Bruhtesfa Memorial Foundation

Bruhtesfa Memorial Foundation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bruhtesfa Memorial Foundation, Public & Government Service, Jemo 1, Addis Ababa.

Bruhtesfa Memorial Foundation has been working ,on the accessibility of quality education for disadvantaged school children , who present at rural and semi-urban governmental schools since 2015.

29/04/2026
27/07/2022
23/04/2018

Bruhtesfa Memorial Foundation has been working ,on the accessibility of quality education for disadvantaged school children , who present at rural and semi-urban governmental schools since 2015.

31/03/2018

STEM( Science, Technology,Engineering And Mathematics) education can have a significant impact on moving people out of poverty.

ብሩህተስፋ መታሰቢ በጎ አድረጎት ድርጅት እንዴት እና ለምን ተቋቋመ?  ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ኢብራሂም ይባል ነበር ። በጅማ ዩኒቨርሲቲ በኢንጅነሪኒግ የወርቅ ተቨላሚ ነበር። ከዛም በኔ...
27/03/2018

ብሩህተስፋ መታሰቢ በጎ አድረጎት ድርጅት እንዴት እና ለምን ተቋቋመ?
ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ኢብራሂም ይባል ነበር ። በጅማ ዩኒቨርሲቲ በኢንጅነሪኒግ የወርቅ ተቨላሚ ነበር። ከዛም በኔዘርላንድ ማስተሩን በመማር በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆአል በኖርዌይ ዶክትሬቱን በ27 አመቱ ሲያጠናቅቅ መመረቂያው በአለም ካሉ ምርጥ 10 የመመረቂያ ምርምሮች አንዱ በመሆኑ ተሸላሚ ነበር። በኢንጅነሪንግ መስክ በለጋ ዕድሜው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ኢትዩጵያን ያስጠራ ነበረ። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ ከ3 አመት በፊት ከዚህ አለም በ29 አመቱ በህይወት አጣነው። ከህይወቱ ትማሩ ዘንድ አጭር የህይወት ታሪኩን አቅርበናል፡፡
_____________________________
የዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ኢብራሂም ጎዳና አጭር የሕይወት ታሪክ
Doctoral degree prizes awarded at NTNU

ExxonMobil has awarded the annual doctoral degree prizes to two ph.d.-students at NTNU in Trondheim.
November 28th2014 Communications director in ExxonMobil Exploration and Production Norway .The company’s award for applied research was granted to Dr. Bruhtesfa Godana from the Institute of Electrical Engineering and Telecommunications, with the thesis: «Feedback and Precoding Techniques for MIMO Wireless Communication».
According to the Norwegian University of Science and Technology (NTNU). Godana’s work is rated as top ten on an international level, and his thesis has been considered so relevant that he is already granted a position in Ericssons’ research department in competition with 80 other applicators with doctoral degrees.

