06/09/2026
#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን!
መንግስት ባመቻቸው የሌማት ቱሩፋት መጠቀማቸውን ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡
**************************
(ጉለሌ ወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን 01/13/2018ዓ.ም)
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀን”ን ምክንያት በማድረግ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን የሚያፋጥኑ የዶሮ እና የኬጅ ስርጭት ተከናወነ።
በዕለቱ የመንግስትን የሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብር ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የገለጹት የወረዳው ነዋሪዎች የተደረገላቸው ድጋፍ በቤተሰብ ደረጃ አምራች ለመሆን እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ እንደገለጹት "የእመርታ ቀን" በርካታ ለውጦች የተመዘገቡባቸውና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውንና ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደ ማንሰራራት የምታደርገውን ጉዞ የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረው፤ በሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን በተግባር በማረጋገጥና በማስፋፋት የስራ እድል በመፍጠር የሀገርን ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበባው አለምነህ በበኩላቸው "የእምርታ ቀን" ሲከበር ህብረተሰባችንን ከተረጂነት አስተሳሰብ እና ተግባር በማውጣት በሁሉም መስኮች አምራች እና ራስን ወደ መቻል ማሸጋገርን አላማ ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፤ በኢኮኖሚ ራስን ከመቻል ባለፈ በገበታ ላይ የሚቀርበውን ምግብ በራስ አቅም ማምረት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴዎችን ጨምሮ የወረዳው አመራሮች፣ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ጉብኝትም ተካሂዷል።