አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .

አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . ይጎብኙን አብረን ለለውጥ እንስራ የመረጃ ምንጮች ነን ።

የቀበና ኮሪደር ልማት ለስፖርተኞች እና ለወጣቶች አዲስ የሰብአት ስፍራ መሆኑ የካራቴ የስፖርት ቤተሰቦች ገለጹነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮበአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳ...
02/09/2026

የቀበና ኮሪደር ልማት ለስፖርተኞች እና ለወጣቶች አዲስ የሰብአት ስፍራ መሆኑ የካራቴ የስፖርት ቤተሰቦች ገለጹ
ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የተገነባው የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት በስፖርት ቤተሰቦች፣ በአሰልጣኞች እና በወጣቶች ዘንድ ተመራጭ የሰብአት ስፍራ ነው ሲ,ሉ የካራቴ ስፖርት ቤተሰቦች ገለጹ

ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ ካራቴ ፌዴሬሽን የተውጣጡ የስፖርት ቤተሰቦች፣ አሰልጣኞች እና ታዳጊ ስፖርተኞች በቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በተከናወነው ልዩ የስፖርታዊ እግር ጉዞ ፕሮግራም ላይ ነው።

ፕሮጀክቱ ያካተታቸው ማራኪ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ ለስነ-ልቦና እረፍትና ለወጣቶች ሁለንተናዊ በጎ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኝ የካራቴ ስፖርተኞች ገልጸዋል፡፡

"የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ውበት መስጠቱ ብቻ ሳይሆን፣ ስፖርተኞችና ታዳጊዎች ከአዳራሽ ውጭ ንጹህ አየር እየተነፈሱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችንና የተለያዩ አርቶችን ለማሳየት እና ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አክለዋል፡፡

ቀደም ሲል ተከልለውና ለአካባቢ ብክለት ተጋልጠው የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ዘመናዊ የስፖርት፣ የብስክሌትና የእግር ጉዞ መስመሮች መለወጣቸው ለአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ለታዳጊዎችና ለወጣቶች ምቹ የሰብዕት ቦታ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

02/09/2026

"መጪው ጊዜ የወጣቶች ነው"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሀዋሳ ከተማ የወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወኑ እና የሲዳማን ባህላዊ እሴቶች እየጎበኙ ይገኛሉነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስ...
02/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሀዋሳ ከተማ የወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወኑ እና የሲዳማን ባህላዊ እሴቶች እየጎበኙ ይገኛሉ

ነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሀዋሳ ከተማ በመገኘት ማህበራዊና ሰብአዊ ድጋፎችን ያካተተ የወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በስኬት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ወጣቶቹ ከተማዋን በበጎ ፈቃድ ከማገልገል ባለፈ በከተማዋ የሚገኙ ታሪካዊና ባህላዊ መዳረሻዎችን በመጎብኘት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን እና የኢትዮጵያን የበለጸገ የባህል ብዝሃነት በቅርበት እያዩ ይገኛሉ።

በጉዞአቸው ማዕቀፍ ውስጥ ወጣቶቹ የሲዳማ ባህል ማዕከልን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የሲዳማን ህዝብ ልዩ ታሪክ፣ የዘመን መለወጫ በዓል አከባበር ስነ-ሰርዓቶች፣ ባህላዊ እሴቶች እና የዕደ-ጥበብ ስራዎች በስፋት ተመልክተዋል።

ይህ ተሞክሮ ወጣቶቹ የሀገራቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ባህልና መስተንግዶ በቅርበት እንዲያውቁ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በከተሞች መካከል ያለው ወንድማማችነት እና አብሮነት ይበልጥ እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አድርጓል።

የበጎ ፈቃድ ጉዞው ተሳታፊ ወጣቶች በሀዋሳ ቆይታቸው ከተለያዩ ማህበራዊ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት አርአያነት ያላቸው ሰብአዊ ስራዎችን ማከናወናቸውን ገልጸው፣ የባህል ማዕከል ጉብኝቱ ሀገራዊ ማንነታቸውንና አንድነታቸውን ይበልጥ እንዳጠናከረላቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወጣቶችን በከተማቸው ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በሀገራዊ አብሮነትና በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ ለማጠናከር መሰል ሁለገብ መርሃ ግብሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

ማዕከላት የሀገርን ባህልና እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ተገለጸ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ውስጥ...
02/09/2026