፩:- የልጅነትና ቅድመ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት
ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ከአባቱ ከአቶ ኢብራሂም ጎዳና አና ከእናቱ ከመምህርት አማከለች ከበደ ግንቦት ፳፬ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በደቡብ ወሎ ዞን ለጋንቦ ወረዳ በአቀስታ ከተማ ተወለደ። እድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢዉ በሚገኝ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመግባት አስከ ፰ኛ ክፍል ያለዉን ትምህርት በ፮ ዓመታት በማጠናቀቅ ደሴ ወደሚገኘዉ ወ/ሮ ስህን ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመዛወር የ፪ኛ ደረጃ ትምህርቱን በ፲፱፻፺፫ ዓም አጠናቀቀ። ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ በ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበረት ወቅት በመላዉ አማራ ክልል በሚገኙ የ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል በተካሄደ የጥያቄና መልስ ዉድ ድር ፩ኛ በመዉጣት ተሸላሚ ነበር ። የ ፲፪ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቅቂያ ፈተና ፯ ትምህርቶችን በመፈተንና በሁሉም የትምህርት አይነቶች ከፍተኛ ወይም የ ኤ ዉጤት በማምጣት በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በጅማ ዩንቨርስቲ የከፍትኛ ትምህርቱን ለመከታተል ተመደበ።
ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ በማህበራዊ ህይወቱ ከልጅነቱ ጀምሮ አስተዋይ ፣ ቁጥብና ሰዎችን ላለማስቀየም ያደርገዉ የነበረዉ ጥንቃቄ ያሳደጉት ወላጅ አናቱንና ሴት አያቱን ያስመሰገነ ነበር። በቤተሰቦቹ አንደተመሰከረለት ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ከልጅነቱ ጀምሮ ለትምህርት ልዩ ቦታ ይስጥ አንደነበርና አብዛኛዉን ጊዜዉን በማጥናትና ጉዋደኞቹን በማስጠናት ያሳልፍ ነበር ። አጥበቆ ይጠላቸው ከነበሩ አንዱና ዋነኛው ፈተና ላይ ማስኮረጅ ነበር። በ፲፱፻፺፭ ዓም ወላጅ እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉንና ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋን ከልጅነቱ ጀመሮ ያሳየው የነበረዉን ከፍተኛ የትምህርት ታታሪነት ምክንያት በማድረግ በ፳፻ ዓ.ም. በአቀስታ ከተማ የተገነባ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስሙ ተሰይሞ ይገኛል (ተሰይሞለታል)።
፪፦ የትምህርትና የምርምር ሕይወት
ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ከ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ጀምሮ በጅማ ዩንቨርስቲ በኤሌክትሪካል ምህንድስና ትምሕርት ክፍል የከፍተኛ ትምህርቱን ሲከታተል ከራሱ አልፎ ሌሎችን እያስጠና የተሰጠውን መክሊት በመጠቅም የምግባረ ሠናይ አርዓያ ለመሆን ችሏል። በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በ፳፩ ዓመቱ በከፍተኛ ማዕረግ የወርቅ ተሸላሚ በመሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን አጠናቀቀ። በዚሁም ወቅት ሶፍትዌር ላይ የተመሠረተ የ AM ራዲዮ መቀበያ ሥርዓት ላይ የመመረቂያ ጽሑፉን አቅርቧል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ የኤለኢክትሪካል ምህንድስና የትምህርት ክፍል በአስተማሪነት ለተወሰኑ ወራት ከሠራ በኋላ የውጭ የትምህርት ዕድል በማግኘት በኔዘርላንድ የደልፍት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪውን በኤሌክትሪካል ምህንድስና በማዕረግ አጠናቋል። በዚሁ ጊዜ የመመረቂያ ጽሑፉን በ GNU ራዲዮ ላይ የተመሠረተ ራዳርን በመጠቀም በቤት ዉስጥ የሚካሄዱ የሰዎችን አንቅስቃሴ መገመት (Human activity characterization in Indoor Environment using GNU Radio based Radar) በሚል ርዕስ ላይ በማተኮር የምርመር ሥራውን ለሳይንስ አበርክቷል። ይህም የምርምር ሥራው የተግባር ጥቅም ያለው ሲሆን ዉጤቱን በዓለም አቀፍ መድረኮችና በምርምር ጋዜጦች በማቅረብና በማሳተም ተሸላሚ ሆኗል።
ከዚህም በኋላ የብዝኃ ግብአት ብዝኃ ውጽአት (Multiple input Multiple Output - MIMO) ራዲዮ መስመሮችን ዱካ በመከታተልና በምላሽ ሂስ ላይ በመመራመርና አዳዲስ ጽንሰሃሳቦችን በመፈልሰፍ በ ፳፯ ዓመቱ በ ፳፻፮ ዓመተ ምህረት የፍልስፍና ሊቅነት (ፒኤችዲ) ዲግሪውን ከኖርዌጂያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል። በዚሁ ጊዜ ብዙ የምርምር ሥራዎቹን በዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችና የሳይንስ ጋዜጦች ላይ አሳትሟል። የሠራው የምርምር ሥራ የሞባይልና የራዲዮ ቴክኖሎጂን ወደፊት ለማራመድ ጥቅም ያለውና የምርምር ሐሳቡም ከዚህ በፊት ያልተሠራ በመሆኑ በ ፳፻፯ ዓመተ ምህረት የ ኤክስ ኦን ሞባይልስ ምርጥ የፒኤችዲ ሥራ ተሸላሚ ሆኗል።
