Bole Woreda 14 Communication

Bole Woreda 14 Communication ይህ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው።

30/05/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!

ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።

እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።

ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።

ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።

#ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

27/05/2026
26/05/2026
26/05/2026
25/05/2026
"ለምርጫው ሰላማዊነት የበኩላችን እንወጣለን"7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ  ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ገልፀዋል።በቦሌ ...
24/05/2026

"ለምርጫው ሰላማዊነት የበኩላችን እንወጣለን"

7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ገልፀዋል።

በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር ለሰላም ሰራዊት አባላት ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ግንቦት 16/18ዓ.ም

ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውልድ የሚሆን አሻራ !!የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውል...
24/05/2026

ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውልድ የሚሆን አሻራ !!

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ የብልፅግና አሻራ ነው።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር በካፒቴን አበራ ለሚ የተሰራው የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም እውነተኛ የሀገር እና የወገን ፍቅር የሚለካው ለራስ በሚኖር ሕይወት ሳይሆን፣ ለሌሎች በሚተርፍ በጎነትና ለሀገር በሚተው ዘላቂ አሻራ መሆኑን ያሳየ ህያው ምስክር ነው።

የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ4,900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየም እና የእቃ ማከማቻ መጋዘንን ያካተተ ነው።

ይህ ዘመናዊ ስታዲየም መለስተኛ አለምአቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያለው ነው።

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስታዲየሙን መርቀው አገልግሎት ሲያስጀምሩ ‎የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ያስረከቡትን ካፒቴን አበራ ለሚን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ የአካባቢው ነዋሪዎችም እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ግንቦት 16/18ዓ.ም

24/05/2026

Address

Gerji Police Station
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Woreda 14 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bole Woreda 14 Communication:

Share