Federal Civil Service Commission

Federal Civil Service Commission Historical sources indicate that the modern Ethiopian civil service began on October 24, 1907 (Tikimt 14, 1900 E.C.)
(1)

when Emperor Menelik II appointed the the first nine ministers.

በምስራቅ ባሌ ዞን የተከናወነ ስኬታማ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር*********አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 17/2018፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንበክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አነሳሽ...
23/08/2026

በምስራቅ ባሌ ዞን የተከናወነ ስኬታማ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር
*********
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 17/2018፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የክረምት በጎ አድራጎት ኢኒሼቲቭ በመደገፍ፤ ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሆኑት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ባሌ ዞን፣ ጊኒር ወረዳ፣ ሸወዴ ቀበሌ ሰፊ የበጎ አድራጎት ተልዕኮ አከናወኑ።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በቦታው ተገኝተው መርሀ ግብሩን ያስጀመሩና መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነሮች ክቡር ዶ/ር ጌታቸው ጀምበርና ክቡር አቶ ሽብሩ አባዲማም ተገኝተዋል፡፡
ለገጠር ኮሪደር ልማት ተስማሚ የሆኑ የ15 መኖሪያ ቤቶች እና የአንድ መዋለ ህጻናት ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ማኖር፣ 42,000 ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር፣ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ለሚገኙ 540 ህጻናት የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ፣ ከአካባቢው ወጣቶች ጋር የማነቃቃት እና የውይይት መድረክ ማካሄድ በክረምት በጎ አድራጎት መርሀግብሩ የተከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡

እስከ መጪው አዲስ ዓመት መባቻ ድረስ የቤቶቹን ግንባታ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ከዞኑ አስተዳደር ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ተጨማሪ 5 ቤቶች በዞኑ አስተዳደር የሚገነቡ ሲሆን፤ ጎን ለጎን አቅም ያላቸው አርሶ አደሮች ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው የራሳቸውን ቤቶች እንዲገነቡ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ በመሆኑ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አካባቢው ለገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎች ጥሩ ማሳያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በስፍራው የተገኙት የተቋማቱ የጋራ ልዑካን ቡድን ከተልዕኮው ጎን ለጎን ከጎባ-ሮቤ ከተማ 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን አስደናቂውን የሶፍ ዑመር ዋሻ ጎብኝተዋል፡፡ ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ታሪካዊ ዳራ ያለው ይህ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ስፍራው የሚያደርሰው መንገድ እየተሰራና አካባቢውም እየለማ በመሆኑ፣ ዜጎች ይህንን ሀገራዊ ሀብትና የቱሪስት መዳረሻ ቦታ ሄደው እንዲጎበኙ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል።
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

የፌዴራል ተቋማት አገልግሎቶችን ወደ መሶብ ለማስገባት የተዘጋጁ የአገልግሎት ልየታ ሰነዶች ተገመገሙ፡፡****************አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽ...
18/08/2026

የፌዴራል ተቋማት አገልግሎቶችን ወደ መሶብ ለማስገባት የተዘጋጁ የአገልግሎት ልየታ ሰነዶች ተገመገሙ፡፡
****************
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
የፌዴራል ተቋማት አገልግሎቶችን በመለየት፣ የአገልግሎት ፕሮሰስ ማፕ እና ካታሎግ በማዘጋጀት ወደ መሶብ ዲጂታል አገልግሎት ለማስገባት የተዘጋጁ ሰነዶች ግምገማ ተካሄደ።

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፌዴራል ተቋማት ከተጠሪ ተቋማቶቻቸው ጋር በመሆን የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች እንዲለዩ፣ የአገልግሎት ፕሮሰስ ማፕና ካታሎግ እንዲያዘጋጁ ከዚህ በፊት ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጥቷል።

ይህንን ተከትሎ በፌዴራል ተቋማት የተቋቋመው የአገልግሎት ልየታ ኮሚቴ፣ በኮሚሽኑ ደጋፊ ባለሙያዎች በመታገዝ የአገልግሎት ልየታ፣ ፕሮሰስ ማፕና ካታሎግ ዝግጅት ስራዎችን አከናውኗል።

በተከታታይ ለሦስት ቀናት በተካሄደው የግምገማ መድረክ፣ ተቋማቱ ያዘጋጇቸው የአገልግሎት ልየታ ሰነዶች በዝርዝር ተገምግመዋል። ግምገማው የተዘጋጁት ሰነዶች የሚፈለገውን የጥራትና የተግባራዊነት ደረጃ ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነበር፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በተገኙበት በተካሄደው መድረክ፣ “National Service Identification and Registration: External Transactional Government Services” በሚል ርዕስ ኮሚሽነሩ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነሩ በገለጻቸው የአገልግሎት ልየታውን አስፈላጊነት፣ ሊካተቱ የሚገባቸውን የትራንዛክሽናል አገልግሎቶች፣ መሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶችና የተለዩ አገልግሎቶች አመዘጋገብ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል።

