የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት Institute of Ethiopian Standards

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት Institute of Ethiopian Standards

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት  Institute of Ethiopian Standards The Institute of Ethiopian Standards has appointed a National Standard Agent for FDRE.

• Develop Ethiopian standards for products and services through stakeholder engagement
• Develop standards for indigenous products and make them competent internationally.
• Engaged in technical assistance, consultation and training on management system and product standards to facilitate the implementation of standard by various manufacturing and service providing organizations.

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት"የማንሠራራት ቀን ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋ...
07/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።"

ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን
06/09/2026

ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን

ለየኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ።ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.ለኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በተቋማዊ ለውጥና በደንበኞች አያያዝ ...
04/09/2026

ለየኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
ለኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በተቋማዊ ለውጥና በደንበኞች አያያዝ ላይ ያተኮረ የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ዱጋሳ ሙሉጌታ ሲሆኑ፣ በስልጠናውም የደንበኞችን ፍላጎትና ጥያቄ በትክክል መረዳት፣ በአክብሮትና በብቃት ማገልገል፣ ቅሬታዎችን በአግባቡ መቀበልና መፍታት እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ሰራተኞች ተቋሙን በተሻለ መልኩ ለመወከል፣ በስራ ቦታ አዎንታዊ አመለካከትን ለማዳበርና የተቋሙን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ደንበኛ ተኮር እንዲሆን ሊወሰዱ በሚገቡ ተግባራት ላይ አተኩሮ ስልጠናው ተሰጥቷል።

ስልጠናው የኢንስቲትዩቱን የሰራተኞች አቅም በማጎልበት የተሻለ የደንበኛ አገልግሎትና የተቋማዊ አፈጻጸም እንዲረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

የሀገሪቱን ልማት የሚያፋጥኑና ዓለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያልቁ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ  ተመላከተ፤የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት አመራርና መላው ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን የ6 ዓ...
04/09/2026

የሀገሪቱን ልማት የሚያፋጥኑና ዓለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያልቁ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ተመላከተ፤

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት አመራርና መላው ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን የ6 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግመዋል።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት አመራርና መላው ሰራተኞች ከ2013 እስከ 2018ዓ.ም በተከናወኑ የስትራቴጂክ ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በተከናወነው የግምገማ መርሃግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሰፋ ባለፉት 6 አመታት በኢንስቲትዩቱ ባሉ በሁሉም ክፍሎች አበረታች ስራዎች የተፈጸሙ መሆኑን ገልጸው ይህም መድረክ ባሳለፍናቸው አመታት የተከናወኑ ስራዎች ያሉበትን ተጨባጭ ሁኔታ በመፈተሽ የተሻሉትን ይበልጥ ለማላቅ፣ እንዲሁም ወቅቱን በሚመጥን የተጠናከረ የዲጂታል አገልግሎት እና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን ለማሳለጥ የሚረዳ ግብአት የምንወድበት መድረክ ነው ብለዋል።

በመቀጠል የዕቅድና ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን ጉደታ በኢንስቲትዩቱ ከ2013 እስከ 2018ዓ.ም የተከናወኑ የስትራቴጂክ ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችም በተቋሙ በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎች አመርቂ እንደነበሩና በተለይ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በርካታ ደረጃዎች መዘጋጀታቸው፣ አዳዲስ የስልጠና ዘርፎች መጀመራቸው፣ የዲጂታል አገልግሎቶች በተጠናከረ መልኩ መስፋፋታቸው፣ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎአችን መጠናከሩ፣ በደረጃ ምልክት አስተዳደር እና በጥናትና ምርምር ዘርፎች እንዲሁም ሌሎች የተፈፀሙ በርካታ ስራዎች የሚበረታቱና በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ያሉ ሲሆን ቢታረሙና ቢጠናከሩ ያሏቸውን የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል።

ከሰራተኞች ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች በተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተሮች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በማጠቃለያ ማብራሪያቸው እስካሁን የተፈፀሙ ውጤታማ ተግባሮች ወሳኝና ዋጋ ልንሰጣቸው የሚገቡ ናቸው ያሉ ሲሆን ለነገ ስኬታችን መሰረት የሚሆኑ በመሆናቸው ልንጠብቃቸው ይገባል ብለዋል። አክለውም ለቀጣይ ስራ ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን ገልጸው
ለተሻለ አገልግሎት ሚያበቁ የሰራተኞች የስልጠናና የአቅም ማጎልበቻ ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሰፋ በሰጡት ማጠቃለያ በሁሉም ዘርፍ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ አሳስበው ለተግባራዊነቱም ሁሉም ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ግዴታና ኃላፊነት ለመወጣት ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

ጳጉሜን፣ የኢትዮጵያ መንሠራራት!ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ መንሠራራት በሚል መሪ ሐሳብ፣ በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎች ይከበራል...
04/09/2026

ጳጉሜን፣ የኢትዮጵያ መንሠራራት!

ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ መንሠራራት በሚል መሪ ሐሳብ፣ በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎች ይከበራል፡፡

የጳጉሜን ቀናት አከባበር ዐቢይ ዓላማ ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ ከፍታ ማንሠራራት መጀመሯን በማብሰር፣ ለበለጠ ሀገራዊ ውጤት ከፍተኛ መነሳሳትንና የተስፋ መንፈስ መፍጠር ነው።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ መንሠራራት ከንግዱ ዘርፍ፣ ከጥራት ተቋማት፣ ከባለ ድርሻ አካላት እና ከተቋማችን ማህበረሰብ ጋር ኅብር በመፍተጠር ይተጋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከሴት ኤክስፖርተሮች ተወካዮች ጋር ተወያየ።ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሴት የወጪ ምርት ነጋዴዎችን በመደገፍ ከ...
03/09/2026

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከሴት ኤክስፖርተሮች ተወካዮች ጋር ተወያየ።

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሴት የወጪ ምርት ነጋዴዎችን በመደገፍ ከፍተኛ ሚና ካለው ከሴት ኤክስፖርተሮች ተወካዮች ጋር በደረጃ ምልክት፣ በምርት ጥራትና በደረጃ ትግበራ ዙሪያ በመተባበር ሊሰራባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል።

ኢትዮጵያ የጣምራ የደረጃ ምልክት (Dual Standard Mark) በመጠቀም ውጤታማ በመሆን በአፍሪካ ካሉ 5 ግንባር ቀደም ሀገራት መካከል አንዷ ሆና እውቅና ከተሰጣት በኋላ በርካታ ኤክስፖርተሮች በአፍሪካ ገበያዎች ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ተግባራት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመቀናጀት እያከናወኑ ይገኛል።

የካዌ ድርጅት ዋና መስራችና ዋና ዳይሬክተር ንግስት ሀይሌ (ዶ/ር) የሴት ኤክስፖርተሮችን በመወከል በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው ባደረጉት ገለጻ፣ ሴት ኤክስፖርተሮቹ ያመረቷቸውን ምርቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየላኩ እንደሚገኙ ተናግረው ሆኖም ምርቶቹን ወደ ውጭ ገበያ በማስገባት ሂደት የሚያጋጥማቸው ዋና ተግዳሮት ከደረጃ መስፈርቶችና የደረጃ ምልክት ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች መሆኑን ጠቁመዋል።
በመሆኑም ከኢንስቲትዩቱ ጋር በደረጃ ትግበራና በምልክት አጠቃቀም እንዲሁም በምርት ጥራት ማረጋገጥ ዙሪያ ተባብሮ ለመስራትና ተቋማዊ ድጋፍን ለማግኘት ጠይቀዋል።

በምክክሩ የተገኙት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ የተወካዮቹን በኢንስቲትዩቱ መገኘት አበረታትተው ኢንስቲትዩቱ በደረጃ ዝግጅት፣ በደረጃ ትግበራ እና ከደረጃ ምልክት አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለተወካዮቹ አስረድተዋል።

በተጨማሪም ሴት ኤክስፖርተሮቹ ያመረቷቸው ምርቶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ገበያዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲገቡና ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ ከምርቶቻቸው ጋር የተጣጣሙ ደረጃዎችን (Harmonized Standards) መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመው የኢንስቲትዩቱን የደረጃ ምልክት ከአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት (ARSO) የደረጃ ምልክት ጋር በማጣመር (Dual Mark) መጠቀም ምርቶቻቸው በአፍሪካ ገበያ ተቀባይነትን እንዲያገኙና የገበያ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠቃሚ መሆኑን አብራርተዋል።

