Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት ገፅ ነው።
(1)

The page belongs for Addis Ababa Education Bureau and it works for the transfer of educational information for the public.

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነውከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡...
06/09/2026

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

ከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የጸደይ መዳረሻን ለማብሰር ከሚከናወኑ ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “የጎቤ” እና “ሺኖዬ” ጨዋታ ተጠቃሽ ነው ሲል አዲስ ሚዲያ ኔቶርክ ዘግባል።

የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ-ምግባር የማጎልበትና የማነፅ ሀላፊነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ።(ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም) ‎በአዲስ አበባ ከተማ አ...
06/09/2026

የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ-ምግባር የማጎልበትና የማነፅ ሀላፊነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ።

(ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም) ‎በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብርሃን ዓይነ- ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት እንደከተማ ለ33ኛ ጊዜ እንደትምህርት ቤት ለ2ኛ ጊዜ"ብሩህ ነገን በዛሬው አዕምሮዎች!" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ጉባኤ የትምህርት ቤቱ አመራሮች መምህራን እና ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል ።

የትምህርት ቤቱ አካዳሚክ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሆርዶፋ በጉባኤው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተማሪዎችን በውጤት እና ስነ-ምግባር የማነፅ ሀላፊነት ስላለበት በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሱፐርቫይዘር አቶ ፀጋዬ አሰፋ በበኩላቸው የነበሩትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ጉድለቶችን በመሙላት በቀጣይ የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ ጥረታችንን አጠናክሰን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ ውባለም ደበበ የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ የውጤት መግለጫ እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፣ የ2018 የትምህርት ዘመን አፈፃፀም በጥንካሬ እና በእጥረት የሚነሱ ጉዳዮች፣በቀጣይ የትምህርት ዘመን በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራት ፣የጉባኤ የትኩረት ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ማብራሪያ በመስጠት ለስኬታማ ስራ መትጋት ይገባል ብለዋል።

በመቀናጀት ፣ በመናበብ ችግሮችን በወቅቱ በመፍታት በመወያየትና ያለን እውቀት ግንዛቤና ችሎታ ጊዜ ለተማሪዎች መማር በማዋል ሀገራዊ፣ ህሊናዊና ሰብዓዊ ኃላፊነት በባለቤትነት ስሜት መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።


ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

በፈጠራና በዲጂታል እውቀት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት ከምንጊዜውም በላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ። (ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም) ‎የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት "ብሩህ ነገን ...
06/09/2026

በፈጠራና በዲጂታል እውቀት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት ከምንጊዜውም በላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

(ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም) ‎የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት "ብሩህ ነገን በዛሬ አእምሮዎች!" በሚል መሪ ሀሳብ 33ኛውን የትምህርት ጉባኤ አካሄዷል።

በጉባኤው ላይ የትምህርት ፅ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ በክፍለ ከተማው በትምህርት ጥራት፣ በክፍል አደረጃጀት እና በወላጆች ተሳትፎ ረገድ በርካታ ስራዎችን መከናወናቸውን ጠቁመው በፈጠራና በዲጂታል እውቀት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት ከምንጊዜውም በላይ በቅንጅት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

አክለውም ለተማሪዎች የተሻለ ትምህርት ለመስጠት እያደረግን ላለው ጥረት ሁሉ ከጎናችን ለሆናችሁ አካላት ምስጋናዬ የላቀ ነው በማለት በጉባኤው ፍሬያማ ውይይቶችን በማድረግ ውጤታማ ውሳኔዎች ላይ እንደሚደርስ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉ ተናግረዋል ።


ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

የእመርታ ቀን አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

06/09/2026

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ለ2019 የትምህርት ዘመን የሚሆኑ የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን ለትምህርት ተቋማት በማከፋፈል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን ተገለ...
05/09/2026

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ለ2019 የትምህርት ዘመን የሚሆኑ የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን ለትምህርት ተቋማት በማከፋፈል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን ተገለጸ።

(ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ለ23 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ካሰራጫቸው የትምህርት ግብአት ውስጥም 66 ሺህ 830 ባለመስመር የተማሪ መማሪያ ደብተሮች ፣ 7 ሺህ 363 የስኩዌር ደብተሮች ፣ 15 ሺህ 926 የስዕል ደብተሮች እና የተለያዩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ መለማመጃ መጻሕፍት ይገኙበታል።

እነዚህ የትምህርት ግብዓቶች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለተማሪዎች በእጃቸው እንዲደርስ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

መንግስት ከዚህ ቀደም ከጀመራቸው አበይት ማህበራዊ ድጋፎች መካከል አንዱ የሆነው የነፃ የተማሪዎች ምገባ መርሃ-ግብር ተማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ ትምህርታቸው ብቻ እንዲያደርጉ ትልቅ እገዛ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል።

