Shir-Shir Ethiopia

Shir-Shir Ethiopia We work for people in the journey and Shir-shir Ethiopia is the open gate to rediscover the new face of Ethiopia

23/05/2026
The new face of Addis , river restoration to public walking lane, entertainment garden , fountain and byke lane.   Ethio...
13/05/2026

The new face of Addis , river restoration to public walking lane, entertainment garden , fountain and byke lane.
Ethiopia Ababa

08/05/2026

በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረትና ረጅም ሰልፍ የዜጎች የዕለት ተዕለት ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ጎረቤት ሀገር ኬንያ የተከተለችው የተሳካ አሠራር ለኢትዮጵያ አመራሮች ትልቅ ጥያቄ ደቅኗል።

WT Media ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኬንያ በሕዝብ ቁጥር ከኢትዮጵያ በግማሽ ብታንስም (55 ሚሊዮን ገደማ)፣ በተሽከርካሪ ብዛት ግን ኢትዮጵያን በሦስት እጥፍ ገደማ ትበልጣለች።

በኬንያ ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ የነዳጅ ሰልፍ ታይቶ የማይታወቅ ሲሆን፣ ማደያዎች ደንበኛ ለመሳብ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችን (Bonus) ሲያቀርቡ ይስተዋላል።

በተቃራኒው ከ126 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ፣ ያላት የተሽከርካሪ ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን የማይበልጥ ቢሆንም፣ ነዳጅ ማግኘት ግን እንደ ሰማይ የራቀ ሆኗል። ይህ ንጽጽር እንደሚያሳየው በኬንያ ለእያንዳንዱ 12 ሰው አንድ መኪና ሲኖር፣ በኢትዮጵያ ግን ለ84 ሰው ነው አንድ መኪና የሚደረሰው።

መኪና እጅግ ባነሰባት ሀገር እንዲህ ያለ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መታየቱ ችግሩ የአቅርቦት ሳይሆን የአሠራር መሆኑን ያሳያል።

ኬንያ እንደ ኢትዮጵያ ነዳጅን ከውጭ ሀገር ገዝታ የምታስገባ ቢሆንም፣ የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ቁጥጥር ሥርዓቷ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃና በዲጂታል ሥርዓት የተደገፈ በመሆኑ የጥቁር ገበያ ዕድል የለውም።

በኢትዮጵያ ግን የነዳጅ እጥረት ሰው ሠራሽ መሆኑንና በአመራሩ፣ በነጋዴውና በአንዳንድ የፀጥታ አካላት መካከል የተዘረጋው የጥቁር ገበያ ሰንሰለት ሕዝቡን ለእንግልት እየዳረገው እንደሚገኝ ይገለጻል።

ሌላው አስገራሚ እውነታ ኬንያ አብዛኛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ የምትገዛ መሆኗ ነው። ይሁን እንጂ ኬንያ ውስጥ የመብራት መቆራረጥ አጀንዳ ሆኖ አያውቅም።

የኃይል ማመንጫው ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በጨለማና በመቆራረጥ ስትፈተን፣ ገዥዋ ኬንያ ግን ከእኛ የገዛችውን ኃይል በአግባቡ በማስተዳደር ለዜጎቿ አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች።

ይህ ተሞክሮ የሚያሳየው የሀብት እጥረት ሳይሆን የአመራርና የቴክኒክ ብቃት ማነስ ትልቁ የኢትዮጵያ ችግር መሆኑን ነው።

ዜጎች በነዳጅ ሰልፍና በመብራት ጨለማ በሚሰቃዩበት በዚህ ወቅት፣ የመንግሥት አመራሮች ለሕዝብ ቅድሚያ የሚሰጥና ግልጽነት ያለው አሠራር መዘርጋት እንዳለባቸው የኬንያ ተሞክሮ ትልቅ ማሳያ ነው።

07/05/2026
ምስካየህዙናን መድሐኒትዓለም፤ እንኳን አደረሰን
05/05/2026

ምስካየህዙናን መድሐኒ
ትዓለም፤ እንኳን አደረሰን

Mountain byke adventure international byke feast is happening in Addis Ababa at Adwa museum arada  park first time   tou...
03/05/2026

Mountain byke adventure international byke feast is happening in Addis Ababa at Adwa museum arada park first time tourism Addis # tourism

Address

Madagascar Street
Addis Ababa
251

Telephone

+251(0)920656690

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shir-Shir Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Shir-Shir Ethiopia:

Shortcuts

Share