07/09/2026
"የማንሰራራት ቀን "ን አስመልክቶ የወርቃማ ሰኞ የፓናል ውይይት ተካሄደ
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ የወርቃማ ሰኞ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
የውይይቱ ዋና ዓላማ የማንሰራራት ቀን የሚያስተላልፈውን መልዕክት በማጉላት፣ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችንና ስኬቶችን በመገምገም ቀጣይ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።
በፓናል ውይይቱ የማንሰራራት ትርጉምና ጠቀሜታ፣ ከተሞችን በተሻለ ደረጃ ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች፣ የመንግስት ሰራተኛው የጋራ ኃላፊነት እንዲሁም የተጀመሩ መልካም ተግባራትን ወደ ዘላቂ ልማት ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሀሳብ ተለዋውጧል።
ተሳታፊዎችም ያለፈውን ልምድ በመገምገም የተሻለ ነገን ለመገንባት ከግለሰብ እስከ ተቋምና ማህበረሰብ ድረስ የሚጠበቀውን ሚና በተግባር መወጣት እንደሚገባ ተገልጿል።
በወረዳ ደረጃ የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል የነዋሪዎችን ኑሮና የአካባቢውን ገጽታ ለማሻሻል በትብብር መስራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።