13/01/2023
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለ11 ተቋማት የላቀ የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና ሰጠ
**********************
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በህክምና ላብራቶሪ፣ በፍተሻና ንጽጽር ዘርፍ ለ11 ተቋማት የላቀ የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና ሰጠ።
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መሰረት ተሰማ እንደገለፁት የላቀ ብቃት የጥራት ማረጋገጫ አክሬዲቴሽን የተሰጣቸው በህክምና ላቦራቶሪ እንዲሁም በፍተሻና ካሊብሬሽን፣ የሚጠበቅባቸውን የሙያና ክህሎት ደረጃ መድረሳቸው ለተረጋገጠ ተቋማት ነው።
የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር፣ የሸጋው ሞጣ ጄነራል ሆስፒታልና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል ትናንት በአዳማ አክሬዲቴሽን ከተሰጣቸው መካከል መሆናቸውን አንስተዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የብሔራዊ የሳንባ ነቀርሳ ላቦራቶሪና የኢትዮጵያ ቴክስታይል ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም የላቀ የጥራት ማረጋገጫውን ካገኙት መካከል መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
የጥራት ማረጋገጫው የሀገር ውስጥና የወጭ ምርቶች ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲዘምኑ እንዲሁም ምርትና ምርታማነት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮችን ለመፍታት ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/