dinqisiifattoota isheef jajjabinan hawwa.
Waaqni Lubbuu ishee Jeennata haa jiraachisu

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?ለበለጠ መረጃ:➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et➜ ፋይዳ: id.gov.et➜ መሶብ: https://mesob...
06/09/2026

ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?

ለበለጠ መረጃ:

➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et

➜ ፋይዳ: id.gov.et

➜ መሶብ: https://mesobcenter.et/

➜ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት: aii.et

06/09/2026

መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት የተዘጋጀ የበዓል ገበያ
ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም
አራዳ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ጽቤት

06/09/2026

#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን‼

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለፀ።ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የዲዛ...
06/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለፀ።

ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ገለፀ።

በበጀት ዓመቱ በዘርፉ በተከናወኑ ስራዎች የከተማውን ገፅታ በዘመናዊ መልኩ መቀየር የተቻለ ሲሆን የ7/24 የስራ ባህልን በማዳበር የግንባታ ፈጣን አፈፃፀም ማምጣት ተችሏል።

በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ፣ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት መረጋገጡ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ አሰራር መታገዙ የዘርፉ እመርታዎች ናቸው።

የሀገር ውስጥ የስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶችን አቅም በዘላቂነት ለመገንባት የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ባለሙያዎች ወጭ ቆጣቢና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የመጠቀም አቅም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።

እነዚህ አመርቂ ውጤቶች ከአራዳ ክፍለ ከተማ ታሪካዊ ቁመና እና አሁን አዲስ አበባ ከምታከናውነው አጠቃላይ የኮሪደር ልማት ማዕቀፍ ጋር ተጣጥመው መተግበራቸው ለዘርፉ የላቀ ስኬት መሠረት ሆኗል።

የኮሪደር ልማቱ አካባቢዎችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ማራኪ በማድረግ የከተማዋን ነዋሪዎችና የቱሪስቶች እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን አድርጎታል።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር የኮንስትራክሽንና የኮሪደር ልማት ስራዎችን በማቀናጀት አራዳን የዕድገትና የብልጽግና ምዕራፍ ማሳያ ለማድረግ በቀጣይም የተጠናከሩ ስራዎች እንደሚሰሩ ጽ/ቤታ ገልጿል።

 #ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን‼የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዲስ ዓመትን በአምራችና በልማታዊ ስራዎች ለመቀበል የሚያስችሉ አበክሮ የሰሩዋቸውን ስራዎች አጠና...
06/09/2026

#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን‼

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዲስ ዓመትን በአምራችና በልማታዊ ስራዎች ለመቀበል የሚያስችሉ አበክሮ የሰሩዋቸውን ስራዎች አጠናክሮ ቀጥሏል። የዘመኑን ማጠናቀቂያና የዕድሳት ምልክት በሆነችው ጳጉሜ 1 ቀን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በወረዳችን የተከናወኑ የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ውጤቶች የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

​በዚህ የጉብኝት መርሃ-ግብር ላይ የወረዳው አስተዳደር ሰራተኞች፣ የኮሙኒኬሽን ቡድን አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወጣቶችና የሴቶች ማህበር ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት ተሳትፈዋል።

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚያረጋግጠው፣ በወረዳው በማኑፋክቸሪንግ እና በኢንዱስትሪ ማዕቀፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የቤተሰብን ወጪ በመቀነስ የኢኮኖሚ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ተሳታፊዎች በጉብኝቱ ወቅት በባዶ ቦታዎችና በሼዶች ላይ የሚከናወኑ የኢንዱስትሪ ውጤቶች አካባቢያችንን ልማታዊ ከማድረግ ባለፈ ህብረተሰቡ የራሱን የምርት ፍላጎት በራሱ ጥረት ለማሟላት ያለውን አቅም አሳይቷል ብለዋል።

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነውከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡...
06/09/2026

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

ከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የጸደይ መዳረሻን ለማብሰር ከሚከናወኑ ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “የጎቤ” እና “ሺኖዬ” ጨዋታ ተጠቃሽ ነው።
AMN

 #ጳጉሜ 1 “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በወረዳችን የተከናወኑ የከተማ ግብርና ውጤቶች ጎብኝት ተካሄደ‼​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዲስ ...
06/09/2026

#ጳጉሜ 1 “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በወረዳችን የተከናወኑ የከተማ ግብርና ውጤቶች ጎብኝት ተካሄደ‼

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዲስ ዓመትን በአምራችና በልማታዊ ስራዎች ለመቀበል የሚያስችሉ አበክሮ የሰሩዋቸውን ስራዎች አጠናክሮ ቀጥሏል። የዘመኑን ማጠናቀቂያና የዕድሳት ምልክት በሆነችው ጳጉሜ 1 ቀን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በወረዳችን የተከናወኑ የከተማ ግብርና የልማት ስራዎች ውጤቶች የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

​በዚህ የጉብኝት መርሃ-ግብር ላይ የወረዳው አስተዳደር ሰራተኞች፣ የኮሙኒኬሽን ቡድን አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወጣቶችና የሴቶች ማህበር ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት ተሳትፈዋል።

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደርና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚያረጋግጠው፣ በወረዳው በጓሮ አትክልት ልማት እና በurban agriculture ማዕቀፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የቤተሰብን ወጪ በመቀነስ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ተሳታፊዎች በጉብኝቱ ወቅት በባዶ ቦታዎች ላይ የሚለሙ አትክልቶችና ፍራፍሬዎች አካባቢያችንን ጽዱና ውብ ከማድረግ ባለፈ ህብረተሰቡ የራሱን የምግብ ፍላጎት በራሱ ጥረት ለማሟላት ያለውን አቅም አሳይቷል ብለዋል።

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደርና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በዕለቱ እንደገለጸው፤ ህብረተሰቡ የልማት ስራዎች ባለቤት በመሆን በንቃት እንዲሳተፍ በማድረግ ረገድ የተገኙት ውጤቶች የሚያበረታቱ ናቸው። ጽ/ቤቱም ለህብረተሰቡ ሁለንተናዊ እድገት፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለአምራችነት እንቅስቃሴዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

​የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደርና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

በትጋት ሰርተን በላባችን አምርተን ከተረጂነት ቀንበር ነፃ ወጥተናል‼​አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የጳጉሜ 1 "እምርታ ቀን"ን "የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ ሃሳብ በደማቅ ሁኔታ እያከከበ...
06/09/2026

በትጋት ሰርተን በላባችን አምርተን ከተረጂነት ቀንበር ነፃ ወጥተናል‼

​አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የጳጉሜ 1 "እምርታ ቀን"ን "የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ ሃሳብ በደማቅ ሁኔታ እያከከበረ ይገኛል።

ጳጉሜ 1 2018ዓ.ም

06/09/2026

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada woreda 7 communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Arada woreda 7 communication office:

Shortcuts

Share