የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር Federal Democratic Republic of Ethiopia Public Servant Social Security Administration
(2)

በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቅጥር ግቢ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደአዲስ አበባ — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሠራተኞች መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል...
04/09/2026

በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቅጥር ግቢ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ
አዲስ አበባ — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሠራተኞች መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል በማስመልከት፣ በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሰፊ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።
ይህ የጽዳት ዘመቻ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተጀመረውን የጽዳትና ውበት መርሃ ግብር መነሻ ያደረገ ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም የተቋሙን ቅጥር ግቢና አካባቢውን ጽዱ፣ ሳቢና ለሥራ ምቹ ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአዲሱ ዓመት በሠራተኞች ዘንድ አዲስ የሥራ መነሳሳትና መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በዕለቱ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ ከተቋሙ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ሠራተኞች ተሳትፈውበታል።

የመንግሥት ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና አስተዳደር ወጣት ሠራተኞች በዲጂታል ዘመን ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ወሰዱ አዲስ አበባ — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ነሐሴ 2...
01/09/2026

የመንግሥት ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና አስተዳደር ወጣት ሠራተኞች በዲጂታል ዘመን ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ወሰዱ

አዲስ አበባ — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ለወጣት ሠራተኞቹ የኢትዮጵያን ወጣቶች ለመጪው ዲጂታል አለም ዕድል ማብቃት (Empowering Ethiopia's Youth for the Digital Future) በሚል አርዕስት የማነቃቂያ ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው “ስለ 2030 የኢትዮጵያ ዲጂታል ጉዞ፣ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና አለም በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የደረሰበትን የሚያሳዩ እና እያንዳንዱን ወጣት ሠራተኛ ለአገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ዝግጁ ለማድረግ ያለመ ነው።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ቴክኖሎጂን መላመድና አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር የአንድ ወቅት ምርጫ ሳይሆን የዘመኑ ግዴታ መሆኑን ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ሥልጠናው አስተዳደሩ የሚሰጣቸውን የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ፍትሃዊ ለማድረግ ለሚከናወነው የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም አስገንዝበዋል። አቶ ሸጉ አክለውም “ወጣት ሠራተኞቻችን እዚህ ያገኛችሁትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር፣ የአገራችንን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባትና የተቋማችንን አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለማርካት በቁርጠኝነት እንድትሠሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ይህ ሥልጠና በዋናነት ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ዘመናዊና ዲጂታላይዝድ ለማድረግ እንዲሁም ወጣት ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ እየመጡ ያሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ክህሎቶችንና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አጠቃቀምን ተረድተው ለተቋማዊና አገራዊ ዕድገት እንዲተገብሩት ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በሥልጠናው ወቅት ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚችሉባቸው የርቀት የሥራ መስመሮች እና ራሳቸውን ለወደፊቱ የሥራ ዓለም እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸው ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥቷቸዋል።

አስተዳደሩ አገልግሎቶቹን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለመቀየር በርካታ ሪፎርሞችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፤ የሰው ኃይልን በተለይም ወጣቱን ክፍል በዕውቀትና በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዚሁ ስኬት ወሳኝ መሆኑን አስታውቋል። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣት ሠራተኞችም የተሰጣቸው ሥልጠና ተነሳሽነታቸውን ያሳደገ እና ለቀጣይ የዲጂታል ሥራዎች አዲስ እይታ የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

አስተዳደሩ ከመንግስት አሰሪ መ/ቤቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደአዲስ አበባ —ነሐሴ 21/2018የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጡረታ አዋጅ 1267/2014 እና በአፈጻጸ...
27/08/2026

