26/08/2026
በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጃን ሜዳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አመራርና አባላት ታካሚዎችን ጎበኙ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጃን ሜዳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አመራርና አባላት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት በሆስፒታሉ የሚገኙ ታካሚዎችን ጎበኙ።
የጃን ሜዳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ስጦታው ቡጤ ታካሚዎች በተጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ፖሊስ መምሪያው እንደዚህ ያሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ፖሊስ ከተሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በመሰል ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያደርገው ተሳትፎ አንዱ ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የፖሊስ መምሪያው የወንጀል መከላከል ም/መምሪያ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር ተሬሳ ጋዲሳ የፖሊስ ተግባር ወንጀልን መከላከልና ህግን ማስከበር ብቻ ሳይሆን፣ ማህበራዊ ኃላፊነትንም መወጣት በመሆኑ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የህንፃ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፊራፊስ አቡና በበኩላቸው ፖሊስ በሆስፒታሉ በመገኘት ያደረገው ድጋፍ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የህዝብ አገልግይነቱም አንዱ ማሳያ ነው ብለው ሆስፒታሉና ፖሊስ መምሪያው በጤናና በማህበራዊ ጉዳዮች በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
የፖሊስ መምሪያው አመራርና አባላትም ለታካሚዎች ምግብና መጠጦችን በስጦታ በማበርከት ከህመማቸው እንዲፈወሱም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