ዶ/ር መሰረት አክለውም፣ ኢንስቲትዩቱ ሴት ኤክስፖርተሮቹ የደረጃ ምልክቶቹን እንዲጠቀሙና የምርቶቻቸውን ጥራት እንዲያሻሽሉ በሙሉ ፈቃደኝነት የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው በተጨማሪም የደረጃዎቹን ትግበራ ለማሳለጥ የሚያግዙ ስልጠናዎችን፣ የማማከር አገልግሎቶችንና የቴክኒክ ድጋፎችን በመስጠት ከሴት ኤክስፖርተሮቹ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የሴት ኤክስፖርተሮች ተወካዮችም በምርቶቻቸው ጣምራ ምልክትን (Dual Standard Mark) ለመጠቀም ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸው የምርቶቻቸውን ጥራት በማሻሻልና ደረጃን በመተግበር ለውጭ ገበያ ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማቅረብ ኢንስቲትዩቱ የሚያደርገው ድጋፍ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል።

በአፍሪካ ገበያዎች ያለውን የንግድ እድል ለማስፋት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቀጣይነት በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ሄልፕ ሎጀስቲክስ (HELP Logistics) የተባለ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በሚሰራባቸ...
02/09/2026

በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ሄልፕ ሎጀስቲክስ (HELP Logistics) የተባለ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ።

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
ውይይቱ ያተኮረው፣ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ የምግብና የጤና ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሚያጋጥሙ የጉምሩክ እንቅፋቶች ላይ ድርጅቱ በቀረጸው ፕሮጀክት ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችል አግባብ ላይ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ ሄልፕ ሎጀስቲክስ ለሰብዓዊ እርዳታ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ምርቶች ለተረጂዎች ከመድረሳቸው በፊት በሚኖሩ ሁኔታዎች ላይ አስፈላጊውን ትብብር እንዲደረግለት ኢንስቲትዩቱን መጠየቁ በጎ አላማ መሆኑን ጠቁመው፣ ምርቶቹ የኢትዮጵያን ደረጃ የሚያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ድርጅቱ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፣ ኢንስቲትዩቱ ደረጃዎችን ከማዘጋጀት ባለፈ ደረጃዎችን ለመተግበር የሚያስፈልግ ስልጠና፣ የቴክኒክ ድጋፍና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ለድርጅቱ ተወካዮች አብራርተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የስኪምና የደረጃ ምልክት አስተዳደር ስራዎችን እንደሚያከናውን ጠቅሰው ደረጃዎች የሚያመጡትን ተጽዕኖ ለመገምገምና ሀገር በቀል ደረጃዎችን እንዲዘጋጁ መነሻ ሀሳብ የሚሆን የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንደሚያከናውንም አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ጥራታቸውን የጠበቁና የኢትዮጵያን ደረጃ የሚያሟሉ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ የምግብና የጤና ምርቶች ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ኢንስቲትዩቱ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ በማረጋገጥ የጉምሩክ ሂደቱን ለማሳለጥ ደረጃዎችን በማጣጣም ረገድ ከአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት ጋር በጋራ እየሰራ ከመሆኑም በተጨማሪ አስመጭዎች የአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅትና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃ ምልክቶችን በጋራ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ለድርጅቱ ተወካዮች አብራርተዋል።

የዚህ ግንኙነት መነሻ የሆነው ፕሮጀክት በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን የጉምሩክ ዝግጁነት ፓይለት ፕሮጀክት (Customs Readiness Pilot Project Ethiopia) ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ ጤና ነክ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ባሉ የጉምሩክ የማስተላለፍ ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ አሰራሮችን እንዲሁም የቅንጅት ስራዎች ጋር በተገናኘ ያሉ ችግሮችን በማጥናት የመፍትሄ ሀሳቦችን በመሰነድ በሂደቱ ለሚሳተፉ አካላት የምክር አግልግሎት ለማቅረብ የተነደፈ ፕሮጀክት ነው።

An international non-governmental organization called HELP Logistics, which operates with the support of the World Economic Forum, held discussions with the Institute of Ethiopian Standards on areas of joint cooperation.

August 20, 2026 - IES

The discussion focused on how to collaborate with the institute regarding a project designed by the organization to address customs obstacles encountered when importing food and health products intended for humanitarian aid into the country.

The Director General of the Institute, Dr. Meseret Bekele, noted that HELP Logistics' request for the necessary cooperation regarding conditions prior to delivering humanitarian aid imports to beneficiaries was a good initiative, and called on the organization to work closely with the institute to ensure that the products meet Ethiopian standards.

The Director General added and explained to the Delegation that the Institute is working on developing standards, and provides the necessary training, technical support, and advisory services required to implement standards.

In addition, she mentioned that it carries out standard mark administration activities, as well as conducting research and study work to evaluate the impact of standards and serve as a basis for developing indigenous standards. Assuring that the institute will play its part to ensure that quality humanitarian food and health products meeting Ethiopian standards.