አስተዳደሩ ከመንግስት አሰሪ መ/ቤቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

አዲስ አበባ —ነሐሴ 21/2018
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጡረታ አዋጅ 1267/2014 እና በአፈጻጸም መመሪያው ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገለጸ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት፣ በተቋማት በኩል የሚታዩ የመረጃ መዛባቶች፣ በወቅቱ መዋጮ አለማስገባት እና ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮች በተገልጋዮች ላይ እንግልት በመፍጠር የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጥሩ ቆይተዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ 8 ሺህ 700 የሚጠጉ የመረጃ መዛባቶች ታይተዋል ያሉት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ይህም የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጥር ቆይቷል ብለዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም የጡረተኞችን መረጃ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር እንዲያያዝ በመደረጉ ከአንድ በላይ የጡረታ አበል የሚቀበሉ ሰዎችን በመለየት የማጭበርበር ድርጊቶችን በመከላከል ረገድ ትልቅ ውጤት አምጥቷል። ከአሁን በኋላ የሚደረጉ አዳዲስ የምዝገባ ጥያቄዎች በሙሉ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ተያይዘው ሊቀርቡ ይገባል ብለዋል።

አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንም ደረጃውን የጠበቀ የዳታ ሴንተር የገነባ ሲሆን፣ እያለማ ያለውን WINSAAS አዲስ ሲስተም ሲጠናቀቅም የምዝገባ እና የገቢ አሰባሰብ ሙሉ በሙሉ ኦንላይን (በዲጂታል) ይከናወናል።

በሌላ በኩል፣ በአንዳንድ አሰሪ መስሪያ ቤቶች በኩል የጡረታ መዋጮን በወቅቱ አለማስገባትና ህገ-ወጥ አሰራሮችን የመከተል ችግሮች እንደሚታዩ ተገልጿል። በተለይም ጥቂት የልማት ድርጅቶች አካውንታቸው እንዳይታገድ በርካታ ህገ-ወጥ የባንክ አካውንቶችን በመክፈት ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ለግማሽ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ በምዝገባ፣ በጡረታ አበል ውሳኔ፣ በጡረታ መዋጮ አሰባሰብ፣ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ የልከፈሉ ተቋማት ሀብትን ስለመያዝና ስለመሸጥ እና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

🌙✨ እንኳን አደረሳችሁ! ✨🌙 የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊ...
25/08/2026

🌙✨ እንኳን አደረሳችሁ! ✨🌙

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ እያለ ልባዊ መልካም ምኞቱን ይገልጻል!

በዓሉ ለሀገራችን ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን የሚያጠናክር እንዲሆን እንመኛለን።

🕌 መልካም የመውሊድ በዓል!

#መውሊድ #የመውሊድበዓል #የመንግስትሠራተኞችማህበራዊዋስትናአስተዳደር

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመሸጋገር የሚያስችለውን የTier-III ሞዱላር ዳታ ሴንተር ፕሮጀክት በይፋ ተረከበ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2018...
22/08/2026

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመሸጋገር የሚያስችለውን የTier-III ሞዱላር ዳታ ሴንተር ፕሮጀክት በይፋ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም — የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር (PSSSA) የአገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲሁም ተቋማዊ ሪፎርሙን በቴክኖሎጂ ለማገዝ ያስገነባውን ባለከፍተኛ ጥራት የTier-III ሞዱላር ዳታ ሴንተር (Modular Data Center) ፕሮጀክት ርክክብ ዛሬ በይፋ ፈጽሟል። ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) በዋና ተቋራጭነት ሲያጠናቅቀው፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ደግሞ በቁጥጥርና አማካሪነት በጋራ ሰርተውታል።

በምረቃና ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ እንደገለጹት፣ ይህ የዳታ ሴንተር ግንባታ መጠናቀቅ አስተዳደሩ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመግባት ለጀመረው ጉዞ ትልቅ ማሳያና አንድ እርምጃ ወደፊት የተራመደበት ታሪካዊ ክስተት ነው። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፦ "ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዳታ ሴንተር መገንባት ተቋማችን ለዓመታት ሲያከናውን የቆየውን ሰፊ የሪፎርም (የለውጥ) ስራ ይበልጥ ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው። የአገልግሎት አሰጣጣችንን ግልጽ፣ ፈጣን እና ተደራሽ በማድረግ የተገልጋይ ማህበረሰባችንን እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል" ብለዋል።