ማዕከላት የሀገርን ባህልና እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ተገለጸ

ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ውስጥ የሚሰሩና የሚሰለጥኑ የኪነ ጥበብ ቡድኖች የሀገርን ባህል፣ ወግና እሴት ለትውልድ በማስተላለፍና በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ማዕከላቱ ታዳጊዎችን በስነ-ምግባርና በስብዕና ከመቅረጽ ባለፈ፣ የተለያዩ ባህላዊ ክህሎቶችንና ትርኢቶችን እንዲያዳብሩ እያደረጉ እንደሚገኙ የተገለጸው፣ ቡሄን አሸንዳ አሸንድዬንና ሶለልን ቱፊታዊ ባህላትንም በደመቀ ሁኔታ በተከበረበት መድረክ ላይ ነው።

በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 ወጣት ስብዕና መገንቢያ የሚገኘው የፊደል የኪነ ጥበባት ቡድን ከአባላትና ቤተሰቦቻቸው በዓሉን ከማክበር ባለፈ የወደፊት ጉዞውን የሚያጠናክር ሰፊ ውይይት አካሂዷል

በመድረኩ ላይ እንደተመለከተው፣ የተለያዩ አካባቢዎች ባህልና እሴት በሚንጸባረቅባቸው መድረኮች በመሳተፍ የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነት እንደሚያጠናክሩ ተመልክቷል

የኪነ ጥበብ ፍቅር ያላቸው ታዳጊዎች በታናሽ እድሜያቸው የራሳቸውን ባህል አውቀው በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ዘመናዊነትን ከባህል ጋር አዋህደው የሚሄዱ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ተመልክቷል።

ማዕከላቱ ታዳጊዎች ትርፍ ጊዜያቸውን ከአልባሳትና ከጎጂ ልማዶች ነጻ በሆኑ ጠቃሚ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲያወሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተዳራሽነት በመጨመር በርካታ ታዳጊዎች የባህልና የስብዕና ግንባታ ስልጠናዎች ተፎካካሪና ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የኢንተርናሽናል ትራዲሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን የስፖርት ቤተሰቦች የቀበና የልማት ፕሮጀክትን ጎበኙነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንተርና...
02/09/2026

የኢንተርናሽናል ትራዲሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን የስፖርት ቤተሰቦች የቀበና የልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ

ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንተርናሽናል ትራዲሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን የስፖርት ቤተሰቦች፣ አሰልጣኞች እና ታዳጊዎች በአዲሱ የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የእግር ጉዞ አካሄዱ

አሶሴሽኑ ያካሄደው የእግር ጉዞ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ የሆኑ የከተማ አከባቢዎችንና የማህበረሰብ ልማቶችን ለማወቅ፣ እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቡ በከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማጠናከር የተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል።

በጉብኝቱ ላይ የትራዲሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ወዳጆች የተገኙ ሲሆን፣ በቀበና ፕሮጀክት የተሰሩ የመዝናኛ፣ የጤና እና የነጻ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጊያ ስፍራዎችን ተዘዋውረው ተመልከተዋል።

በእግረኛ መንገድ፣ በወንዝ ዳርቻ ውበት እና ለዜጎች ምቹ በሆነ መልኩ በተገነቡት የስፖርት ማእከላት የተደሰቱት የስፖርት ቤተሰቦቹ፣ መሰል ፕሮጀክቶች ለአካላዊና አእምሮአዊ ጤንነት ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድናቀዋል።

አሶሴሽኑ ወደፊትም የትራዲሽናል ቴኳንዶ ስፖርትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን፣ ማህበረሰባዊ እና አካባቢን መሠረት ያደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በመገኘት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጡነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖ...
02/09/2026

የአዲስ አበባ ወጣቶች በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በመገኘት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጡ

ነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ከተማቸውን አልፈው በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀዋሳ ከተማ በመገኘት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በታላቅ የክብር ስሜት እየወጡ ይገኛሉ።

ወጣቶቹ በከተማው በሚኖራቸው አጠቃላይ ቆይታ የተለያዩ ማህበራዊና ሰብአዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን የሚያከናውኑ ሲሆን በጉዞአቸውም ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው "ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን የአረጋውያን መረጃ ማዕከል" በመገኘት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል።