ፒኤችዲውን ካጠናቀቀ በኋላ ስዊድን በሚገኘው የኤሪክሰን የምርምር ክፍል ልምድ ያለው ተመራማሪ በመሆን ለአንድ ዓመት ሕይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ሠርቷል። በኤሪክሰን ሲሰራ በነበረበት ጊዜ በሥራ ባልደረቦቹ የተወደደ ፣ ታታሪ ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥም የብዙ ዓመት የሥራ ልምድ የሚጠይቁ የሥራ ብቃቶችን ያሳየ መሆኑን የሥራ ባልደረቦቹ ይመሰክራሉ። በዚሁም ጊዜ ፲ የሚሆኑ ሥራዎች የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት (patent) በራሱ ስምና ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር አስመዝግቧል።
የምርምርና የሕትመት ሥራዎች
፳፻፮ አስከ ፳፻፯ በኤሪክሰን ልምድ ያለው ተመራማሪ ፣
• በሞባይል ብሮድባንድ ሥርዓት ራዲዮ አክሰስ መረብ ላይ ተመራማሪ
• የ 3GPP LTE ና ክር አልባ /WiFi የመሳሰሉ/ የአጭር ርቀት ቴክኖሎጂ የራዲዮ መረብ አልጎሪዝም ጽንሰ ሃሳብ ማፍለቅና ማበልጸግ ፣ የብቃት ፍተሻ እና ልኬታ ሥራዎች ተመራማሪ
፳፻፪ አስከ ፳፻፮ በኖርዌያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማራማሪ ፣
• በሲግናል ፕሮሰሲንግ አልጎሪዝሞችና የባለብዙ አንቴና ክር አልባ ሥርዓትና ስልቶች ተመራማሪ
• በድኅረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም በሚሰጡ የሲግናል ፕሮሰሲንግ ትግበራ ፣ የዲጂታል ሲግናል ፕሮሰሲንግ እና የራዲዮ ግንኙነት ትምህርቶች ረዳት መምህር
• ሶፍትዌር ላይ የተመሠረተ የራዲዮ ቤተሙከራ ሥራ አከናዋኝ
፳፻፩ አስከ ፳፻፪ በፊሊፕስ ኩባንያ የምርምር ሥራ
• ረዳት ተመራማሪ ፣ በ GNU ራዲዮ ላይ የተመሠረተ ራዳርን በመጠቀም በቤት ዉስጥ የሚካሄዱ የሰዎችን እንቅስቃሴ መገመት
• የሰዎችን እንቅስቃሴ ለመጠቆም፣ ለመለየትና ለመመደብ የሚያስችል በዶፕለር ራዳር ላይ የተመሠረቱ የሲግናል ፕሮሰሲንግ አልጎሪዝሞች ዲዛይን ማድረግ
• USRP እና GNU ራዲዮ በመጠቀም በሶፍትዌር ላይ የተመሠረተ የራዳር ፕላትፎርም ማበልጸግ
በ፳፻፩ በኔዘርላንድ የቴኖ የመረጃ ግንኙነት ቴክኖሎጂ የትምህርት ላይ ልምምድ
• ለቻናል ዛፒንግ ልኬታ የኢንተርኔት ፕሮቶኮል ቴሌቪዥን ፕሮቶታይፕ ማበልጸግ
• በኢንተርኔት ፕሮቶኮል ቴሌቪዥን የልምድ ጥራት ማረጋገጫ ሞዴሎችን መቅረጽ
የሕትመት ሥራዎች
• በ ሲግናል ፕሮሰሲንግ፣ ራዳር እና ክር አልባ ግንኙነቶች አምስት የሕትመት ሥራዎች በዓለም አቀፍ የሳይንስ ጋዜቶች (IEEE) ላይ እና አስር የተመረመሩ የኮንፈረንስ ሕትመቶች (IEEE) አሳትሟል።
ሽልማቶች
• በ ፳፻፯ ዓመተ ምህረት የኤክስ ኦን ሞባይል ምርጥ የፒኤችዲ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ተሸላሚ
• በ ፳፻፪ ዓመተ ምህረት የሴንሰር መሣሪያዎች ኮንፈረንስ ምርጥ የምርምር ሥራ ሕትመት ተሸላሚ
• በ ፳፻፩ ዓመተ ምህረት የአምስተኛው የአይካስ /ICAS/ ኮንፈረንስ ምርጥ የምርምር ሥራ ሕትመት ተሸላሚ
• ከ ፳፻ እስከ ፳፻፪ የ ኢዊ /EWI/ ፋኩሊቲ የትምህርት ዕድል ተሸላሚ
• በ ፲፱፻፺፰ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን በከፍተኛ ማዕረግ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ
• በ፲፱፻፺፪ ዐማራ ክልል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ውድድር ልዩ ተሸላሚ
፫፦ማህበራዊ ሕይወት
በጓደኞቹና በሥራ ባልደረቦቹ እይታ በማህበራዊ ሕይወቱ የተመሰገነ ፣ ቅን ፣ ትሑት ፣ ሩህሩህ ፤ ከጓደኞቹ አልፎ ለሰው ልጅ ሁሉ መልካም አሳቢና አድራጊ ነበር። ሕይወቱ ፤ አኗኗሩ ምሳሌ የሚሆን አብዝቶ የሚተገብር ፣ በንግግሩ የተቆጠበ ፣ በደለን የማይወድ ፣ ክፋትን የሚጸየፍ ነበር። በድርጊቱ ሁሉ በጓደኞቹ በሥራ ባልደረቦቹ የተወደደ በሥራ ብቃቱ ፣ በቀና አስተሳሰቡና በታማኝነቱ የተከበረ ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ ክብር የሚሰጥ ነበር።
፬:- እረፍት
ዶክተር ኢንጅነር ብሩህተስፋ ረቡዕ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ስቶክሆልም ስዊድን በሚገኘው በካሮሊንስካ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ማክሰኞ መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል። የቀብር ስነሥርዓቱ እሑድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም ቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተፈጽሟል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ብሩህተስፋዎችን የምታፈራ ሀገር በመሆኗ ለህጻናት ታላቅ አርአያነት ያለው ወጣት በመሆኑ በስሙ የበጎአድራጎት ድርጅት በማቋቋም ሀብት አጠር በሆኑ እና በገጠሪቱ ኢትየጵያ በሚገኙ የመንግስት ትምህረት ቤቶች ላይ በተለይም በሳይንስ የትምህረት መስክ እገዛ ለማድረግ ለመስራት ታቅዶ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡
በመሆኑም የትምህርት ጉዳይ የሀገር ጉዳይ በመሆኑ ብሩህተስፋ መታሰቢየያ በጎአድራጎት ድርጅት የሁሉንም እገዛ ይፈልጋል!!!!!
ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ www.bruhtesfafoundation.org