ይህ ዘመናዊ የTier-III ደረጃውን የጠበቀ የዳታ ሴንተር ለአስተዳደሩና ለተገልጋዮች በርካታ ዘላቂ ጥቅሞችንና የአገልግሎት ፋይዳዎችን ያስገኛል። የጡረታ ባለመብቶችና የመንግስት ሰራተኞች መረጃዎችን በአንድ ማዕከል በማደራጀት ቀደም ሲል የነበሩ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ አዲሱ ሲስተም (Migration) ለማዘዋወር የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም የጉዳይ ማስተናገጃ ጊዜን እጅግ በማሳጠር ቀልጣፋና ፈጣን የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሰፍን ያደርጋል። ከዚህም በላይ የዜጎችን ሚስጥራዊ የጡረታና የማህበራዊ ዋስትና መረጃዎች ከተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችና አደጋዎች በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅ ባለከፍተኛ ጥራት ቴክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ፣ ተቋሙ ወደ ወረቀት አልባ (Paperless) አሰራር ለሚያደርገው ሽግግርና ለውስጥ የአሰራር ሪፎርም እንደ ዋና የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።

አቶ ሸጉ ኬሎ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ ይህንን ግዙፍና ውስብስብ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ላደረገው ለዋና ተቋራጩ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) እንዲሁም የቁጥጥርና የሙያ እገዛ ላደረገው ለአማካሪው ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሀገር በቀል ተቋማትን እምቅ የቴክኖሎጂ አቅም ያሳየ ፕሮጀክት መሆኑን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ አስተዳደሩ በቀጣይም በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

12/08/2026

ለጡረታ ባለመብቶች በሙሉ!

የኢፌድሪ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር፣ የ2019 በጀት ዓመት የጡረታ መታወቂያ ዕድሳት ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ይህ ወሳኝ የዕድሳት አገልግሎት እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ፣ የተከበራችሁ የሀገር ባለውለታ የጡረታ ባለመብቶች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የአስተዳደሩ ጽሕፈት ቤቶች ወይም ጽ/ቤቶቹ በሚያዘጋጇቸው የዕድሳት ማዕከላት እና መርሃ ግብር መሠረት በአካል በመገኘት መታወቂያችሁን እንድታድሱ በአክብሮት እናሳስባለን።

ስለ ዕድሳቱ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት፣ በአስተዳደሩ የነፃ ስልክ መስመር 8926 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር!

“የ2018 ስኬት ለ2019 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም መነሻ መሆን አለበት” — አቶ ሸጉ ኬሎ አዳማ — የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 02/2018...
08/08/2026

“የ2018 ስኬት ለ2019 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም መነሻ መሆን አለበት” — አቶ ሸጉ ኬሎ

አዳማ — የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት አጠናቋል።

በመድረኩ መጀመሪያ ዕለት (በ26/11/2018 ዓ.ም) ተሳታፊዎቹ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ጥሪ በመቀበል በአዳማ ከተማ በተዘጋጀ ቦታ ላይ በ800 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ከ1000 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

አስተዳደሩ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት የተጣለበትን ሀገራዊና ተቋማዊ ኃላፊነት ለመወጣት ባደረገው የተቀናጀ ጥረት 97 በመቶ አጠቃላይ የዕቅድ አፈጻጸም ማስመዝገቡ በዚሁ የጋራ ግምገማ ላይ ይፋ ሆኗል።

በዚሁ በአንድ ሳምንት የምክክር መድረክ ላይ የዋና መሥሪያ ቤት የሥራ ሂደት ኃላፊዎች፣ የሪጅን ኃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ አስሩም የአስተዳደሩ ሪጅን ጽ/ቤቶች እና በዋና መሥሪያ ቤት ደረጃ የአበል መወሰኛ ዳይሬክቶሬት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ ዳይሬክቶሬት፣ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት፣ የግዥ ዳይሬክቶሬት፣ የሰው ሀብት አስተዳደርና መሠረታዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የኦዲት ዳይሬክቶሬት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይትና ግምገማ ተደርጎባቸዋል።

