Women's Wing HQ - የሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት

Women's Wing HQ - የሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት This is the Official page of Prosperity Party Women's Wing HQ. ይህ የብልፅግና ሴቶች ክንፍ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡

03/09/2026
03/09/2026
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ያጠናክራል።   ሳሚያ አብደላ የኦሮሚያ ብልጽግና ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊበጎነት ለእህትማማችነት በሚል መሪ ቃል በብልጽግና ፓርቲ...
31/08/2026

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ያጠናክራል።
ሳሚያ አብደላ የኦሮሚያ ብልጽግና ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

በጎነት ለእህትማማችነት በሚል መሪ ቃል በብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተጀመረው የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሁሉም ክልሎች በሁሉም የትኩረት መስኮች እየተተገበረ ይገኛል።

የበጎ ፈቃድ ባህል በማድረግ የመረዳዳት፣የመተሳሰብና የህዝብን አብሮነትና ትስስር በማጠናከር የተሻለች ሀገር ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ አለው።
የኦሮሚያ ክልል የሴቶች ክንፍ በባሌ ሮቤ በተለያዩ ድጋፎችና ኩነቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን አከናውነዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከህሊና እርካታ ባለፈ ማኅበራዊ ትስስርን እያጎለበተ መምጣቱም በወቅቱ ተመላክቷል።

‎በጎነት ለእህትማማችነትና ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት! ‎‎​የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ በንሳ ዋሬ ቀበሌ ሰው ተኮር የበጎ አ...
28/08/2026

‎በጎነት ለእህትማማችነትና ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት!

‎​የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ በንሳ ዋሬ ቀበሌ ሰው ተኮር የበጎ አድራጎት ስራዎችን አከናውነዋል።

‎​ በዚህ የክረምት የበጎ ፍቃድ መርሐ ግብር የቤት እድሳት፦ ለአቅመ ደካማ እናቶች የሚሆኑ የቤት እድሳት ቁሳቁሶች ድጋፍና የእድሳት ስራ ፣ የአልባሳት ድጋፍ እና አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ የደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

‎​በዕለቱም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ኤርሚያስ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዘውዲቱ ዘለቀ እንዲሁም የምስራቃዊ ሲዳማ ዞንና የክንፉ አመራሮች ተገኝተው ድጋፉን አስተባብረዋል።

27/08/2026
ለእሰልምና እምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳቹሁ  ።መልካም በዓል
25/08/2026

ለእሰልምና እምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳቹሁ ።
መልካም በዓል

22/08/2026
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በሀዲያ ዞን ፎንቆ ከተማ  ለአቅመ ደካማ እናቶች እና ተማሪዎች ድጋፍ ተበረከተ።ለአቅማ ደካማ እና...
21/08/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በሀዲያ ዞን ፎንቆ ከተማ ለአቅመ ደካማ እናቶች እና ተማሪዎች ድጋፍ ተበረከተ።

ለአቅማ ደካማ እናቶች እና ተማሪዎች ከ380 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የደብተር ፣እስኪሪብቶ ፣የሴቶች ንፁህና መጠበቂያ፣ የምግብ ዱቄት እና የምግብ ዘይት ድጋፍ ተበርክቷል።

ድጋፉ ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪካ ባደረገ ወጣት ባለሀብት አቡሽ ብርሃኑ የተበረከተ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በድጋፉ መሳተፋቸውም ተጠቁሟል።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር ባስተላለፉት መልዕክት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰው ተኮር የሆነ የመደመር መንግስት እሳቤ መሬት ላይ መውረዱን በግልፅ የሚያሳይና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ የሚገኝ የቅን ልቦች ወጤት መሆኑንም ጠቁመዋል።

በጎነት መልካም ልብ ያላቸው ሰዎች ተግባር ስለመሆኑ የተናገሩት አቶ በረከት፣ ወጣት አቡሽ ያደረገው ተግባር የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይህን ተግባር ይበልጥ በየአካባቢው አጠናክሮ በማስቀጠል እርስ በእርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ማጎልበት ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ በበኩላቸው፣ የሴቶች ክንፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልገሎትን በክልሉ በሁሉም መዋቅር በተቀናጀ መንገድ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በክልሉ በ14 የስራ ስምሪት መስኮች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሴቶች ክንፍ በተቀናጀ መንገድ እየተከናወነ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

ከሀገር ውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውንን ጭምር በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ የማሰበሰብ ተግባር በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተግባሩን ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።

የመደጋገፍ ባህላችንን ይበልጥ ማጎልበት ይገባል ያሉት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ፣ በዚህ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፉና ያስተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።

በጎነት ለህትማማችነት ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ! የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አመራሮች በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ የአቅመ ደካማ እናት የቤት ግንባታ አስጀመረዋል።የሲዳማ ክ...
19/08/2026

በጎነት ለህትማማችነት ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት !

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አመራሮች በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ የአቅመ ደካማ እናት የቤት ግንባታ አስጀመረዋል።

የሲዳማ ክልል የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች "በጎነት እና እህትማማችነት ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ የአቅመ ደካማ እናት የቤት ግንባታ አስጀምረዋል።

የሲዳማ ክልል የሴቶች ክንፍ አመራሮች "በጎነት እና እህትማማችነት ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወኑ ይገኛል።

የሲዳማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች በአስተዳደር ብቻ የሚለያዩ ወንድማማች ሕዝቦች መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን መሰል የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር መድረኮች በሲዳማ ክልል እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለፉት ስምንት የለዉጥ አመታት ባህል እየሆነ የመጣ ተግባር መሆኑ በመርሃ-ግብሩ ተገልጿል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ስምንት የለዉጥ አመታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የተቸገሩ ወገኖችን የመርዳት እንቅስቃሴ በሁሉም መዋቅሮች በስፋት እየተተገበረ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።

በመርሃ-ግብሩ በተያዘዉ አመት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የአንዲት አቅመ ደካማ እናት የቤት ግንባታ በብሎኬት የተጀመረ ሲሆን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርም ተከናውኗል።

በተጨማሪም የግንባታ፣ የትምህርት መርጃና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Women's Wing HQ - የሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Women's Wing HQ - የሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share