The Director General explained to the Delegates that it is working jointly with the African Organization for Standardization (ARSO) to harmonize standards to speed up the customs process, and that importers are jointly using the standard marks of both ARSO and the Institute of Ethiopian Standards.

The project that formed the basis of this partnership is currently in the implementation phase. The "Customs Readiness Pilot Project Ethiopia" is designed to study processes and coordination challenges associated with customs clearance procedures for importing health-related humanitarian aid products into Ethiopia, document proposed solutions, and provide advisory services to stakeholders involved in the process.

በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸው ምርትና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ደረጃን የሚተገብር ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ፤የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋ...
01/09/2026

በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸው ምርትና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ደረጃን የሚተገብር ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ፤

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያካሄደው አመታዊ የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
ኢንስቲትዩቱ ባዘጋጀው አመታዊ ምክክር መድረክ
መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ የውይይት አጀንዳዎች ቀርበው ምክክር ተደርጓል።

በመድረኩ የደረጃ ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ይልማ መንግስቱ የደረጃ ዝግጅት፣ ትግበራ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ሚና እና አለም አቀፋዊ ተሳትፎና ተሞክሮዎች ላይ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም የጥናትና ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ግርማ ረጋሳ በተመረጡ ተቆጣጣሪ ተቋማት ላይ ያተኮረና የደረጃ አተገባበርን የሚመለከት ጥናትና በጥናቱ የተገኙ ግኝቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተጨማሪም የስኪምና የደረጃ ምልክት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኦሊያድ ሌንጮ የደረጃ ምልክት አጠቃቀምና በደረጃ ምልክቶች አጠቃቀም ላይ የተሰራ የዲጂታል አገልግሎትን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ የሆኑት ባለድርሻ አካላትም የቀረቡትን ማብራሪያዎች መነሻ በማድረግ በማድረግ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

በተነሱት ሀሳቦች ላይም ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።
ዶ/ር መሰረት በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ የምክክር መድረኩ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው በተሳታፊዎች የተሰጡን አስተያየቶችም ለቀጣይ እንደተቋም የተሻለ ስራ እንድንሰራና በዘርፉ አመርቂ ውጤት ለማምጣት እንድንችል የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በሀገራችን ደረጃን የሚተገብር ማህበረሰብ ለመገንባትና ማንኛውም ምርትና አገልግሎትም በቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ገበያዎች ተቀባይነት ያላቸው አንዲሆኑ ለማስቻል የተጠናከረ ስራ በትኩረት እንደሚሰራና ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሰፋ በደረጃ ትግበራ ላይ ማብራሪያዎችን የሰጡ ሲሆን ጥራትን ባህል ለማድረግና በዘርፉ በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ባለድርሻ አካላት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በንቃትና በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ሀገራችን የአፍሪካ የንግድ ቀጠና አባል መሆኗና የአለም የነፃ ንግድ ላይ ለመቀላቀል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከጫፍ በደረሰበት በዚህ ወቅት ለዛ የሚመጥኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸው ከደረጃ ዝግጅት ጀምሮ እስከ አተገባበር ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ
ባለድረሻ አካላት ያላቸው ሚና ላቅ ያለ በመሆኑ የተያዙ እቅዶች እንዲሳኩ በየዘርፉ እርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በአመታዊ የምክክር መድረኩ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች፣ ከአስፈጻሚና ተቆጣጣሪ አካላት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከተለያዩየሙያ ማህበራት፣ ከምርምር ተቋማትና ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት የተወከሉ ተሳታታፊዎች የተገኙ ሲሆን ውይይቱም በመግባባት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር አመታዊ የምክክር መድረክ አካሄደ።ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር አ...
01/09/2026