በበጀት ዓመቱ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከናወን የተቻለ ሲሆን፣ የበጀት አጠቃቀም ሥርዓቱም መመሪያውን የተከተለ እና ቁጠባን ማዕከል ያደረገ እንደነበር ተመልክቷል። ከተገልጋዮች ምልልስ ጋር ተያይዞ የሚታዩ መጉላላቶችን በመቀነስ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ለማሻሻል ሰፊ ጥረት ሲደረግ መቆየቱም ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአስተዳደሩ የፋይናንስና አሠራር ግልጽነትን ለማረጋገጥ ለኦዲት ሪፖርት እና ለግብረ-መልስ አሰጣጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል። የአሠራር ክፍተቶችን ለመሙላት የተከናወኑ የመስክ ሱፐርቪዥን ሥራዎች ውጤታማ የነበሩ በመሆኑ፣ በቀጣይም ተቋማዊ የቁጥጥር ሂደቱን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመድረኩ ላይ በልዩ ትኩረት ከተነሱት አበይት ጉዳዮች መካከል ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ ለማዘመን ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመግባት እያደረገ ያለው ሰፊ እንቅስቃሴ አንዱ ነው። ይህም የጡረተኞች መረጃ አያያዝን ሥርዓታማ፣ አስተማማኝና ዘመናዊ ለማድረግ እንዲሁም የጡረታ መረጃ ተደራሽነትን ለባለጉዳዮች በፈጣን ሁኔታ ለማድረስ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተብራርቷል።

በማጠቃለያው ላይ የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት፣ “የ2018 ስኬት ለ2019 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም መነሻ መሆን አለበት” ሲሉ ገልጸዋል። በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገበው የ97 በመቶ የዕቅድ አፈጻጸም የሚበረታታ ቢሆንም፣ በ2019 በጀት ዓመት ከተቀመጡት ሰፋፊ ዕቅዶች አንጻር ይበልጥ የተሻለ እና የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ እያንዳንዱ አመራርና ሠራተኛ በቁርጠኝነትና በተነሳሽነት ተግቶ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ ለተሳተፉት ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግና ስራዎችን በስትራቴጂ ለመምራት የሚያስችል “የስጋት አስተዳደር” (Risk Management) በሚል አርዕስት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጥቷል።


ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም
አዳማ

በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ አዲስ አበባ — የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሀገር...
03/08/2026

በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

አዲስ አበባ — የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ብሔራዊ መርሃ-ግብር በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ ባወጣው የክንውን ሪፖርት መሠረት፣ በዕለቱ የታቀደውን ግብ 100% በላይ በማሳካት አጠቃላይ 9,230 ችግኞችን መትከል ችሏል።

በዚሁ የአንድ ጀምበር መርሃ-ግብር ላይ የአስተዳደሩን ዋና መሥሪያ ቤት እና ዘጠኝ ሪጅኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ 727 ሠራተኞች በቀጥታ ተሳትፈዋል። ተቋሙ ለሠራተኞቹ ሙሉ የትራንስፖርት፣ የውሃ እና የምግብ አቅርቦት ያመቻቸ ሲሆን፣ ሂደቱም በከፍተኛ አመራሮች በተዋቀረ አስተባባሪ ኮሚቴ እና በቡድን መሪዎች የቅርብ ክትትል ሲደረግበት ውሏል።

መጀመሪያ ላይ ለመትከል የታቀደው 8,830 ችግኞችን የነበረ ቢሆንም፣ ተጨማሪ 400 ጉድጓዶችን በማዘጋጀት አፈጻጸሙን ማሳደግ ተችሏል። በተከላው ላይ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ቡና፣ ጥድ እና ዋንዛ ያሉ የተለያዩ የኢኮኖሚና የአካባቢ ጥበቃ ጠቀሜታ ያላቸው የችግኝ ዓይነቶች በየክልሉ ተተክለዋል።

የሪጅኖች አፈጻጸምን በተመለከተ ደቡብ ሪጅን እና ምዕራብ ሪጅን እያንዳንዳቸው 1,500 ችግኞችን በመትከል ቀዳሚነቱን የያዙ ሲሆን፣ ምስራቅ ሪጅን 1,300 እንዲሁም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን 1,200 ችግኞችን አሳክተዋል። ዋና መሥሪያ ቤትና አዲስ አበባ ሪጅንን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ መዋቅሮችም በተመደቡባቸው ቦታዎች ሁሉ ችግኞችን በስኬት መትከላቸው ተገልጿል።

