02/09/2026
ከ 77 ሚሊዮን ብር በላይ የማማከር፣ ጥናትና ዲዛይን እና ግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ 77 ሚሊዮን ብር በላይ የማማከር፣ ጥናትና ዲዛይን እና ግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።
የውል ስምምነቱን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ አካባቢዎቹ ውሃ አጠር በመሆናቸው በውሉ መሰረት የማማከርና የግንባታ ቁጥጥር ስራው ቢቻል ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብለው ሰርተው እንዲያስረክቡ አሳስበው፤ ለህብረተሰቡ ዘላቂ ጥቅም በሚያስገኝ አግባብ እንዲተገበርም አደራ ብለዋል።
ክቡር አምባሳደር አክለውም ተቋሙ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም በመከታተል አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።
የ LETINSA Share Company ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ማሞ እና የ DH Consult PLC ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አስቴር ተሰማ በበኩላቸው የፕሮጀክቱን አስቸኳይነት ተረድተን ከተያዘው ጊዜ ቀድመን በጥራት ሰርተን ለማስረከብ ቃል እንገባለን ብለዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነውና በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበረው ፕሮጀክት የ88 መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን የአማካሪ ቅጥር እየተከናወነ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ72ቱ ፕሮጀክቶች አማካሪ ቅጥር የተፈፀመ በመሆኑ፤ በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 4 ፕሮጀክቶች 2ቱ በሱርማ እና 2ቱ በሸኮ ወረዳ በ45,260,435.00 ወጪ ከ DH Consult PLC ጋር ውል የተፈረመ ሲሆን፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3 ፕሮጀክቶች 2ቱ በጠምባሮ እና 1ዱ በሙሁር አክሊል ወረዳ በ31,750,137.69 ወጪ ከ LETINSA Share Company ጋር በ12 ወራት የሚጠናቀቅ ውል ተፈርሟል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/