ከተመሰረተ 10 ዓመታትን ያስቆጠረው እና ለአቅመ ደካማ አረጋውያን እንዲሁም ለህፃናት ዘላቂ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየውን ይህንን ታሪካዊ ማዕከል የጎበኙት ወጣቶቹ፤ የእናትና አባቶችን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ከመከባከብ ጀምሮ ማዕከሉ በምግብ እጥረት እንዳይቸገር የተለያዩ የምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አበርክተዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ወጣቶቹ ላሳዩት የላቀ የሰብአዊነት እና የርህራሄ ስሜት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ም/ቢሮ ሀላፊው በሰጡት አስተያየት
"የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበራዊ እሴቶቻችንን፣ መተሳሰብን እና አብሮነትን በባህሪያቸው ያጸኑ በመሆናቸው ድንበር ተሻግረው በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ አረጋውያን አባቶችና እናቶች እያደረጉት ያለው የበጎ ፈቃድ ስራ እጅግ ኩራት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በጎነት የኢትዮጵያውያን መለያ በመሆኑ ወጣቶቻችን ይህንን መልካም እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሸጋገር ረገድ ግንባር ቀደም ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ክብረአለም ቢሮአችንም እንዲህ ያሉ የሰብአዊነት ስራዎችን ሁልጊዜም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ጉዟቸው ማዕከሉን በመደገፍና አረጋውያንን በመንከባከብ የተጀመረው ይህ በጎ አድራጎታዊ ተግባር በቆይታቸውም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ወጣቶቹ በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ማህበራዊ ልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ አርአያነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።

የወደፊቶቹ ኮከቦች በቀበና ኮሪደር ልማትና አረንጓዴ ስፍራ የእግር ጉዞ አካሄዱነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮየታዳጊ ስፓርት ልማት ሰልጣኞች ከእንጦጦ ኮሪደር እስከ ቀበ...
02/09/2026

የወደፊቶቹ ኮከቦች በቀበና ኮሪደር ልማትና አረንጓዴ ስፍራ የእግር ጉዞ አካሄዱ

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የታዳጊ ስፓርት ልማት ሰልጣኞች ከእንጦጦ ኮሪደር እስከ ቀበና ድረስ በተዘረጋው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት የእግር ጉዞ አካሄዱ

15ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የቀበና ፕሮጀክት ምቹነት ብቻ ሳይሆን፣ ለታዳጊ ስፖርተኞች የክህሎት ለማሳደና የአካል ብቃታቸውን ለማጠናከር አዲስ ዕድል መፍጥሩ ተመልክቷል።

በጉብኝቱ የተሳተፋ ታዳጊዎች የአረንጓዴ ልማት፣ የሕዝብ መዝናኛ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ የለወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት የልማት ስራ አነቃቂ መሆኑን የጠቀሱት ታዳጊዎቹ ፣ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ አብራርተዋል።

የእንጦጦ-ቀበና ኮሪደር ልማት አዲስ አበባን ለአየር ንብረት ተስማሚ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የተዋበች ከተማ ለማድረግ ከታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሐዋሳ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸውነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ምወጣቶችና ስፖርት ቢሮ«በጎነት ለኢ...
01/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሐዋሳ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ምወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

«በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የወሰን ተሻጋሪ እና ሀገራዊ ትስስርን የሚያጠናክር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት ሐዋሳ ከተማ ያቀኑ ሲሆን ከተማዋ ሲደርሱም በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም በአካባቢው ወጣቶች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የሲዳማ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች የወሰን ገደብን ሰብረው በመምጣት በሐዋሳ ከተማ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በመሆን የሚያከናውኑት የበጎ ፈቃድ ስራ ማህበራዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም፣ ወጣቶቹ ከሚያከናውኑት ሰብአዊ ስራ ባሻገር በሁለቱ ከተሞች ወጣቶች መካከል ያለው አንድነት፣ አብሮነት እና የዘመናት ወንድማማችነት ይበልጥ የሚጠናከርበት ትልቅ ድልድይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የቢሮው ተወካይ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምንም አይነት የጂኦግራፊ ወሰን እና ድንበር እንደሌለው ገልጸዋል።

እውነተኛ በጎ ፈቃደኛ ለመሆን ሰብአዊነት እና ሰው መሆን ብቻ በቂ መሆኑን በመጥቀስ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች አሁን ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንደ መልካም ስነ-ምግባር እና ባህል እያዳበሩት መምጣታቸውን አስገንዝበዋል።

አቶ ዳዊት አክለውም ይህ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አሰራር በወጣቶች ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን በዘላቂነት የሚያጠናክር፣ ሀገራዊ መተሳሰብን የሚያጎለብትና የጋራ የሆኑ የወል ትርክቶቻችንን ከፍ የሚያደርግ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች በሐዋሳ ቆይታቸው የአረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ፣ የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላና እንክብካቤን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን የሚያከናውኑ ሲሆን ከሐዋሳ ወጣቶች ጋር በመሆንም የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ሀገራዊ ሚና አስመልክቶ ጥልቅ የፓናል ውይይት እንደሚያደርጉ አቶ ክብረአለም ደምሴ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አሳውቀዋል።

ይህ መርሃ ግብር ወጣቶች በጉልበታቸውና በእውቀታቸው ማህበረሰባቸውን ከማገልገል ባለፈ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት መልዕክት የሚያስተላልፉበት ትልቅ መድረክ ነው።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share