ተቋሙ በማጠቃለያው፤ ይህንን ሀገራዊ ጥሪ ለመመለስና የአረንጓዴ አሻራ ግብን ለማሳካት ሁሉንም ሪጅኖች ያሳተፈ የተቀናጀ ርብርብ መደረጉን ገልጾ፣ መርሃ-ግብሩ በታቀደው መልኩ በድል መጠናቀቁን አረጋግጧል።

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በኢሉ አባ ቦር ዞን የ16 ሚሊዮን ብር የሞዴል አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ግንባታ አስጀመረ፤ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላም አካሄደሐምሌ 18/20...
25/07/2026

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በኢሉ አባ ቦር ዞን የ16 ሚሊዮን ብር የሞዴል አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ግንባታ አስጀመረ፤ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላም አካሄደ

ሐምሌ 18/2018 (ኢሉ አባቦራ መቱ) — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በኢሉ አባ ቦራ ዞን በሁሩሙ ወረዳ በ16 ሚሊዮን ብር ወጪ የሞዴል አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ግንባታ ማስጀመሩንና በመቱ ወረዳ ጫቱ ክላስተር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማካሄዱን አስታወቀ።

አስተዳደሩ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የሕፃናት ት/ቤት ግንባታን ከመጀመር ባለፈ፣ የ1.1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶችን ለተማሪዎች ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል። በተጨማሪም የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውን የሻይ ቅጠልና የአቮካዶ ችግኞችን ከአስተዳደሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር ተክሏል።

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ አገር የመገንባት ብሄራዊ ጉዞን በመቀበል በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በአረንጓዴ አሻራ ልማት ላይ በንቃት እየተሳተፋ መሆናቸውን ገልጿል። ያስጀመሩት የአጸደ ህጻናት ሞዴል ት/ቤት ግንባታ አዲስን ትውልድ በስነ-ምግባርና በእውቀት ኮትኩቶ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ያለው ሲሆን፣ ይህ መሰል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአገር አንድነትንና ብዝሃነትን እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።

የኢሉ አባ ቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንደልካቸው ተፈሪ አስተዳደሩ ያለውን አቅም በማስተባበር በዞኑ የነገውን ትውልድ ለመቅረጽ የጀመረውን ሥራ አመስግነዋል። ግንባታው በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል በዞኑ ደረጃ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥላሁን አበራ በበኩላቸው፤ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገትና ልማት ያላት አገር ለመገንባት የአረንጓዴ አሻራ ልማት አማራጭ የሌለው ወሳኝ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሁሩሙ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ቸሩ ት/ቤቱ በወረዳው መገንባቱ በትምህርት ረገድ የሚታዩ መዋቅራዊ ክፍተቶችንና የመማር ማስተማር መቋረጥን ለማስተካከል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ሲገልጹ፣ የመቱ ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ አብዱ በቀለ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ ልማት አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የተማሪዎች ወላጆች እና በዕለቱ በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ በቤተሰብ ደረጃ የነበረውን የኢኮኖሚ ጫና ያስቀረላቸው መሆኑንና የችግኝ ተከላው የአገሪቱን የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ እድገት ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንዳለው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ኑ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ ለ2ኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ ተካሄደ==============//==============የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ሐም...
23/07/2026

ኑ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ ለ2ኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ ተካሄደ

==============//==============

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ሐምሌ 16 ቀን 2018 “ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለ2ኛ ጊዜ አካሄዱ።

አራት ኪሎ በሚገኘው ግንፍሌ ፓርክ ለ2ኛ ጊዜ በተከናወነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም የመሃል ሪጅን ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመጀመሪያው መርሃ ግብር ሐምሌ 3 ቀን 2018 በዚሁ ፓርክ የፍራፍሬና ሌሎችም የዕፅዋት ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል።

Address

Queen Elizabeth Street
Addis Ababa
1030

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share