የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር   Ministry of Women and Social Affairs Holistic benefit and social protection of citizens for national prosperity!
(1)

ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት‎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ምስጋናቸውን ገለፁ‎****** ‎‎የኢፌዴሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ኢ...
03/08/2026

ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት‎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ምስጋናቸውን ገለፁ
‎******

‎የኢፌዴሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን ላሳዩት የላቀ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆትና ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

‎ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።

‎በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡

‎በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለፅ አመስግነዋል፡፡

‎ኢትዮጵያውያን ላሳዩት ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉንም በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)***********************ዛሬ ኢትዮጵያ 800 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለመትከል አቅዳ ከ805 ሚሊዮን በላይ ች...
03/08/2026

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***********************

ዛሬ ኢትዮጵያ 800 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለመትከል አቅዳ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል ማሳካቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል።

እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ
03/08/2026

እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ

የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ለመትከል የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለማሳካት ከ5ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል******************የሴቶችና ...
03/08/2026

የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ለመትከል የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለማሳካት ከ5ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል
******************
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ ታዳጊ ህፃናት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ ጥሪን በመቀላቀል ከአምስት ሺህ በላይ ችግኞችን በጋራ ተክለዋል።

በዕለቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሀገሪቱ የጀመረችውን የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም እና የደን ሽፋን የማሳደግ እንቅስቃሴ አካል ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም እያደገ የመጣው የደን ሽፋን ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የህፃናት እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ልዩ ድምቀት የሰጠው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ህፃናት በችግኝ ተከላው ላይ በንቃት በመሳተፋቸው የተፈጥሮ አካባቢን የመንከባከብ ባህል ለተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

በተጨማሪም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉትን ተክሎች መንከባከብ እና ማሳደግ ለነገዋ ኢትዮጵያ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የማህበረሰብ ተሳትፎን ያማከሉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችንና እና የማህበራዊ ደህንነትን የማረጋገጥ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

በዕለቱ 7 የደን አይነቶች የተተከሉ ሲሆን ከ200 በላይ በጎ ፈቃድኛ ወጣቶች፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን እና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል።

ሐምሌ 27 ‎ ! በሚል መሪ ሃሳብ በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ሌላ ታሪክ ለመስራት እኔ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?‎‎የተያዘው ይህ ታላቅ ሀገራዊ ግብ እንዲሳካ የተቋሙ ሰ...
02/08/2026

ሐምሌ 27 ‎ ! በሚል መሪ ሃሳብ በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ሌላ ታሪክ ለመስራት እኔ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?

‎የተያዘው ይህ ታላቅ ሀገራዊ ግብ እንዲሳካ የተቋሙ ሰራተኞችና መላው የሀገራችን ሴቶች፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች በእለቱ በነቂስ በመውጣት በችግኝ ተከላ እንድትሳተፉና የዜግነት ድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

‎ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

  !
02/08/2026


!

እኛ ተዘጋጅተናል፤ እናንተስ?በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በጋራ የምንተክልበት የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀረው። እኛ ተዘጋጅተናል፤ እናን...
02/08/2026

እኛ ተዘጋጅተናል፤ እናንተስ?
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በጋራ የምንተክልበት የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀረው። እኛ ተዘጋጅተናል፤ እናንተስ?

የፀጥታ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ
02/08/2026

የፀጥታ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ

የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ
02/08/2026

የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ

02/08/2026

Address

Arat Kilo, Behind Tourist Hotel
Addis Ababa
1293

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115528394

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs:

Shortcuts

Share