Gerd network

Gerd network mobilization

05/09/2024
01/04/2022
Great Ethiopia Renaissance Dam is a question of fairness!
01/04/2022

Great Ethiopia Renaissance Dam is a question of fairness!

አባይ ወንዝና ተፋሰሱን አለማልማት በራስ ላይ ሞትን መፍረድ ነው፡እንዳይለማ መከራከር ደግሞ በዓለም ብቸኛው ቀልድ ነው፡ ይህን ለመደገፍ መሞከርም የዩንቨርሳችን ብቸኛው ኢፍትኃዊነት ነው!
24/03/2022

አባይ ወንዝና ተፋሰሱን አለማልማት በራስ ላይ ሞትን መፍረድ ነው፡

እንዳይለማ መከራከር ደግሞ በዓለም ብቸኛው ቀልድ ነው፡

ይህን ለመደገፍ መሞከርም የዩንቨርሳችን ብቸኛው ኢፍትኃዊነት ነው!

የሕዳሴ ግድብ ዋንጫለሕዳሴ ግድብ በተመሳሳይ ዓላማ እንድንሰባሰብ ከተፈጠሩ ሁነቶች አንዱ “የሕዳሴ ግድብ ዋንጫ” ነው፡፡ ዋንጫው በኦሮሚያ የሚገኙ ኢትዮጵያንን ለማስተባበር ዛሬ ከክልሉ ወደ ዞ...
15/03/2022

የሕዳሴ ግድብ ዋንጫ

ለሕዳሴ ግድብ በተመሳሳይ ዓላማ እንድንሰባሰብ ከተፈጠሩ ሁነቶች አንዱ “የሕዳሴ ግድብ ዋንጫ” ነው፡፡

ዋንጫው በኦሮሚያ የሚገኙ ኢትዮጵያንን ለማስተባበር ዛሬ ከክልሉ ወደ ዞኖች ጉዞውን ጀምሯል፡፡

ጅማዎች ቀዳሚ ናችሁ!

የግብጽ አስዋን ግድብ በታላቋ ሩሲያ ድጋፍ ሲገነባ አሜሪካኖች ደግሞ በ1950ዎቹ የአባይን የግድብ ምቹ ሁኔታ አጥንተውልን ነበር፡፡ “ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመቻላችን ምልክት ነው” ስንል በምክ...
15/03/2022

የግብጽ አስዋን ግድብ በታላቋ ሩሲያ ድጋፍ ሲገነባ አሜሪካኖች ደግሞ በ1950ዎቹ የአባይን የግድብ ምቹ ሁኔታ አጥንተውልን ነበር፡፡

“ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመቻላችን ምልክት ነው” ስንል በምክንያት ነው!

የሀገራችንን ዕምቅ አቅም ሲያውቁ ቁጭቱን አይችሉትም፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የዚህ ቁጭት አንዱ መልስ ነው፡፡ አቅሙ ደግሞ የከበበንን ውጫዊ ተጽዕኖ ለዘለቄታው እንድንሻገር ማስቻሉ ነው!
13/03/2022

የሀገራችንን ዕምቅ አቅም ሲያውቁ ቁጭቱን አይችሉትም፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የዚህ ቁጭት አንዱ መልስ ነው፡፡ አቅሙ ደግሞ የከበበንን ውጫዊ ተጽዕኖ ለዘለቄታው እንድንሻገር ማስቻሉ ነው!

ለ11 ዓመታት በየወሩ የ1000 ብር ቦንድ የገዙት ጡረተኛ!«ምናልባት ግድቡ ሳያልቅ ባልፍ እንኳ፤ ልጆቼ የገባሁትን ቃል ጠብቀው እስከመጨረሻው የቦንድ ግዥውን እንዲፈፅሙ ተስማምተን ነበር።»አ...
11/03/2022

ለ11 ዓመታት በየወሩ የ1000 ብር ቦንድ የገዙት ጡረተኛ!

