ቦሌ 13 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 13 Communication

ቦሌ 13 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 13 Communication Bole 13 Communication

«በትጋትና ጥረታችን፣የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» አከባበር የቀጠለ ሲሆን በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ልማ...
06/09/2026

«በትጋትና ጥረታችን፣የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» አከባበር የቀጠለ ሲሆን በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ልማት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች መስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል።

ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
ቦሌ ወረዳ 13 ኮምዩኒኬሽን ፅ/ቤት

#ጳጉሜ1 #የእመርታቀን #ኢትዮጵያታምርት #አዲስአበባታምርት #ቦሌክፍለከተማ #ወረዳ13

06/09/2026
«በትጋትና ጥረታችን፣ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀትና ተስፋ ሰጭ መንፈስ እየተከ...
06/09/2026

«በትጋትና ጥረታችን፣ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀትና ተስፋ ሰጭ መንፈስ እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉን ዓላማ አስመልክተው የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማንደፍሮ እንደገለጹት፤ የእመርታ ቀን ዋና ዋና ግቦች፡

የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፡-
በምግብ ራስን ለመቻል የተደረጉ ጥረቶችንና የተመዘገቡ ስኬቶችን ማሳየት።

የ«ኢትዮጵያ/አዲስ አበባ ታምርት» ንቅናቄ፡-የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ የተከናወኑ አበራች ተግባራትን ማጎላት፤

ታሪካዊ ሽግግር፡-ከተማችን ከተረጂነት እና ከጥገኝነት ወጥታ ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ጉዞ ማበሰር፤

የተስፋና የመነሳሳት መንፈስ፡-ለላቀ አገራዊ ውጤትና ለበለጠ ስኬት የህብረተሰቡን የመስራት ፍላጎት ማነቃቃት ናቸው።

የወረዳው ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ለማ ይህ ታሪካዊ ሽግግር በእያንዳንዳችን ትጋትና ጥረት የሚረጋገጥ በመሆኑ፣ ሁላችንም እጃችንን ለአምራችነት እና ለእድገት እንዘርጋ ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል።

ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
ቦሌ ወረዳ 13 ኮምዩኒኬሽን ፅ/ቤት

#ጳጉሜ1 #የእመርታቀን #ኢትዮጵያታምርት #አዲስአበባታምርት #ቦሌክፍለከተማ #ወረዳ13

06/09/2026

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

06/09/2026
የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ...
06/09/2026

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የውል ምዝገባና እድሳት ስራው እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ጊዜ ገደብ አስቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በጊዜው አሟልተው ያልቀረቡ፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ ምክንያት ከአዲስ አበባና ከሀገር ውጭ የነበሩ ተዋዋዮች መኖራቸውን ተረድቷል።በህብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት የመጨረሻ ተጨማሪ እድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ቢሮው ገልጿል።

በመሆኑም እስከ ዛሬ ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮችና ተከራዮች ይህንን የመጨረሻ እድል በመጠቀም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በክፍለ ከተሞች፣ በሁሉም የመሶብ አንድ ማዕከላት እና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ቦታዎች በመቅረብ ውላቸውን እንዲያድሱ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

የመጨረሻ እድል — ጊዜዎ ሳያልቅ ውልዎን ያድሱ!!

ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 !!
06/09/2026

!!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ለአዲሱ ዓመት በቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሁለቱም የሰንበት ገበያዎች ለነዋሪዎች እያቀረበ ነዋሪውም እየሸመተ ይገኛል።መጪውን የ2019 ...
05/09/2026

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ለአዲሱ ዓመት በቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሁለቱም የሰንበት ገበያዎች ለነዋሪዎች እያቀረበ ነዋሪውም እየሸመተ ይገኛል።

መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት አስመልክቶ የኅብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቅለልና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ሰፊ ዝግጅት በማድረግ መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ ስራ ተሰርቷል።በተለይም ለአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ የምግብ እህሎችን፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ሽንኩርት፣ እንቁላል እና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶችን በአነስተኛ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለወረዳው ነዋሪዎች ቀርቧል።

የወረዳ 13 ብርሃን ቦሌ ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ከምርት አቅራቢዎችና ከገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየኖች ጋር በቀጥታ በመስራት ያለምንም የደላሎች ጣልቃገብነት ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርሱ በማድረግ ላይ ነው። ይህም አሰራር በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሚፈጠር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በኅብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና እየቀነሰው ስለመሆኑም ተገልጿል።

ነሐሴ 30/2018
ቦሌ ወረዳ 13 ኮሙኒኬሽን

የሁለት ወረዳዎች የተቀናጀ ጥረት፤ ለበዓላት ሰላማዊ አከባበር ጠንካራ መሠረት!የመጪዎቹ የዘመን መለወጫ፣የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በፍቅር፣ በደስታ እና በሙሉ ሰላም ተከብረው እንዲያ...
04/09/2026

የሁለት ወረዳዎች የተቀናጀ ጥረት፤ ለበዓላት ሰላማዊ አከባበር ጠንካራ መሠረት!

የመጪዎቹ የዘመን መለወጫ፣የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በፍቅር፣ በደስታ እና በሙሉ ሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 እና ወረዳ 14 አስተዳደሮች በጋራ በመቀናጀት የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ሰጥተዋል።

በዚሁ ጥምር የፀጥታ ስምሪት ላይ የሁለቱም ወረዳዎች አመራሮች፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች እንዲሁም የሰላም ሰራዊት አባላት በስፋት የተሳተፉ ሲሆን፣ይኸው የተቀናጀ ስራ የበዓላቱን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ያለመ ነው።

በዓላቶቻችን የደስታ፣የፍቅር፣የይቅርታ እና የሕብረት መግለጫዎች ናቸው። ይሁን እንጂ የነዚህ እሴቶች ሁሉ መሠረትና ማደምቂያ ሰላም ነው። ሰላም በሌለበት ቦታ በዓልን በሙሉ ደስታ ማከበር አይቻልም።የአካባቢያችንን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ደግሞ የፀጥታ አካላት ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነው። የፀጥታ አካላት፣ የሰላም ሰራዊት እና ህብረተሰቡ እጅና ጓንት ሆነው ሲሰሩ የበዓላቱን የተቀደሰ እሴት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም ትልቅ አቅም መፍጠር ይቻላል ሲሉ መልክት ያስተላለፉት የወረዳ 13 ወና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማንደፍሮ ተመስገን ናቸው።

የወረዳ13 ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ለማ በበኩላቸው የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሌሊትና ቀን ለሚደክሙት የፖሊስ፣ የደንብ ማስከበር እና የሰላም ሰራዊት አባላት አስፈላጊውን ትብብርና ምስጋና መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመው አዲሱን ዓመት፣ የመስቀል ደመራንና የኢሬቻ በዓልን እርስ በእርስ በመረዳዳት፣በመከባበር እና ሰላምን በመስበክ በጋራ እንቀበል ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል።
#ወረዳ13 #ሰላምናጸጥታ #ዘመንመለወጫ2019 #መስቀልደመራ #እሬቻ

ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም
ቦሌ ወረዳ 13 ኮምዩኒኬሽን

Address

Addis Ababa

Telephone

+251116299896

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቦሌ 13 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 13 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ቦሌ 13 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 13 Communication:

Shortcuts

Share