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር አመታዊ የምክክር መድረክ አካሄደ።

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር አመታዊ የምክክር መድረክ ሲያካሄድ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ - ተቋሙ ባሳለፍነው የስራ ዘመን ደረጃዎችን ከማዘጋጀት ባሻገር አተገባበሩ ላይ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የደረጃ ምልክት አስተዳደር ስራዎችን በመተግበር ወቅቱ በሚፈልገው መልኩ የዲጂታል ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ "IES verifier" የደረጃ ምልክት ማረጋገጫ የሞባይል መተግበሪያን በማዘጋጀት ጥራትን በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ ጥራትና ተቀባይነት ያላቸው ምርቶች እንዲኖሩና የንግድ ስርአቱንም በማሳለጥ በአፍሪካ ሀገራት ገበያዎች የሀገራችን ምርቶች በቀላሉ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማስቻል አምራቾች የጣምራ የደረጃ ምልክት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደተሰራ ተናግረዋል። አክለውም የጣምራ ምልክት ላይ ከመስራት አኳያ ከጥቂት ውጤታማ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆን መቻሏን አስታውቀው በዚህም ኢንስቲትዩቱ አህጉራዊ እውቅና እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ባሳለፍነው አመት በርካታ ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ሰርተናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ይህ የምክክር መድረክም በርካታ ግብአት የምናገኝበትና በቀጣይ ጊዜያት የላቀ ስራ ለመስራት የሚያስችለንን ምቹ ሁኔታዎችንም የሚፈጥርልን ነው ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

ጥራት የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ዋነኛ መሸጋገሪያ መንገድ እንደሆነ ተገለፀ፤2ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት መድረክ በጥራት መንደር ውስጥ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የጥራት አዳራሽ ተ...
28/08/2026

ጥራት የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ዋነኛ መሸጋገሪያ መንገድ እንደሆነ ተገለፀ፤

2ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት መድረክ በጥራት መንደር ውስጥ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የጥራት አዳራሽ ተካሄደ።

ነሀሴ 22/2018 አ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
በዛሬው እለት ምን ከማን መልቲ ሚዲያ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት 2ኛ ሀገር አቀፍ የጥራት መድረክ መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱም ፓናሊስት የነበሩት የኢትዮጲያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ "ጥራትና ደረጃ ተስስራቸው ምንድን ነው?" በሚለው እና በሌሎችም የውይይቱ ዋነኛ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ባደረጉት ገለፃ ኢንስቲትዩቱ የጥራት መሰረት የሆኑትን ደረጃዎችን በማዘጋጀት፣ የደረጃዎችን መተግበር እውን ለማድረግ ለአምራችና ለአገልግሎት ሰጪና ለተለያዩ ተቋማት የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት፣ ለምርቶች የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፍቃድ በመስጠተና በማስተዳደር፣ የደረጃዎች አተገባበርን ለማላቅና አዳዲስ ደረጃዎች ኢንዲዘጋጁ የጥናትና ምርምር ስራዎች በማከናወን ለጥራት መረጋገጥ መነሻና ዋና የሆኑ መሰረታዊ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ኢንስቲትዩቱ አለት ከእለት ከሚከውናቸው ተግባራት ከፍ ባለና የሀገሪቱን ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ የሚመጥን ስራዎች እየከወነ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር መሰረት፣ ኢንስቲትዩቱ የሚሳጣቸውን አገልግሎት ወቅቱን በሚመጥን መልኩ በማዘመን የምርቶችን ጥራት ለማወቅ እና የደረጃ ምልክቶችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ IES verifier የሞባይል መተግበሪያ መዘጋጀቱንም አብራርተዋል።

በተጨማሪም በአፍሪካ የደረጃ ተቋም ARSO የሚካሄድ Essay ውድድርን ኢንስቲትዩቱ አብሯቸው የሚሰራባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ድርጅቶችን በማሳተፍ ጥራትና ደረጃ ላይ ያተኮሮ የጥናት ፅሁፎች እንዲዘጋጁ በማድረግ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ተወዳድረው አንደኛ በመውጣት ማሸነፋቸው እንዲሁም በጣምራ የደረጃ ምልክት አተገባበር ላይ ከ5 የአፍሪካ ሀገራት ግንባር ቀደም ሆነን መገኘታችን ምን ያህል ጥራትን የሚያረጋግጡ ስራዎች መሰራታቸውን ማሳያ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በ2ኛው የጥራት መድረክ መርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ አካላትም ለፓናሊስቶች የተለያዩ ጥያቄ አንስተው
በዋና ዳይሬክተሮች ምላሽና ማብራሪ ተሰጥቷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ተቆጣጣሪ አካላት፣ አምራቾች፣ የሸማች ተወካዮች፣ በዘርፉ የሚሰሩ ሚዲያዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
For Additional information

Website:-
https://ies.gov.et
LinkDin:- https://www.linkedin.com/company/institute-of-ethiopian-standards-ies/
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EeqTnj4sk/?mibextid=wwXIfr
Email :- [email protected]

Address

Around Megenagna
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251116460111

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት Institute of Ethiopian Standards posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት Institute of Ethiopian Standards:

Shortcuts

Share