«ምናልባት ግድቡ ሳያልቅ ባልፍ እንኳ፤ ልጆቼ የገባሁትን ቃል ጠብቀው እስከመጨረሻው የቦንድ ግዥውን እንዲፈፅሙ ተስማምተን ነበር።»
አቶ ፋንታ መስተሳህል

ነዋሪነታቸው በደብረማርቆስ ከተማ ነው፡፡ በቀድሞው አውራ ጎዳና ይባል በነበረው መስሪ ቤት በተለያዩ አካባቢዎች ለዓመታት ተዘዋውረው ሰርተዋል፡፡ በዚህ የስራቸው ባሕሪ የአባይ ወንዝ ለም የሆነውን የኢትዮጰያ አፈር በገፍ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሲያግዝ የማየት እድል ስለነበራቸው ይቆጩ ነበር፡፡ በ2003 ዓ ም በጡረታ ሲገለሉ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ስራው የተጀመረበት ወቅት ነበር፡፡

አቶ ፋንታ ከዶይቼ ቬሌ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደነገሩን በወቅቱ የጡረታ አበላቸው ከ1ሺህ 600 ብር የዘለለ አልነበረም፣ ይሁን እንጂ ከልጆቻቸውና ከባለቤታቸው ጋር በመመካከርና የጋራ ውሳኔ በመድረስ ከሚያገኙት አበል የ1000 ብር ቦንድ ለመግዛት ወሰኑ፡፡ አደረጉትም፡፡ እሳቸው ቢያልፉ እንኳ ልጆቻቸው መግዛቱን እንዲቀጥሉ ጭምር ቃል አስገቡ፡፡

አባይ ኃይል መስጠት ጀመረ! ስራው ሊጠናቀቅም 16 ከመቶ ብቻ ቀረው! ኢትዮጵያውያንም እንደ አቶ ፋንታ ተዓምር መስራታቸውን ቀጠሉ!

11/03/2022

ታላቁ ግድባችን ለኛና ለተፋሰሱ ሀገራት!

አባይ ኤሌክትሪክ እያመነጨልኝ ይፍሰስ በማለት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ላይ ትገኛለች። ይሁን እንጂ ሁለቱ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት “ምን ሲሆን በአባይ ላይ ግድብ ይሰራል” በማለት የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ፕሮጀክቱን ለማስተጓጎል ሲሞክሩ ይታያል። ምክንያታቸው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብታዊ ጥንካሬ የኃይል ሚዛን ሊቀይር ይችላል የሚል ስጋት ነው።

የአፍሪካ እና እስያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ ግን እንዲህ ይላሉ፡፡

“ህዳሴ ግድብ የግጭት ምክንያት ሳይሆን በጋራ የመልማትና የጋራ ተጠቃሚነት እቅድ ያነገበ ፕሮጀክት ነው”

“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቀጠናውን አገራት በብዙ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ከብክለት የፀዳ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን የሚያደርግ ግዙፍ የአፍሪካ ፕሮጀክት ነው”

“ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ኢትዮጵያ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን እንድታንቀሳቅስ ያስችላታል”

“የቀጠናውን አገራት አውንታዊ ግንኙነት በማጠናከርም የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስችላል”

“የንግድ ትስስር በማጠናከር፣ የማህበረሰብ ግንኙነት በማሳደግ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን በማስፋት፣ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ያደርጋል”

“ኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ እና ያላት ሰፊ የህዝብ ቁጥር ለዓረቡ ዓለም፣ ለኤስያ፣ ለአውሮፓ፣ ለመካከለኛው ምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል መግቢያ በር በመሆኗ ተመራጭ መዳረሻ ያደርጋታል”

በመሆኑም

“ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ መጠናቀቅ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው በማስቀጠል ከግብ እንዲደርስ ማድረግ አለባቸው”
ህዳር 13/2014 (ኢዜአ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለዓለም የፍትህ ሚዛን ትልቁ መፈተኛ ነው፡፡ እኛ እንደሆን የቅኝ ግዛትን ኢፍትኃዊነትም ጭምር የሰበርን ነን፡፡ ግድባችን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የደገመው ይህንኑ...
11/03/2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለዓለም የፍትህ ሚዛን ትልቁ መፈተኛ ነው፡፡ እኛ እንደሆን የቅኝ ግዛትን ኢፍትኃዊነትም ጭምር የሰበርን ነን፡፡ ግድባችን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የደገመው ይህንኑ ነው፡፡

11/03/2022
11/03/2022

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gerd network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gerd network:

Share