Addis Ababa City Roads Authority /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Addis Ababa City Roads Authority /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን This is Addis Ababa City Roads Authority's official face book page. Respected followers of the page,please get verified information here.

We appreciate if you could invite others to like our page.

07/09/2026
07/09/2026

ጳጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን"

አዲስ አበባ ከተማ በከፍታ ወደ ሁለንተናዊ ማንሰራራትና የቱሪዝም መሻገሪያ

ከተማችን አዲስ አበባ ባለፉት ዓመት ታላላቅ ፕሮጀክቶቸን በስኬት በማከናወን የማንሰራራት ጉዞዋን በተግባር አረጋግጣለች። ከተማዋ ለዘመናት የተጫናትን አስቸጋሪ ገፅታ በመቀየርና ታሪካዊውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በስኬት በመፈፀም ከተማዋን ተመራጭ የቱሪዝም መሻገሪያ በማድረግ እንዲሁም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ ብሎም ፅዱና አረንጓዴ ከተማ በመፍጠር መዲናዋን ወደ ሁለንተናዊ ዕድገት ተሸጋግራለች፡፡

በተለይም በመዲናዋ የተከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የዜጎችን የመኖርና የመስራት ክብር ያረጋገጡ፣ የከተማዊ ሁለንተናዊ ማንሰራራትን እውነታነት የመሰከሩ የከተማዋን የገቢ አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ያሻገሩ ደማቅ ስኬቶቻችን ለመሆን ችለዋል። በሁሉም ዘርፎች የላቀ ስራ ያስመዘገበችው መዲናችን አዲስ አበባ ከመሰረተ ልማት ስራዎች በተጨማሪ ባከናወነችው ሰው ተኮር ግዙፍ ፕሮጀክት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና ለሰው ክብር ቅድሚያ በመስጠት የተዘነጉና ትኩረት ያልተሰጣቸውን ዜጎችን በማስታወስ ዘመናዊ ቤቶችን ፤ የኢንዱስትሪ መንደሮችን ትምህርት ቤቶችን እና ጤና ማዕከላት ጨምሮ መሰል ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በብቃት በመገንባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ አለኝታነቷን አሳይታለች፡፡

በአጠቃላይ የአዲስ አመት መዳረሻ የሆነውን ጳጉሜን 2 የ"ማንሰራራት ቀን" ስናከብር በአዲስ አበባ የተከናወኑት ግዙፍ የሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደር ልማቶች እና ሰው ተኮር ኢኒሼቲቮች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የዜጎችን፣ በተለይም የሴቶችንና በችግር ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የቀን ተቀን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሻሉ መሆናቸውን ማስታወስ ይገባል፡፡

07/09/2026
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።"

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Address

Sar Bet
Addis Ababa
9206

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Roads Authority /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa City Roads Authority /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን:

Shortcuts

Share