መንግስት ከዚህ የነፃ ምገባ ባሻገር አሁን ላይ እነዚህን አስፈላጊ የመማሪያ ግብዓቶች በነፃ ማቅረቡና ማሰራጨቱ ለትምህርት ቤቶችና ለተማሪዎች ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ እንደሆነም ተመላክቷል።

ይህ ድጋፍ በተለይም ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው የተማሪ ወላጆች በየዓመቱ መጀመሪያ ላይ የትምህርት ቁሳቁስ ግዢን አስመልክቶ የሚገጥማቸውን የገንዘብ ጫና እና ስጋት የሚቀንስ በመሆኑ ትምህርታቸውን ያለምንም ስጋት እንዲከታተሉ የሚያስችል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የተማሪዎች ዩኒፎርም በሁሉም የትምህርት ተቋማት እየገባ እና በቀጥታ ለተማሪዎች እየተሰራጨ መሆኑ ትምህርት ቤቶች ለአዲስ ዓመት የመማር ማስተማር ሂደት ያደረጉትን ዝግጅት የተሟላ አድርጎታል።

ይህ ሁሉ አቀፍ ድጋፍና ቅድመ ዝግጅት ተማሪዎች ያለምንም እንከንና በሰዓቱ ወደ ትምህርት ገበታቸው በመግባት ውጤታማ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aebc

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል:: ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።

በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እየተሻሻለ መምጣቱን ባለድርሻ አካላት ተናገሩ። (ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) ‎የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/...
05/09/2026

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እየተሻሻለ መምጣቱን ባለድርሻ አካላት ተናገሩ።

(ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) ‎የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎች በማከናወን በአዕምሮ የበለፀገ ትውልድን ለማፍራት ዘርፈብዙ ተግባራት ማከናወኑን ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት ገልፀዋል።

በክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት በ2018 በጀት አመት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ከመፍጠር በተጨማሪ የትምህርት መሰረተ ልማቶች፣ የትምህርት ለትውልድ ስራዎች፣ ማህበራዊ ፍትህ ለማስፈን የተማሪዎች ምገባ ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውን ባለድርሻ አካላት ተናግረዋል።


የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው ትምህርት የነገው ሀገር ተርካቢ ትውልድ ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር በማሻሻል፣ ሰፋፊ የትምህርት ቤት ማስፋፍያዎች በመገንባት፣ የተምህርት ግብአቶች በሟማላት፣ እንዲሁም ሰለማዊ የመማር ማስተማር በመፍጠር በፈጠራ የተካነ ትውልድ በመገንባት ረገድ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም በክፍለ ከተማውም የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነት ለማስፋት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ380 ሚሊየን ብር በላይ ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ የትምህርት ቤት ደረጃ የማሻሻል፣ ት/ቤቶች ከፈረቃ ትምህርት ለማስቀረት የሚያስችሉ አዳዲስና የማስፋፊያ የትምህርት ቤቶች ግንባታዎች ስራ መሰራቱንም ገሌፀዋል።

በክፍለ ከተማው ያለፈው አመት የትምህርት ጉባኤ አፈፃፀምና 33ኛው የትምህርት ጉባኤ የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ የትምህርት አመራሮች፣ በዘርፉ ያሉ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂደዋል ፡፡


ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡(ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን 33ኛው ...
05/09/2026

የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡

(ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን 33ኛው የትምህርት ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል።

ጉባኤው "ብሩህ ነገን በዛሬው አእምሮዎች!" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ ሙሉነህ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የትምህርት አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች ፣ የተማሪ ወላጅና መምህራን ማህበር አመራሮች ፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል የትምህርት ጉባኤው በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ጠንካራ ስራዎችን ለማስቀጠል እና በሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በ2019 ዓ.ም የትምህርት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚቀርቡበት መሆኑን ጠቁመው በክፍለ ከተማው በ2018 ዓ.ም በ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል የተመዘገበው አበረታች ውጤት በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የከተማ አስተዳደሩና ቢሮው እንዲሁም በየደረጃው ያለው የትምህርት መዋቅር ለተማሪዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ማረጋገጥ ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና የትምህርት ዘርፉ የጀርባ አጥንት መሆኑን በመገንዘብ የባለድርሻ አካላትን ከፍተኛ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል:: አያይዘውም በክፍለ ከተማው ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት የመምህራን ተጠቃሚነትንና አቅም ማሳደግ እንዲሁም ተማሪዎች ሰላማዊ በሆነ አካባቢ ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አብራርተው እቅዱ ግብ እንዲመታ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ::

በመርሀ ግብሩ ላይ በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችና የተማሪዎች ውጤት ትንተና ሪፖርት እንዲሁም የ2019 እቅድ በክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት አስተባባሪ ወ/ሮ ደመቁ ገረመው አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

Address

6 Kilo Near Anbesa Gibi
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:30
Tuesday 02:30 - 23:30
Wednesday 02:30 - 23:30
Thursday 02:30 - 23:30
Friday 02:30 - 23:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Education Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share