በግምገማው የተለዩ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያዎች እንዲደረጉና ሰነዶቹ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተስተካክለው በድጋሚ እንዲቀርቡ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመድረኩ የስራና ክህሎት፣ ፕላንና ልማት፣ ገንዘብ፣ ጤና፣ ገቢዎች፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ውሃና ኢነርጂ፣ ከተማና መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ፣ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ ቱሪዝም፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢ፣ ባህልና ስፖርት፣ ውጭ ጉዳይ፣ ሰላም፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ፍትህ፣ ትምህርት እና ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከተጠሪ ተቋማቶቻቸው ጋር ተሳትፈዋል።

ተቋማቱ በቀጣይ ስራውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማጠናቀቅ የኮሚሽኑን ቀጣይ የቴክኒክ ድጋፍ ጠይቀዋል። ለተደረገላቸው ገለጻም አመስግነዋል፡፡ ክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌም የኮሚሽኑ የቴክኒክ ድጋፍ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

17/08/2026
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን  ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን  እና  ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት  ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደ...
11/08/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን እና ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ፣በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሐሴ 5 ቀን በወጣው መሠረት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች ለያንዳንዱ በተቀመጠው ሊንክ Online መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡Good Luck!!

+ ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ሊንክ 👇
https://forms.gle/TY3WhC7Mohh2rhGr6

+ ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ሊንከ 👇
https://forms.gle/tT99DadA3scHnC8j7

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን  ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሕፍት አገልግሎት፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እና  ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎ...
10/08/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሕፍት አገልግሎት፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እና ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ፣በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሐሴ 3 እና 4 ቀን በወጣው መሠረት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች ለያንዳንዱ በተቀመጠው ሊንክ Online መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡Good Luck!!

+ ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሕፍት አገልግሎት ሊንከ👇
https://forms.gle/dxgeogAqveHXyyTV7

+ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም 👇
https://forms.gle/Wip8f9qaPduHLvsX9

+ ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት 👇
https://forms.gle/rp6LqKDz6HrAikh48

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለአመራሮች በPower BI እና Canva አጠቃቀም ላይ ስልጠና ሰጠ::********አዲስ አበባ: ነሐሴ 2/2018:ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ...
09/08/2026

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለአመራሮች በPower BI እና Canva አጠቃቀም ላይ ስልጠና ሰጠ::
********
አዲስ አበባ: ነሐሴ 2/2018:ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለኮሚሽኑ አመራሮች በPower BI እና Canva አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የአቅም ማሳደጊያ ስልጠና አካሄደ።

በስልጠናው የኮሚሽኑ ምክትል አመራሮች ተሳትፈዋል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ሽብሩ አባዲማ የመንግስት ሰራተኞች ሥራ ስምሪት ም/ ኮሚሽነር፣ በስልጠናው የተገኘው ዕውቀትና ክህሎት በተግባር እንዲተረጎም አሳስበዋል።

በስልጠናው ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመዝጊያ ንግግራቸው የአደረጃጀትና ጥቅማ ጥቅም ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር፣ አመራሮች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ለማዳበር ጊዜ ሰጥተው በተግባር እንዲለማመዱ አሳስበዋል። በተጨማሪም ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በስራቸው ላሉ ባለሙያዎች በማስተላለፍ የዕውቀት ሽግግርን እንዲያጠናክሩ አደራ ሰጥተዋል።

ከስልጠና ወደ ተግባር፤ ከዕውቀት ወደ ውጤት!

#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

የኢስሚስ (ICSMIS) እና ኢፍሚስ (IFMIS) ትስስር ወርክ ሾፕ በአዳማ እየተካሄደ ነው+++++++++አዲስ አበባ ነሀሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን:የሲቪል ሰርቪስ...
07/08/2026

የኢስሚስ (ICSMIS) እና ኢፍሚስ (IFMIS) ትስስር ወርክ ሾፕ በአዳማ እየተካሄደ ነው
+++++++++
አዲስ አበባ ነሀሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን:
የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት መረጃ ስርዓት ኢስሚስ እና የተቀናጀ የፋይናንስ ማኔጅመንት መረጃ ስርዓት ኢፍሚስ ትስስር ላይ ያተኮረ ወርክ ሾፕ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ወርክ ሾፕ የመረጃ ልውውጥን ለማቃለል፣የባዬ ሜትሪክስ አቴንዳንስ ከፔሮል ጋር ለማስተሳሰር: የአስተዳደር ውጤታማነትን ለማሳደግ እና በመንግሥት የሰው ሀብት አስተዳደር እንዲሁም በፋይናንስ እንቅስቃሴዎች መካከል የተቀናጀ አሰራርን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላትና የቴክኒክ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
#የውጭ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለትምርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት  ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ፣በቋሚነት መቅጠር ይ...
05/08/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፡
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለትምርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ፣በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ Good Luck

በመሆኑም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 28 ቀን በወጣው መሠረት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተቀመጠው ሊንክ Online መመዝገብ ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡👇

https://forms.gle/8dCCcmTP7i1268pr6

Address

Bole Road, Kirkos S. City Woreda 09 Around Flamingo Restaurant
Addis Ababa
1082

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 02:30 - 17:30
Wednesday 02:30 - 17:30
Thursday 02:30 - 17:30
Friday 02:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal Civil Service Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Federal Civil Service Commission:

Shortcuts

Share