Some of Bruhtesfas's scientific contributions to the world at young age of mid-20s. (sources:1.http://ieeexplore.ieee.or...
16/03/2018

Some of Bruhtesfas's scientific contributions to the world at young age of mid-20s. (sources:
1.http://ieeexplore.ieee.org/document/6612899/…
2.https://www.researchgate.net/…/2036248770_Bruhtesfa_E_Godana)
1.Estimating Indoor Walking Velocity Profile Using a Software Radio-Based Radar
2. Linear prediction of time-varying MIMO systems using Givens rotations
3.A reduced quantization range feedback method for time-varying MIMO systems
4.On Channel Capacity of Communication Via Antenna Arrays with Receiver Noise Matching
5.Compressed Sensing Performance Analysis via Replica Method using Bayesian framework
6.Egoistic vs. altruistic beam forming in multi-cell systems with feedback and back-haul delays
7. Parametrization Based Limited Feedback Design for Correlated MIMO Channels Using New Statistical Models
8. Coordinated beam forming in multi-cell networks with Channel State Information exchange delays
for further information
Visit our website http//www.bruhtesfafoundation.org
Support quality education disadvantaged rural school children

Parametrization of unitary matrices using Givens rotations has been used for limited feedback in multiple-input multiple-output (MIMO) systems. Feedback ba

16/03/2018

Let us make learning possible for every child of school age.

15/03/2018

Support quality education disadvantaged rural school children.

Address

Jemo 1
Addis Ababa
02

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 13:00

Telephone

+251-911-57-06-90

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bruhtesfa Memorial Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share